Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.80K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-05 13:09:02 #ሼር_ፖስት! ብልፅግና ሆቴል ውስጥ አስቀምጦ እንደ ሰንጋ በሬ የሚቀልባቸው አክቲቪስቶች ይህን ዘግናኝ አገዳደል (horrifying killing) ከማውገዝ ይልቅ ለማስተባበል የሄዱበት እርቀት ያስገርማል። እነዚህ አእምሯቸው የታጠበ አክቲቪስት ተብየዎች ሰብአዊነት ከማስቀደም ይልቅ የመሪያቸውን ገመና ለመሸፈን ሲጋጋጡ ማዬት ያሳዝናል።አንድ እውነት ግን መታወቅ ይኖርበታል እንዲህ ያለ ግድያ እየተፈፀመ ያለው በኦህዴድ ብልፅግና ዘመነ መንግሥት፣ በአብይ አሕመድ የሥልጣን ዘመን እና በብርሃኑ ጁላ ፊልድ ማርሻል ዘመን ነው። ታሪክም መዝግቦ የሚያስቀምጠው በዚህ መልኩ ነው። ሁለት ኦርቶዶክሳዊን ወጣቶችን በገመድ ለኋሊት የፍጥኝ በማሰር አነጣጥረው ተኩሰው የገደሏቸው የመከላከያ ዩኒፎርም የለበሱ ናቸው። እንዴት እንደገደሏቸውም ቪዲዮ ቀርፀዋል። ቪድዮውን ሚቀርፃቸው ሌላ ሶስተኛ ወገን ሳይሆን ደግሞ እራሳቸው ገዳዮቹ ናቸው። ከቪድዮ ቀራጩ ውጭ በቁጥር አራት ሲሆኑ፣ ሁሉንም የመከላከያ ዩኒፎርም ልብስ የለበሱ ናቸው።

አብይ አሕመድ ወደሥልጣን ከመጣ ጀምሮ እንደዚህ ያሉ ግድያዎች ተራ ጉዳይ ሆነዋል። ባጠቃላይ ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2015 በዐማራ ከተፈጸሙ ግድያዎች መካከል እነዚህ ይገኙበታል፣

1. ወደ ገደል መጣል
2. ጡት መቁረጥ
3.ብልትና ምላስ መቁረጥ
4.ሥጋቸውንም ቆርጦ ማብላት
5.በድንጋይ መቀጥቀጥ
6. በሜንጫ እና በስለት ማረድ
7. በቀስት መውጋት
8. ፅንስ ማቋረጥ
9. በጅምላ መረሸን
10.በእሳት ማቃጠል...ወዘተ ይገኙበታል።

እነዚህን በጥቂት ምሳሌዎች ላስረዳ!

ሀ. #ወደገደል_መጣል፦ የዐማራ ተወላጆች ከተገደሉባቸው ገደሎች መካከል በወልቃይት ገነሃም ግንብ እና እመን አላምንም፣ በኦሮሞ ክልል እንቁፍቱ ገደል፣ ሞሶ ጊዎርጊስ ገደል፣ ጥርሶ ገደል፣ ኩርባ ጀርቲ ገደል ይገኙበታል። የአገዳደሉ ስልት የኋሊት በማሰር፣ ዐይናቸው ሸፍኖ ወደገደሉ ጫፍ ከአስጠጓቸው በኋላ በጥይት በማርከፍከፍ እንዲወድቁ ማድረግ አንደኛው ነው። ሁለተኛው አገዳደል እጅና እግራቸውን በማሰር ፊታቸውን በመሸፈን ከነሕይወታቸው ወደጥልቁ ገደል መጣል ሲሆን፣ ሦስተኛው አንገታቸውን በሰይፍና በሜንጫ ቀልቶ መወርወር ናቸው።

ሕወሓት ከደጀና ከተማ በስተሰሜን ምስራቅ በኩል ወደሚገኘው "እመን አላምንም" እየተባለ ከሚጠራው ወደ 200 ሜትር ከሚረዝመው የገደል አፋፍ ላይ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራዎችን በመወርወር ይገድላቸው ነበር። በተመሳሳይ የዐማራው ልኳንዳ አራጅ ኦነግ ደግሞ በደኖ መግቢያ ላይ ከሚገኘው የእንቁፍቱ ገደል ዐማሮችን እጃቸው በገመድ እያሰረ ዐይናቸው በሻሽ እየሸፈነ ይጥላቸው ነበር። ለምሳሌ፣ አፈሩን ገለባ ያድርግላቸውና አቶ አበበ ምትኬ በሐረርጌ የበደኖ ከተማ ኗሪ ነበሩ፡፡ በ1984 ዓ.ም. በበደኖ ዕልቂት ሙሉ ዘጠኝ ቤተሰቦቻቸውን ከነነፍሳቸው አስረው እንቁፍቱ ገደል በመወርወር ጨረሷቸው። (ምጽአተ ዐማራ፣ 327)

ለ.#ጡት_መቁረጥ፦ በጃዋር ምክንያት ዶዶላ ላይ የሁለት ህፃናት እናት የነበረችው ዘምሼ ሲሳይ የገደሏት ጡቷን ቆርጠው ነው። ኦነግ በ1984 ዓ.ም. ብቻ በሐረርጌ ክፍለሀገር፣ ደጉ መድኃኔዓለም 3፣ ከሀረር ከተማ በ7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ፈዲስ 7፣ ከበደኖ አለፍ ብላ ከምትገኘው ቡርቃ 4 ባጠቃላይ 14 የዐማራ ሴቶችን ጡት ቆርጧል። (ምጽአተ ዐማራ፣ 329)

ሐ.#ብልትና_ምላስ_መቁረጥ፦ በምሥራቅ ወለጋ ህዳር 21 ቀን 1993 ዓ.ም. በጊዳ ኪራሞ ወረዳ፣ ዲቡክ ማርያም 1100 የሚሆኑ የብሉይ ዘመን ሕይወትን የሚገፉ ሚስኪን ዐማሮችን ሕፃናት፣ አዛውንቶችና ሴቶች አልቀዋል። በወቅቱ ጦቢያ መጽሔት "የዐማራው ሕዝብ ዕልቂት በአንድ ዘር ላይ የተነጣጠረ ጥቃት" በሚል ይዞት በወጣው ልዩ ጥንቅር ከዕልቂቱ አስከፊ ገጽታ መካከል የሚከተለውን በዝርዝር ይገልጻል፣

"አባ በላይ ዋለ የተባሉትን ዓይነ ሥውር ገደሏቸው። 'ዐማራ ዐማራ ነው' ብለው ብልታቸውን ቆረጡት። መልካሙ ውባለምን አርደው ገደሉትና ምላሱን አውጥተው ወሰዱት።
(ጦቢያ መጽሔት፣ ቅጽ 8፣ ቁጥር 8፣ 1993)

መ.#ሥጋቸውንም_ቆርጦ_ማብላት፦ በዐማራ ላይ ከተፈፀሙ የግድያ አይነቶች ሌላኛው ልብሳቸውን እያስወለቁ ሥጋቸውን እያበሉ መግደል ነው። ለምሳሌ፣ ገቦ ሀብሩ ወረዳ አቶ ፀደቀ አውሉው የሚባል የዐማራ ተወላጅን መጀመሪያ ወርቅ ጥርሱን አውልቀው ወሰዱ። ቀጥሎ ሰውነቱን እንደ ጥሬ ሥጋ በመቆራረጥ እያበሉ ገደሉት። በገለምሶ በልበልቲ ይኖር የነበረው አቶ ገብሬ አወቀ የሚባል ሕዝብ በተሰበሰበት በሚስማር እንደ ክርስቶስ እጅና እግሩን ቸንክረው በመጀመሪያ ብልቱን ከዚያም የተለያየ የአካል ክፍሉን እየቆራረጡ እያበሉ ገድለውታል።

ሠ. #ፅንስ_ማቋረጥ፦ "የዐማራ ልጅ አይወለደም" እያሉ ፅንስን መግደል በዐማራ ከተፈፀሙ ዘግናኝ ግድያዎች መካከል አንዱ ነው። በሃጫሉ ሞት ምክንያት በተነሳ አመፅ ሻሸመኔ ከተማ የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡር መሬት ላይ ጥለው፣ ልብሷን አስወልቀው፣ እግሯን ይዘው እየጎተቱ "የዐማራ ልጅ አይወለድም፤ የክርስቲያን ልጅ አይወለድም፤ ግደላት ሰንጥቅና አሳየኝ " እያሉ ሜጫቸውን፣ ጩቤያቸውንና መጥረቢያቸውን ወደ አንገቷ እና ሆዷ አስጠግተው እየሳሉ አሰቃይተው ከነፅንሷ እስከወዲያኛው ህይወቷ እንዲያልፍ ሆኗል። ሕወሓትም በጦርነቱ ወቅት "የዐማራ ልጅ ተወልዶ አድጎ ይወጋናል" በሚል ከእናቱ ሆድ እያለን ፅንስ በርግጫ እና በሰደፍ እየጨፈለቀ አጨናግፏል።

ሰ. #በእሳት_ማቃጠል፦ ሰኔ 11ቀን 2014 ዓ.ም በምዕራብ ወለጋ ግምቢ በምትገኘው ቶሌ ቀበሌ ከ600 በላይ የሚሆኑ ዐማሮችን ተጨፍጭፈዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ዐማሮች በብዛት በሚኖሩበት የቶሌ መንደሮች ጉቱ፣ ጨቆርሳ፣ ስልሳው፣ በገኔ፣ ጫካ ሰፈር እና ሀያው ሲሆን፣ ከተፈጸሙ ዘግናኝ አገዳደሎች መካከል በእሳት ማቃጠል ይገኝበታል። ከላይ በተጠቀሱት መንደሮች ወደ 22 የሚሆኑ ዐማሮች በር ተዘግቶባቸው ከነሕይወታቸው ቤታቸው ውስጥ ተቃጥለዋል።

ባጠቃላይ ከኢትዮጵያዊያን ባሕል፤ ሃይማኖት፤ ሞራል እና ሰብአዊነት ተግባር ባፈነገጠ መልኩ በዐማራ ላይ ያልተፈፀመ የግድያ አይነት የለም። እነዚህ አውሬዎች በዐማራ ላይ እንዲህ ያለውን ዘግናኝ ድርጊት ሲፈፅሙ በደስታ ነው። የዐማራ ሴቶችን ጡት ጥሬ ስጋ እንደሚበላ ሆዳም ሰው ተስገብግበው ሲቆርጡት በኩራት ነው። አይሁዶች በክርስቶስ በየተራ እንደተዘባበቱበት ሁሉ እንደ በግ ጠቦት ለመግደል ባዘጋጁት ዐማራ ላይ ሲዘባበቱ በሲቃ ነው። ምክንያቱም ይህን እያደረጉ ያሉት በዐማራው ላይ ስለሆነ!
16.3K viewsTadele Tibebu, edited  10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 12:54:47
20.6K viewsTadele Tibebu, 09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 12:54:38
19.1K viewsTadele Tibebu, 09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 12:53:47 #ሼር_ፖስት! በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በዳንሻ፣ በወፍ አርግፍና በሌሎች አካባቢዎች ደማቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።ይህ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ በአደባባይ ያሰማው ድምፅ፦

☞ ወልቃይት ጠገዴ የከለው ልጅ የአማራ ዘር ግንድ መነሻ ነው!

☞ለእንግዶች እንጂ ለወንጀለኞች ቦታ የለንም!

☞ለነፃነታችን ዋጋ ከፍለንበታል፣ ወደኋላ ላንመለስ ነፃ ወጥተናል!

☞አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም!

☞የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍፁም ፍትሐዊና ህጋዊ ነው።

☞የማይገባንን አልፈን አንጠይቅም፣ የራሳችንንም አሳልፈን አንሰጥም!

☞የወልቃይት ጠገዴ እና የራያ አማራ የማንነት ጥያቄን "የርስት ማስመለስ ብሎ በመፈረጅ አማራን ማሸማቀቅ አይቻልም ! ሀገር ርስት ነው! ለርስት መሞት ክብር ነው!"

☞ የፖለቲካ ሴራ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ለድጋሜ እልቂት እንጂ ሰላምን አያመጣም የሚሻለው መራራውን ሀቅ መቀበል ብቻ ነው!


☞በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ላይ ለተፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፍትህ ካሳ እንፈልጋለን!

☞ተበዳይ እንጂ በዳይ፤ ተጨፍጫፊ እንጂ
ጨፍጫፊ፣ ተወራሪ እንጂ ወራሪ፤ ተፈናቃይ እንጂ አፈናቃይ አይደለነም!

☞ የትግራይ ህዝብ ሆይ መጣችሁብን እንጅ አልመጣንባችሁም የመጭው ዘመን የሰላም ሁኔታ በእጃችሁ ነው፣ ከተከዜ በመለስ አማራ የመሆኑን ሀቅ ተቀበሉና ጥሩ ጎረቤት እንሁን!

☞ በዳይ የተበዳይን ጩሆት ነጥቆ ተበዳይ ለመምሰል የሚደረግ አካሄድ ዓይነ ደረቅነት ነው!

☞ ወንጀለኞች ለህግ ይቀርባሉ እንጅ በተፈናቃይ መልክ እናስፍር አይባልም!

☞ አማራዊ ማንነታችን እና የወሰን አስተዳደር ግዛት በህግ አግባብ ይከበር!

☞ ከትግራይ ጋር ደንበራችን ተከዜ ነው።
18.4K viewsTadele Tibebu, 09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 20:23:46
15.9K viewsTadele Tibebu, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 20:23:19 #ሼር_ፖስት! አማርኛ ቋንቋ እንደሆነ የራሡ የሆነ ሥርዓተ ድህፈት (Orthography) ያለው፣ ከፍተኛ የሆነ የሰዋሠው (Grammar) እና የሥነ-ልሣን (Linguistics) ጥናትና ምርምር የተደረገበት፣ በአፍሪካ ምድር በስነ ጽሁፍ ሀብት የበለጸገ ብቸኛውና ነባር ዓለምአቀፍ ቋንቋ ነው።

ከትግራይ ሥርዓተ ትምህርት ብታስወግደው በ2007 ዓ.ም.የአፕል የቴክኖሎጂ ማዕከል አማርኛን ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ተርታ መድቦ የቴክኖሎጂ ቋንቋ አድርጎታል።

አማርኛን ከትግራይ ብትፍቀው በ2008 ዓ.ም. የጎግል የቴክኖሎጂ ማዕከል የመተርጎሚያ ቋንቋ አድርጎታል።

እንዲያው አዲስ የጫጉላ ሽርሽር ሆናባችሁ እንጂ አማርኛ በUS አሜሪካ የመንግስት ቋንቋም ነው። በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ዳሽ የሚባለው የከተማ አውቶቢስ ላይ "እንኳን ወደ #WESTEND በደህና መጣችሁ!" የሚል ጽሁፍ ማየትም የተለመደ ነው።

Dstv'ም የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ የኦሊምፒክ ውድድሮችን ጨምሮ የእንግሊዝ ኘሪሚየር ሊግ ፣ የስፔን ላሊጋ ፣ የጣሊያን ሴ ሪ ኤ እንዲሁም ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ እንዲተላለፉ ከወሰነ አመት አስቆጥሯል።

ከጀርመን ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ሀምቡርግ ዩንበርሲቲ የአማርኛ ት/ ት ማስተማር ከጀመረ መቶ ዓመት አልፎታል።

ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ እያስተማረች ነው። ትምህርቱ እየተሰጠ ያለው በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ነው።

በቅርቡ ደግሞ የፑቲን ሀገር ሩሲያ የአማርኛን ቋንቋ በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ልትጀምር መሆኗን ይፋ እንዳደረገች የምናስታውሰው ነው።

እነዚህ የግንጠላ አራማጅ ዘውጌዎች ተፈራረሙ አልተፈራረሙ የሚመጣ ለውጥ የለም። ከትግራይ ሥርዓተ ትምህርት ተወገደ አልተወገደ የሚጎዳቸው እራሳቸውን እንጂ ማንንም አይጎዱም። አማርኛ እንደሆነ እንደ ሰሜን አሜሪካ የመሣሠሉ ታላላቅ ሀገሮች ውስጥ በኦፊሻል ቋንቋነት መንግሥታት እየተቀበሉት የመጣ ቋንቋ ነው።አሜሪካ ከ500 ሺህ በላይ ተናጋሪ ላለው ለተጨማሪ የሥራ ቋንቋነት በማጨት ከ10 ዓመት በፊት ነበር አማርኛ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ያደረገችው።

እነዚህ ስብስቦች ግን ከኢትዮጵያ ለመሸሽ የግእዝ/አማርኛን ፊደል በመጤ የላቲን ፊደል የተኩ የማ*ህ*ይ*ም መጨረሻዎች ናቸው። የኦሮምኛ ቋንቋ አህጉር ተሻግሮ በመጣ የላቲን ፊደል እንዲተካ የተደረገው በ1984 ዓ.ም. ነው። ይህን ያደረጉት የግዕዝ/አማርኛ ፊደል የዐማራ ብቻ ስለመሰላቸውና በዐማራ፣ በአማርኛና በግዕዝም ላይ በነበራቸው ጥላቻ የተነሣ ነው።

ዛሬ በአለም ላይ የራሳቸው የሆነ የጽህፈት ስርዓት ወይም ፊደላት አላቸው ከሚባሉት ቻይና፣ ሕንድ፣ ፋርስ፣ ግሪክ፣ ሮም፣ እስራኤል፣ ባቢሎን እና ግብፅ መካከል ኢትዮጵያ አንዷ የሆነችው ግእዝ ከሚናገሩ አግዓዝያን እና አማርኛ ከሚናገሩ ዐማራዎች የተገኘ ነው። የግዕዝ ፊደል የሚባሉት 24ቱ' ፥ሀ፥ ለ፥ ሐ፥ መ፥ ሠ፥ ረ፥ ሰ፥ ቀ፥ በ፥ ተ፥ ኀ፥ ነ፥ አ፥ ከ፥ ወ፥ ዐ፥ ዘ፥ የ፥ ደ፥ ገ፥ ጠ፥ ጸ፥ ፀ፥ ፈ፥ ናቸው። እነዚህ የግዕዝ ፊደል ኆኅያት ለአማርኛ ቋንቋ በቂ ሆኖ ስላልተገኘ የዐማራ የትምህርቱ ኀላፊዎች ከግእዝ ፊደል ተጨማሪ ምልክትና ተጨማሪ ኆኄያትን መፍጠር ስላስፈለጋቸው፣ የኆኄዎች ምንጮች የቶቹ የግዕዝ ኆኄዎች እንደሆኑ አጥንተው ፦
ግዕዝ አማርኛ
ከ “ደ” “ጀ”ን
ከ“ጠ” “ጨ”ን
ከ“ሰ” "ሸ”ን
ከ"ነ" ”ኘ”ን
ከ “ተ” “ቸ” ን
ከ"ከ" "ኸ"ን
ከ"ዘ" "ዠ"ን አስወለዱ።

እነዚህ ሰባት ግንደ ፊደላት ከእንዚሮቻቸው ጋር ሲደመሩ 49 ይሆናሉ። የኢትዮጵያ የፊደላት ቁጥር ከግዕዝ ኆኄዎች 24'ቱ ከግሪኮች ኆኄዎች 2'ቱ ፊደላት ከአማርኛ ኆኄዎች 7' ቱ ፊደላት ተደምረው ወደ 33 ኆኄዎች ሊያድግ ችሏል።

ኢትዮጵያ በነዚህ ፊደላት አማካኝነት ልጆቿን አስተምራለች፣ ለወግ ለማዕረግ አብቅታለች፣ ታሪኳንና ማንነቷን ፅፋበታለች፣ ነገሥታቶቿ እና ደራሲዎቿ አያሌ ጉዳዮችን ፅፈውባቸዋል። የኢትዮጵያ የማንነት ሐውልት የተገነባውና የቆመው በእነዚህ ፊደላት ነው። እንደ አኩስም፣ እንደ ላሊበላ፣ እንደ ጎንደር ኪነ-ሕንፃዎች አባቶቻችን ያወረሱን ድንቅዬ ቅርሶች፣ የማንነታችን መገለጫ ሀብቶች ናቸው።

ነገርግን በአልባኒያ የኮሚኒዝም ፍልስፍና የሰከሩና
የጐሣ ዕፀ ፋርስ ያሳበዳቸው እንደ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ያሉ ቡድኖች የግእዝ/አማርኛ ፊደል አንፈልግም ብለው ባህር ማዶ ተሻግረው የላቲንን አምጥተዋል። በግእዙ በሁለት ፊደል "ቄሮ" ብሎ ከመጻፍ በላቲን 7 ፊደል "Qeerroo" ብለን ነው የምንጽፈው አሉ ይሄው እየደረደሩት ነው።


ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
14.8K viewsTadele Tibebu, edited  17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 17:27:42
34.3K viewsTadele Tibebu, 14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 11:25:37
17.7K viewsTadele Tibebu, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 11:25:36
17.7K viewsTadele Tibebu, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 11:25:18 የድንጋዩ ግዝፈት፣ የመቃብሩ ጥልቀትና የመቃብር ዘበኞች የክርስቶስን ትንሳዔ እንዳላስቀሩት ሁሉ፤ የዐማራን ትንሣኤ እንደ ዔሳው ብርኩናቸውን የሸጡ የይሁዳ ፍየሎች (The Judas goat) ሆኑ፣ የሀገሪቱ ፊልድ ማርሻሎች አያስቀሩትም። እስራኤላውያን ከፈርዖን ባርነት ነፃ ለመውጣት የፈጀውን ያህል ግዜ ይወስድ እንደሆነ እንጂ
እንደ ኡጋንዳው ኢዲ አሚን ዳዳ ያሉ አምባገነኖች የዐማራ ትንሣኤን አያስቀሩትም። እንደ ፕሮፌሰር አሥራት ያሉ ተቆርቋሪ ዐማሮችን ልክ እንደ "ቀያፋ" እንዲያዙ ምክር የሚሰጡ ተላላኪዎች ትንሳኤውን አያስቀሩትም። በኢየሩሳሌም ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ እየሱስን ለማስያዝና ፍርድ እንዲፈረድበት፣ "ሕዝብ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል" ብሎ የመከረ ሰው ነው። ምክሩ ግን የክርስቶስን ትንሳኤ አላስቀረውም።

በአንጻሩ፣ ዛሬ ትንሳኤ ላይ ያሉ የሚመስላቸው መጨረሻቸው እንደ አሚን ዳዳ ስደተኛና ፍርደኛ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለም። "ያለምንም ደም፤ ያለምንም ደም" (With out blood, without blood) በሚል መፎክር የተጀመረው የደርግ አብዮት ኢትዮጵያውያንን በመረፍረፍ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የሞት ጠረን ሸተተኝ ብሎ ፈርጥጦ ዝምባዋብዌ ገብቷል። የደርግን ሥርዓት በቀይ ሽብር በመደዳ ጭፍጨፋ ገድሎ የሸጠው ሬሳ የብረት ዓምድ ሆኖ አላስቆመውም። የዘረፈው ንብረት መሰላል ሆኖ አላቆየውም። ይልቁንስ እንደ በግ እየነዳ ያረደው የደም ጎርፍ ጠራርጎ ወሰደው። በነ ማርክስ ቴዎሪ የረገጠው ሃይማኖት እንጦሮጦስ አወረደው።

ዛሬ ትንሣኤ ላይ ያሉ የሚመስላቸው አምባገነኖች
የዐማራን ህዝብ እንደ ሂትለር፣ ሙሶሎኒ፣ ስታሊን፣ ፓል ፖት እያሰቃዩ፣ እየጨፈጨፉና እያፈናቀሉ መሠረትነው የሚሉት ርዕዮተዓለም እንደ ናዚ ፓርቲ መንኮታኮቱ አይቀርም። ወለጋ ውስጥ አንዲት የ6 ዓመት ህፃን "ወላሂ ሁለተኛ ዐማራ አልሆነም" እያለች በጉንጮቿ ያፈሰሰችው ዕንባ፣ እየተሳለቁ!..ለማየት በሚያሣሣ ገላዋ ላይ እሽቅድምድም በሚመስል መልኩ ባዘነቡት የጥይት አረር ያፈሰሱት ደሟ የእንጦሮጦስን ጎዳና መጥረጉ አይቀርም።

ይህ ታሪክ ከሩዋንዳዋ ህፃን ጋር የሚመሳሰል ነው። ሩዋንዳ ውስጥ በነበረው ፍጅት ወቅት አንዲት የ7 ዓመት ህፃን በሁቱ ገዳዮች ተከባ "እባካችሁ አትግደሉኝ። ከእንግዲህ ቱትሲ አልሆነም" (Please don't kill me, I will never be a Tutsi again) እያለች መማፀኗን ተከትሎ የዓለምን ልብ ሰብረው ነበር። ይህ የሁቱዎች ጭካኔ የተቱሲዎችን ትንሣኤ አላስቀረውም። ቱትሲዎች ሥልጣን ይዘው በደም የታጠበችውን ሩዋንዳን ውብና ፅዱ፣ የቱሪስቶች መዳረሻ፣ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ አደረጓት። ከትንሣኤው በኋላ የሩዋንዳ ህፃናቶች በውቧ ኪጋሊ ከተማ መናፈሻዎች ሲቦርቁ ታዩ።

ዛሬም በአዳነች አበቤ የከንቲባነት ዘመን በአዲስአበባ ከተማ ቤታቸው ፈርሶ መጠጊያ አጥተው የሚንከራተቱ፣ በፈረስ ጋሪ ከቤት እቃ ጋር ተጭነው የሚሰደዱ ህፃናቶች ዕንባ በዮዲት ጉዲት የወረደውን አይነት መቅሰፍት ማምጣቱ አይቀርም። ግፈኞች ወደ ከርሠ መቃብርና ወህኒ ሲወርዱ፣ የአዲስአበባ ህፃናቶች፣ የወለጋ ህፃናቶች፣ ተፈናቀለው በመጠለያ ካምፕ የሚገኙ ህፃናቶች የሩዋንዳን አይነት የትንሣኤ ዘመን ይመጣላቸዋል።

የግፈኞች መጨረሻ ግን እንደ መንጌ መፈርጠጥ፤ እንደ ዣን ፖል እስርቤት መሆኑ አይቀርም። የሩዋንዳዋ ታባ ከተማ ከንቲባ የነበረው "ዣን ፖል አካይሱ" በፈፀመው የዘር ጭፍጨፋና ሰብዓዊ መብት ጥሰት ከፍርድ እንዳላመለጠው ሁሉ፣ አዲስአበባ ላይ እንደ ዣን ፖል ግፍ እየፈጸሙ ያሉ ሰዎች ዕጣ ፈንታ እንደ ዣን ፖል ይሆናል። በወቅቱ ባንኩና ታንኩ በእጃችን ነው ብለው በጥጋባቸው ቦሲኒያን የጨፈጨፉት ጄነራል ራዲስላቭ ክርስቲች እና ኮማንደር ራትኮ ምላዲች ከፍርድ አላመለጡም። ስለዚህ ግፈኞች ሲዋረዱ እንጂ ትንሳኤን አስቀርተው አያውቁም። ናዚዎች በኑምበርግ ፍርድቤት ቀርበው የዕድሜ ልክና የስቅላት ቅጣታቸውን አገኙ እንጂ፣ የእስራኤላውያንን ትንሳኤ አላስቀሩትም። ሁቱዎች በወረንጦ እየተለቀሙ ፍርዳቸውን አገኙ እንጂ የቱትሲዎችን ትንሣኤ አላስቀሩትም። ኢትዮጵያ ላይ ይህ ዘመን አይርቅም።

ከስቅለት በኋሏ ትንሳኤ፤ ከጨለማ በኋላም ብርሀን አለና!
17.6K viewsTadele Tibebu, edited  08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ