Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ ዘመን እንደ ኢትዮጵያ አስፈሪና አሳፋሪ ሀገር የለም። በየቀኑ በሰው ልጅ ደም መሬቷ ይረሰርሳ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

በዚህ ዘመን እንደ ኢትዮጵያ አስፈሪና አሳፋሪ ሀገር የለም። በየቀኑ በሰው ልጅ ደም መሬቷ ይረሰርሳል፤ ማቆሚያ የሌለው የግፉአን ዕንባ በየቀኑ ይፈሳል፤ በየቀኑ ክቡር የሰው ልጅ እንደ ቅጠል ይረግፋል፤ ሀገሪቱ በነፍሰ ገዳዮች የተሞላች ነች፤ ዘረኝነት፣ ድንቁርና ኋላቀርነት ሠልጥኖባታል፤ ደህነነት አጉብጧታል፤ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰው ልጅ ከትንኝ ያነሰ ዋጋ ነው ያለው። ማንም ይገድለዋል፥ የትም ይቀበራል። ፍትህ ርትዕ የለም፣ ህግ የለም፣ ሽማግሌ የለም፣ መንግሥት የለም፣ በሀገሪቱ ሰው ጠፍቶ የጃርት መፈንጫ ከሆነች ቆዬች። እናም ኢትዮጵያ ታስፈራለች፣ በኢትዮጵያ ለመኖር ሰቀቀን ነው። በነፃነት መኖር የለም፣ በነፃነት ከጎጃም ተሳፍሮ ወለጋ ዘመድ ጠይቆ መመለስ አይቻልም፣ እንደ ጥንቱ ስንቅ አዘጋጅቶ በእግር ተጉዞ አክሱም ፅዮን ተሳልሞ መመለስ አይቻልም። በምድሯ የበቀሉ ጃርቶች አደገኛዎች ናቸው።

ቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ መምጫሽ ናፈቀኝ" ያለው ያቺዋን ቅድስት ኢትዮጵያ እንደሆነ ልብ ይለዋል!