Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! ብልፅግና ሆቴል ውስጥ አስቀምጦ እንደ ሰንጋ በሬ የሚቀልባቸው አክቲቪስቶች ይህን ዘግ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! ብልፅግና ሆቴል ውስጥ አስቀምጦ እንደ ሰንጋ በሬ የሚቀልባቸው አክቲቪስቶች ይህን ዘግናኝ አገዳደል (horrifying killing) ከማውገዝ ይልቅ ለማስተባበል የሄዱበት እርቀት ያስገርማል። እነዚህ አእምሯቸው የታጠበ አክቲቪስት ተብየዎች ሰብአዊነት ከማስቀደም ይልቅ የመሪያቸውን ገመና ለመሸፈን ሲጋጋጡ ማዬት ያሳዝናል።አንድ እውነት ግን መታወቅ ይኖርበታል እንዲህ ያለ ግድያ እየተፈፀመ ያለው በኦህዴድ ብልፅግና ዘመነ መንግሥት፣ በአብይ አሕመድ የሥልጣን ዘመን እና በብርሃኑ ጁላ ፊልድ ማርሻል ዘመን ነው። ታሪክም መዝግቦ የሚያስቀምጠው በዚህ መልኩ ነው። ሁለት ኦርቶዶክሳዊን ወጣቶችን በገመድ ለኋሊት የፍጥኝ በማሰር አነጣጥረው ተኩሰው የገደሏቸው የመከላከያ ዩኒፎርም የለበሱ ናቸው። እንዴት እንደገደሏቸውም ቪዲዮ ቀርፀዋል። ቪድዮውን ሚቀርፃቸው ሌላ ሶስተኛ ወገን ሳይሆን ደግሞ እራሳቸው ገዳዮቹ ናቸው። ከቪድዮ ቀራጩ ውጭ በቁጥር አራት ሲሆኑ፣ ሁሉንም የመከላከያ ዩኒፎርም ልብስ የለበሱ ናቸው።

አብይ አሕመድ ወደሥልጣን ከመጣ ጀምሮ እንደዚህ ያሉ ግድያዎች ተራ ጉዳይ ሆነዋል። ባጠቃላይ ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2015 በዐማራ ከተፈጸሙ ግድያዎች መካከል እነዚህ ይገኙበታል፣

1. ወደ ገደል መጣል
2. ጡት መቁረጥ
3.ብልትና ምላስ መቁረጥ
4.ሥጋቸውንም ቆርጦ ማብላት
5.በድንጋይ መቀጥቀጥ
6. በሜንጫ እና በስለት ማረድ
7. በቀስት መውጋት
8. ፅንስ ማቋረጥ
9. በጅምላ መረሸን
10.በእሳት ማቃጠል...ወዘተ ይገኙበታል።

እነዚህን በጥቂት ምሳሌዎች ላስረዳ!

ሀ. #ወደገደል_መጣል፦ የዐማራ ተወላጆች ከተገደሉባቸው ገደሎች መካከል በወልቃይት ገነሃም ግንብ እና እመን አላምንም፣ በኦሮሞ ክልል እንቁፍቱ ገደል፣ ሞሶ ጊዎርጊስ ገደል፣ ጥርሶ ገደል፣ ኩርባ ጀርቲ ገደል ይገኙበታል። የአገዳደሉ ስልት የኋሊት በማሰር፣ ዐይናቸው ሸፍኖ ወደገደሉ ጫፍ ከአስጠጓቸው በኋላ በጥይት በማርከፍከፍ እንዲወድቁ ማድረግ አንደኛው ነው። ሁለተኛው አገዳደል እጅና እግራቸውን በማሰር ፊታቸውን በመሸፈን ከነሕይወታቸው ወደጥልቁ ገደል መጣል ሲሆን፣ ሦስተኛው አንገታቸውን በሰይፍና በሜንጫ ቀልቶ መወርወር ናቸው።

ሕወሓት ከደጀና ከተማ በስተሰሜን ምስራቅ በኩል ወደሚገኘው "እመን አላምንም" እየተባለ ከሚጠራው ወደ 200 ሜትር ከሚረዝመው የገደል አፋፍ ላይ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራዎችን በመወርወር ይገድላቸው ነበር። በተመሳሳይ የዐማራው ልኳንዳ አራጅ ኦነግ ደግሞ በደኖ መግቢያ ላይ ከሚገኘው የእንቁፍቱ ገደል ዐማሮችን እጃቸው በገመድ እያሰረ ዐይናቸው በሻሽ እየሸፈነ ይጥላቸው ነበር። ለምሳሌ፣ አፈሩን ገለባ ያድርግላቸውና አቶ አበበ ምትኬ በሐረርጌ የበደኖ ከተማ ኗሪ ነበሩ፡፡ በ1984 ዓ.ም. በበደኖ ዕልቂት ሙሉ ዘጠኝ ቤተሰቦቻቸውን ከነነፍሳቸው አስረው እንቁፍቱ ገደል በመወርወር ጨረሷቸው። (ምጽአተ ዐማራ፣ 327)

ለ.#ጡት_መቁረጥ፦ በጃዋር ምክንያት ዶዶላ ላይ የሁለት ህፃናት እናት የነበረችው ዘምሼ ሲሳይ የገደሏት ጡቷን ቆርጠው ነው። ኦነግ በ1984 ዓ.ም. ብቻ በሐረርጌ ክፍለሀገር፣ ደጉ መድኃኔዓለም 3፣ ከሀረር ከተማ በ7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ፈዲስ 7፣ ከበደኖ አለፍ ብላ ከምትገኘው ቡርቃ 4 ባጠቃላይ 14 የዐማራ ሴቶችን ጡት ቆርጧል። (ምጽአተ ዐማራ፣ 329)

ሐ.#ብልትና_ምላስ_መቁረጥ፦ በምሥራቅ ወለጋ ህዳር 21 ቀን 1993 ዓ.ም. በጊዳ ኪራሞ ወረዳ፣ ዲቡክ ማርያም 1100 የሚሆኑ የብሉይ ዘመን ሕይወትን የሚገፉ ሚስኪን ዐማሮችን ሕፃናት፣ አዛውንቶችና ሴቶች አልቀዋል። በወቅቱ ጦቢያ መጽሔት "የዐማራው ሕዝብ ዕልቂት በአንድ ዘር ላይ የተነጣጠረ ጥቃት" በሚል ይዞት በወጣው ልዩ ጥንቅር ከዕልቂቱ አስከፊ ገጽታ መካከል የሚከተለውን በዝርዝር ይገልጻል፣

"አባ በላይ ዋለ የተባሉትን ዓይነ ሥውር ገደሏቸው። 'ዐማራ ዐማራ ነው' ብለው ብልታቸውን ቆረጡት። መልካሙ ውባለምን አርደው ገደሉትና ምላሱን አውጥተው ወሰዱት።
(ጦቢያ መጽሔት፣ ቅጽ 8፣ ቁጥር 8፣ 1993)

መ.#ሥጋቸውንም_ቆርጦ_ማብላት፦ በዐማራ ላይ ከተፈፀሙ የግድያ አይነቶች ሌላኛው ልብሳቸውን እያስወለቁ ሥጋቸውን እያበሉ መግደል ነው። ለምሳሌ፣ ገቦ ሀብሩ ወረዳ አቶ ፀደቀ አውሉው የሚባል የዐማራ ተወላጅን መጀመሪያ ወርቅ ጥርሱን አውልቀው ወሰዱ። ቀጥሎ ሰውነቱን እንደ ጥሬ ሥጋ በመቆራረጥ እያበሉ ገደሉት። በገለምሶ በልበልቲ ይኖር የነበረው አቶ ገብሬ አወቀ የሚባል ሕዝብ በተሰበሰበት በሚስማር እንደ ክርስቶስ እጅና እግሩን ቸንክረው በመጀመሪያ ብልቱን ከዚያም የተለያየ የአካል ክፍሉን እየቆራረጡ እያበሉ ገድለውታል።

ሠ. #ፅንስ_ማቋረጥ፦ "የዐማራ ልጅ አይወለደም" እያሉ ፅንስን መግደል በዐማራ ከተፈፀሙ ዘግናኝ ግድያዎች መካከል አንዱ ነው። በሃጫሉ ሞት ምክንያት በተነሳ አመፅ ሻሸመኔ ከተማ የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡር መሬት ላይ ጥለው፣ ልብሷን አስወልቀው፣ እግሯን ይዘው እየጎተቱ "የዐማራ ልጅ አይወለድም፤ የክርስቲያን ልጅ አይወለድም፤ ግደላት ሰንጥቅና አሳየኝ " እያሉ ሜጫቸውን፣ ጩቤያቸውንና መጥረቢያቸውን ወደ አንገቷ እና ሆዷ አስጠግተው እየሳሉ አሰቃይተው ከነፅንሷ እስከወዲያኛው ህይወቷ እንዲያልፍ ሆኗል። ሕወሓትም በጦርነቱ ወቅት "የዐማራ ልጅ ተወልዶ አድጎ ይወጋናል" በሚል ከእናቱ ሆድ እያለን ፅንስ በርግጫ እና በሰደፍ እየጨፈለቀ አጨናግፏል።

ሰ. #በእሳት_ማቃጠል፦ ሰኔ 11ቀን 2014 ዓ.ም በምዕራብ ወለጋ ግምቢ በምትገኘው ቶሌ ቀበሌ ከ600 በላይ የሚሆኑ ዐማሮችን ተጨፍጭፈዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ዐማሮች በብዛት በሚኖሩበት የቶሌ መንደሮች ጉቱ፣ ጨቆርሳ፣ ስልሳው፣ በገኔ፣ ጫካ ሰፈር እና ሀያው ሲሆን፣ ከተፈጸሙ ዘግናኝ አገዳደሎች መካከል በእሳት ማቃጠል ይገኝበታል። ከላይ በተጠቀሱት መንደሮች ወደ 22 የሚሆኑ ዐማሮች በር ተዘግቶባቸው ከነሕይወታቸው ቤታቸው ውስጥ ተቃጥለዋል።

ባጠቃላይ ከኢትዮጵያዊያን ባሕል፤ ሃይማኖት፤ ሞራል እና ሰብአዊነት ተግባር ባፈነገጠ መልኩ በዐማራ ላይ ያልተፈፀመ የግድያ አይነት የለም። እነዚህ አውሬዎች በዐማራ ላይ እንዲህ ያለውን ዘግናኝ ድርጊት ሲፈፅሙ በደስታ ነው። የዐማራ ሴቶችን ጡት ጥሬ ስጋ እንደሚበላ ሆዳም ሰው ተስገብግበው ሲቆርጡት በኩራት ነው። አይሁዶች በክርስቶስ በየተራ እንደተዘባበቱበት ሁሉ እንደ በግ ጠቦት ለመግደል ባዘጋጁት ዐማራ ላይ ሲዘባበቱ በሲቃ ነው። ምክንያቱም ይህን እያደረጉ ያሉት በዐማራው ላይ ስለሆነ!