Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ 5 ዓመት ደብረ ዳሞ ላይ እንዳየሻቸው ያሉ ሴት መነኮሳት ተደፍረዋል ስልሽ ሰውነቴን እየሰቀጠ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የዛሬ 5 ዓመት ደብረ ዳሞ ላይ እንዳየሻቸው ያሉ ሴት መነኮሳት ተደፍረዋል ስልሽ ሰውነቴን እየሰቀጠጠኝ ነው።

በመሃል ሜዳ መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ቀበሌ 03 አንዲት የ20 ዓመት ሴት በሦስት የትግራይ ሰዎች የተደፈረችው የ80 ዓመት አባቷን አውጥተው ውጪ ግንድ ላይ አስረው እና የ2 ዓመት ሕፃን ልጇ ፊት ላይ ነው። አስቢው እንግዲህ...አባትሽ አይኑ እያዬ ስትደፈሪ፣ ህፃን ልጅሽ እይኗ እያየና እያለቀሰች ስትደፈሪ? አየሽ ፅጌረዳ ከአንቺ ላይ ያለው ቁስል ከዐማራ ሴቶች ላይ አለ። ህመሙ የሁላችንም ነው። ጦርነቱ የእብሪተኞችና የቁማርተኞች ነው። እነሱ ምንምን አልሆኑም፣ የድሃ ልጆች ግን አለቁ። እነሱ ተደራደሩ የድሃ ልጆች ግን አካለ ጎደሉ ሁነው ቀሩ። ዛሬ አንቺ በሰው ሸክም የምትንቀሳቀሽ አካል ጉዳተኛ ሆነሻል፣ የሕወሓት ልጆች ግን አውሮፓ እየተማሩ ናቸው። አሁንም መፍትሔው በኢትዮጵያ የዘረኝነት ፖለቲካ በህግ እንዲታገድ መታገል ነው። እንደ በርሊን ግንብ አለያይቶ የሚያናክሰንን ሕገመንግሥት ተብዬ ቀዳዶ መጣል ነው። አሁንም በየሚዲያው እየወጡ የሚፎክሩትን ሁላችንም "በቃችሁ!" ማለት ነው። በፅጌረዳና በኢክራም 'ይብቃ!' ማለት አለብን።

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut