Get Mystery Box with random crypto!

በጣም አስደንጋጭ ነው። ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር ማረፋቸውን ሰማሁ። ብፅዕነታቸው ሐምሌ 9 ቀን | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

በጣም አስደንጋጭ ነው። ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር ማረፋቸውን ሰማሁ። ብፅዕነታቸው ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አንብሮተ ዕድ ከሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ። ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ነበሩ። ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል።

በረከታቸው ይደርብን።