Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በዳንሻ፣ በወፍ አርግፍና በሌሎች አካባቢዎች ደማቅ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በዳንሻ፣ በወፍ አርግፍና በሌሎች አካባቢዎች ደማቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።ይህ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ በአደባባይ ያሰማው ድምፅ፦

☞ ወልቃይት ጠገዴ የከለው ልጅ የአማራ ዘር ግንድ መነሻ ነው!

☞ለእንግዶች እንጂ ለወንጀለኞች ቦታ የለንም!

☞ለነፃነታችን ዋጋ ከፍለንበታል፣ ወደኋላ ላንመለስ ነፃ ወጥተናል!

☞አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም!

☞የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍፁም ፍትሐዊና ህጋዊ ነው።

☞የማይገባንን አልፈን አንጠይቅም፣ የራሳችንንም አሳልፈን አንሰጥም!

☞የወልቃይት ጠገዴ እና የራያ አማራ የማንነት ጥያቄን "የርስት ማስመለስ ብሎ በመፈረጅ አማራን ማሸማቀቅ አይቻልም ! ሀገር ርስት ነው! ለርስት መሞት ክብር ነው!"

☞ የፖለቲካ ሴራ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ለድጋሜ እልቂት እንጂ ሰላምን አያመጣም የሚሻለው መራራውን ሀቅ መቀበል ብቻ ነው!


☞በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ላይ ለተፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፍትህ ካሳ እንፈልጋለን!

☞ተበዳይ እንጂ በዳይ፤ ተጨፍጫፊ እንጂ
ጨፍጫፊ፣ ተወራሪ እንጂ ወራሪ፤ ተፈናቃይ እንጂ አፈናቃይ አይደለነም!

☞ የትግራይ ህዝብ ሆይ መጣችሁብን እንጅ አልመጣንባችሁም የመጭው ዘመን የሰላም ሁኔታ በእጃችሁ ነው፣ ከተከዜ በመለስ አማራ የመሆኑን ሀቅ ተቀበሉና ጥሩ ጎረቤት እንሁን!

☞ በዳይ የተበዳይን ጩሆት ነጥቆ ተበዳይ ለመምሰል የሚደረግ አካሄድ ዓይነ ደረቅነት ነው!

☞ ወንጀለኞች ለህግ ይቀርባሉ እንጅ በተፈናቃይ መልክ እናስፍር አይባልም!

☞ አማራዊ ማንነታችን እና የወሰን አስተዳደር ግዛት በህግ አግባብ ይከበር!

☞ ከትግራይ ጋር ደንበራችን ተከዜ ነው።