#ሼር_ፖስት! እነ ዶክተር ደሳለኝ ፓርላማውን ጥለው መውጣታቸው የሚያስመሰግናቸው ነው ይህን ቀን ታሪክ የሚመዘግበው ስለሆነ "በዛሬው የምክርቤት ውሎ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለአፈጉባኤው ያቀረቡት ጥያቄ እና ቃለምልልሱ....እንደሚከተለው ነው! አቶ ታገሰ ጫፎ " ... በዛሬው ዕለት የተያዙ አጀንዳዎች አንደኛ የምክር ቤቱ አንደኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ ፤ 2ኛ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የ2013 በጀት ዓመት የሂሳብ፣ ፋይናንስ እና ህጋዊነት ኦዲት እና የክንዋኔ ኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ ናቸው ፤ ...የሚቀርቡ ማስተካከያዎች እና እርማቶች ካሉ " የአብን ተወካይ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን " እ... " አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " ቃለ ጉባኤ ላይ ነው ? " ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " ቃለ ጉባኤው ላይ ሳይሆን " አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " አይቻልም " ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " አጀንዳው ላይ ቀዳሚ አጀንዳ እንዲያዝልን ለመጠየቅ ነው " አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " አይቻልም ፤ ባለተያዘ አጀንዳ አንወያይም። " ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " የተከበሩ አፈጉባኤ ...አንድ ደቂቃ እድል እንዲሰጠኝ ጥያቄ ለማቅረብ " አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " ስነስርዓት ፤ ድምፅ ማሰማት አይቻልም ስነስርዓት " ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " ቀዳሚ አጀንዳ እንዲያዝልን ጥያቄ ለማቅረብ ነው " አቶ ታገሰ ጫፎ፤ " ማይክራፎኑን ይዝጉት " ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ " ቀዳሚ አጀንዳ አለን የአብን ተወካዮች እሱ እድል ይሰጠን " አቶ ታገሰ ጫፎ፤ " ማይክራፎኑን ይዝጉት፤ አጀንዳ ካለ በአማካሪ ኮሚቴ አባል ስለሆኑ በአማካሪ ኮሚቴ እንነጋገራለን " ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ " አስቸኳይ ነው ዛሬ ም/ቤቱ እንዲያይልን የምንፈልገው " አቶ ታገሰ ጫፎ፤ " ቃለ ጉባኤ ላይ ሚቀርቡ እርማቶች እና ማስተከከያዎች ካሉ .." ከዚህ በኃላ ዶ/ር ደሳለኝን ጨምሮ 4 አብን ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል። እነሱም፦ 1.ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ (የባህርዳር ተወካይ) 2.አቶ አበባው ደሳለኝ (የጅጋ/ም/ጎጃም ተወካይ) 3.አቶ ሙሉቀን አሰፋ (ሸበል በረንታ/ዕድ ውሃ ተወካይ 4.አቶ ዘመነ ኃይሉ (የጭስ ዓባይ ተወካይ) ለሀሳብ ለአስተያየት በዚህ ሊንክ @Tadeletibebut 15.4K viewsTadele Tibebu, edited 12:43