Get Mystery Box with random crypto!

በአስቸኳይ #ሼር_ፖስት ይሁን። የአብይ አሕመድ አገዛዝ አማራ ክልል ላይ ወረራ ፈጽሟል። ዳታና ዋይ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

በአስቸኳይ #ሼር_ፖስት ይሁን። የአብይ አሕመድ አገዛዝ አማራ ክልል ላይ ወረራ ፈጽሟል። ዳታና ዋይፋይ በማጥፋት ንፁሃንን በጅምላ እየጨፈጨፈ ይገኛል። ትናንት ጎንደር ማረሚያ ቤት ብቻ ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ልክ እንደ ቀይ ሽብር ዘመን ሰዎች አውራ ጎዳና ላይ ተግድለው እየተጣሉ ናቸው። በጥቅሉ አማራ ክልል አፈና ተፈጽሟል። የዘር ማጥፋት እና የጦር ወንጀል እየተፈጸመ ነው።

ኔትዎርክ ባለበት አካባቢ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊን፣ በውጭ የምትኖሩ ዲያስፖራዎች፣ በመላው ዓለም የምትገኙ የአማራ ማህበራት፣ የሲቪክ ተቋማት፣ የአማራ ህዝብ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ በሙሉ ለሰብአዊ መብት ተቋማት፣ ለዲፕሎማቲኩ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሚዲያዎች በማሳወቅና ጫና በማድረግ እንድታግዙ ጥሪ ቀርቦላችኋል። መሬት ላይ ያለው ወታደራዊ ጀብዱ በፖለቲካ ክንፍ መታገዝ ስለሚኖርበት በጋራ ተሰባስባችሁ የምትመክሩበት ጊዜው አሁን ነው። አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቶ በውጭው አለም የጋራ ደጋፊ ኃይል መቋቋም ይኖርበታል።

በአሁኑ ሰዓት የጎጃም፣ የጎንደር፣ የወሎና የሸዋ ፋኖ ታላቅ ተጋድሎ እየፈፀመ ይገኛል። እንደ አርመኖች ያለፍትህ ላለመቅረት፣ እንደ ኩርዶች ተበትኖ ላለመኖር የመጨረሻውን መሰዋእትነት እየከፈለ ነው። ከኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ ነፃ ያወጣቸውን አካባቢዎችም የአማራ ፋኖ የራሱን ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ ፀጥታ እያስከበረ ይገኛል። የግለሰብም ይሁን የህዝብ መገልገያ ተቋሞች ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው። እስካሁን የመርፌ ስባሪ ታህል ንብረት አልተዘረፈም። ይህ ጥብቅ ስነ-ምግባር ለትግሉ ወደፊት መገስገሻ ፓወር ነው። ፋኖነት ሕዝባዊነት ማለት በተግባርም ይሄው ነው። ስለሆነም ሁሉም በሚችለው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግና የመከራችንን ግዜ ለማሳጠር መረባረብ ይኖርበታል!

ድል ለዐማራ ሕዝብ
ድል ለኢትዮጵያ!

@እንደዚህ ኔትዎርክ ከተገኘ መረጃዎችን
update ለማድረግ እሞክራለሁ!


ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut