Get Mystery Box with random crypto!

”ዐማራን አከርካሪውን ሰብረነዋል” ያለው አቦይ ስብሃት ለህክምና አሜሪካ ሲገባ፣ ብርጋዴር ጀነራል | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

”ዐማራን አከርካሪውን ሰብረነዋል” ያለው አቦይ ስብሃት ለህክምና አሜሪካ ሲገባ፣ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በአብይ አሕመድ አገዛዝ ተከልክሎ አልጋ ላይ ተኝቶ እየተሰቃዬ ይገኛል።

የሰሜን ዕዝ በተኛበት ያረዱ ሂትለራዊያን ህክምና እንዲያገኙ ፈቅደው፣ የ1ዐ8'ኛ ኮር ምክትል ኣዛዥ፣ የሰሜን ዕዝ ኦፕሬሽናል ምክትል አዛዥ፣ በመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ የእቅድ ዝግጅት መምሪያ ሃላፊ ሆኖ ሀገሩን ያገለገለን ጀግና ህክምና መከልከል "አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ" የሚያስብል ነው።

በርግጥ ኢትዮጵያ እንዲህ ናት። በ1933 ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በጎጃም የነፃነት ጥርጊያ መንገድ ከስደት ከተመለሱ በኋላ ለሆዳቸው ያደሩ፣ ኢትዮጵያን ከጥሊያን ጋር ተባብረው ከጀርባ የወጓትን ባንዳና ስደተኞችን ሲሾሙና ሲሸልሙ በአንጻሩ የዐማራ አርበኞች የድካማቸው ዋጋ የሆነው ስቅላት፣ እሥራትና ግዞት ነበር።

የጥቁ አንበሣን እና የራስ እምሩ ኃይለሥላሴን የሽምቅ ተዋጊ አርበኛ ከፋ ውስጥ አስከብቦ ከፊሉን አስገድሎ መሪዎቹን ያሲያዘው ፍቅረ ማርያም ገብረእግዚአብሔር የወለጋ ገዥ ሲሆን፣ ፀረ-ፋሽት አርበኛ በላይ ዘለቀ እና ወንድሙ እጅጉ ዘለቀ በስቅላት ተገድለዋል። ባንዳው ራስ ሥዩም መንገሻ የትግራይ ገዥ ሆኖ የአገሪቱ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ ሲሆን፣ ፊታውራሪ ኃይሉ ደጀኔ በሞት እንዲቀጣ ተደርጓል። ስደተኞችና ባንዶች በየቢሮው ተሰግስገው እጅና ጓንት በመሆን ለአገራቸው የታገሉትን አገር ወዳድ አርበኞች ጉዳይ ለማስፈፀም የነሱ ደጅጠኝ ሲሆኑ፣ እነራስ አሞራው ውብነህ ተሰማ ያምጻሉ ተብለው ተፈርተው አብዛኛውን ግዜአያቸውን ያሳለፉት በግዞት ነበር። አርበኛው ደጃዝማች ነጋሽ ወርቅነህ በግዞት አዲስአበባ እንዳሉ ሞተው ቀርተዋል። በጥሊያን የሽምቅ ውጊያን (Guerrilla warfare) ለማቀናጀት በነሐሴ ወር 1929 ዓ.ም. ሸዋ ክፍለ ሀገር ግንደበረት ላይ በተካሄደው ስብሰባ የትጥቅ ትግሉ ዋና አስተባባሪ የነበሩትን ደጃዝማች ታከለ ወልደሃዋርያት በገዛ ቤታቸው በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።

እነዚህና ሌሎች ታዋቂ የዐማራ አርበኞች እየተፈሩና እየተጠረጠሩ ሥልታዊ በሆነ ዘዴ እንዲጠፉ ተደርገዋል። ሌሎቹ በዚህ አስነዋሪ ድርጊት ቅስማቸው ተሰብሮ በችግር እየተበሳጩ አልቀዋል። ይህ ድርጊት ያሳዘነው ያገሬው ህዝብ ሁኔታውን እንዲህ በማለት ቅኔ ቋጠረለት፤

"አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ"