Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! ይህ ዛሬ ጎጃም ጅጋ ከተማ የሆነ ነው። እንዳጋጣሚ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ 'ከልዩ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! ይህ ዛሬ ጎጃም ጅጋ ከተማ የሆነ ነው። እንዳጋጣሚ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ "ከልዩ ኃይሉ ጎን ነን" እያለ ነበር። እነዚህ ልዩ ኃይሎች ደግሞ እንዳጋጣሚ ጅጋ ከተማ ደረሱ። በዚህ ቅፅበት ህዝቡ ዙሪያቸውን ከቦ እየጨፈረ ጀግንነታቸውን በህብረት አስተጋባ። "እህል ውሃ ሳትቀምሱ ከጅጋ ከተማ አትወጡም" ተብለው ምሳ ተጋብዘው፣ ከህዝቡ ጋር ተወያይተው በክብር ተሸኝተዋል። የህዝብ ልጅ ስትሆን እንደዚህ ትከበራለህ። ህዝብ ቀድሞ ይሞትልሃል። ያለውን ይሰጥሃል። ከምንም በላይ ለአንድ ሠራዊት የሞራል ድጋፍ፣ የህዝብ አክብሮትና ፍቅር ከታጠቀው መሳሪያ በላይ ነው። ለልዩ ኃይሎቻችን የማያቋርጥ ድጋፍ በተናበበ መልኩ መቀጠል ይኖርበታል።