Get Mystery Box with random crypto!

አያት፣ አባትና ልጅ። መሀከለኛው ባያብል ምትኩ ይባላሉ አያቴ ናቸው። በቀኝ በኩል አባቴ ቄስ ጥበቡ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

አያት፣ አባትና ልጅ። መሀከለኛው ባያብል ምትኩ ይባላሉ አያቴ ናቸው። በቀኝ በኩል አባቴ ቄስ ጥበቡ ባያብል ናቸው። በግራ እኔ። አባቴ የአያቴ የመጀመሪያ ልጅ ነው። እኔ ደግሞ የአባቴ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ። ፎቶውን የዛሬ ሳምንት ነበር የተነሳነው። አያቴ ትንሽ አመመኝ ብለው ህክምና ላሳያቸው ሲመጡ ነበር በስልክ ካሜራ ያስቀረሁት። በነገራችን አያቴ 85 አመት ሆኗቸዋል። እግዚአብሔር ይመስገን ይህን ያህል ግዜ ሲኖሩ ለመጀመሪያ ግዜ አመመኝ ብለው ህክምና የታዩት አንድ ግዜ ብቻ ነው። በዚህ ምርመራም ሙሉ ጤነኛ ናቸው ተብለው ወደቤታቸው ተመልሰዋል።

አያቴ እጅግ ሲበዛ ሰው ወዳድ፣ ሰው አክባሪና በሀገሩ የተከበሩ፣ አስታራቂ፣ ልጆቻቸውን በሥርዓት ያሳደጉ አባት ናቸው። ሴቷ አያቴም በሙሉ ጤንነት በህይወት አሉ።

ለአባቶቻችን እድሜና ጤና ይስጥልን

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut