Get Mystery Box with random crypto!

በጎንደር ከተማ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። በሰልፉ የሚከተሉት መልዕክቶች በደማቁ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

በጎንደር ከተማ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። በሰልፉ የሚከተሉት መልዕክቶች በደማቁ ተላልፈዋል!

1.አንቀፅ 39 ሳይፈርስ ልዩ ሀይላችን አይፈርስም

2. በዓለም አቀፍ መድረክ ፊት የተደረገ የሰላም
ስምምነት በጓዳ አይቀየርም!

3. የፕሪቶሪያውን ስምምነት በጓዳ ውል መቀየር ውጤቱ ሃገራዊ ውድቀት ማስከተል ነው!

4. በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት አሸባሪው ትህነግ ትጥቅ ይፍታ!

5. ጠላት ወያኔ ለዘር ማጥፋት እየተዘጋጀ ባለበት ሁኔታ ልዩ ሃላችንን ትጥቅ ማስፈታት መንግስታዊ ክህደት ነው!

6. ለኢትዮጵያ ህልውና ዋጋ የከፈሉ ሁሉ ስለ ሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም የማወቅ መብት አላቸው!

7. ዛሬም እንደትናንቱ የምንመካው በእውነት ፣ በፍትሐዊነት እና በህዝባችን አቅም ነው!

8. በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ እየተፈጸመ ያለው ዘር-ተኮር ጥቃት ግቡ ሃገር ማፍረስ ነው! አዲስ አበባ የኢትዮጵያ አንድነት የስበት ማዕከል ናት!

9. የወልቃይት እና የራያ አማራ ማንነት ጥያቄን “የርስት ማስመለስ” ብሎ በመፈረጅ አማራን ማሸማቀቅ አያቻልም!

10. የወልቃይት-ጠገዴ-ጠለምት የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍጹም ፍትሐዊ እና ሕጋዊ ነው!

11. መንግስት የግጭት ፕሮጀክቶችን አቁሞ የልማት ፕሮጀክቶችን ይጀምር!

12. መላ ኢትዮጵያውያንን ያጎሳቆለው ፖሊሲ አመጣሽ የኑሮ ውድነት መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል፡፡

13. የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ወያኔ የተከለው መዋቅር እና ህገ-መንግስት ነው!

14. ህዝብ ያላመነበትንና ለምክር ቤት ያልቀረበን ውሳኔ አንቀበልም

15. መከላከያ ወደ ልዩ ሀይላችን ከመተኮስህ በፊት ጥቅምት 24ን አስታውስ ።

16. የሶማሌ ህዝብና አስዳዳሪው ሙስጦፌ ስለ ኢትዮጵያ እየከፈላችሁት ላለው ዋጋ ክብር ይገባችኋል ።