Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-08 14:25:51
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በአዲስ አፍሪካዊ መንፈስ ተነስተን አዲስ ራዕይ ሰንቀን የአፍሪካን ሀይል፣ እድል እና እምቅ አቅም ለእድገት እናውል እያለ ነው። ይህን በፃፈበት ቲዊተር የለቀቀው ፎቶ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ያሸበረቀ ነው። እኛ ወደ መንደር ስንወርድ አፍሪካውያን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አለማ እያሸበረቁበት አዲስ የተነሳሽነት መንፈስ እያደረጉት ይገኛሉ። #ሼር

የዊሊያም ሩቶ መልዕክት ከታች የተፃፈው ነው

Owing to the emerging interaction of critical factors at various levels, it is inevitable to develop and articulate a new vision of African power and prospects in terms of opportunities, resources and potential.
5.3K viewsAnt B, 11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 04:14:47 ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ የሁላችንም  መሆን አለበት  የኢትዮጲያ ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር)

የተፈናቀሉ ጎሳዎችን ወደ ቄያቸው መመለስ አለባቸው።

ኢትዮጲያን መሸከም የማይችል የትኛውም ግዛት መኖር የለበትም።

ይህ ትክክል አደለም።

''እዚህ ላይ ሁለት ችግሮች አሉ''

አንደኛው በተፈናቃይ ስም የሚነግድ አለ ፣ላለመመለስ ሁለተኛው ደግሞ ሰው ሲፈናቀል የሚሰፋ የሚመስለው አለ::

ወንድም ወንድሙን  አፈናቅሎ አይሰፋም ኢትዮጲያ የመሬት ችግር የለባትም ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ የሁላችንም ስራ መሆን አለበት

የኢትዮጲያ ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28 ኛው መደበኛ ጉባዔ ላይ  ተፈናቃዮችን በሚመለከት ከሰጡት ማብራሪያ  የተወሰደ።
5.6K viewsAnt B, 01:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 23:07:22 https://vm.tiktok.com/ZM2HmRAtQ/
5.0K viewsAnt B, 20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 03:06:32 https://vm.tiktok.com/ZM2ugVBw8/
304 viewsAnt B, 00:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 22:58:55
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ፦

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል ለመደራጀት ያካሄዱትን የህዝበ ውሳኔ ውጤት በሙሉ ድምፅ አጸድቋል።

ይህም ማለት በኢትዮጵያ 12ኛው ክልል እንዲደራጃ ይሁንታ ሰጥቷል።

በዚህም መሠረት ፦

ላለፉት 30 ዓመታት ገደማ በደቡብ ክልል ሥር ሲተዳደሩ የቆዩት ፦
የዎላይታ ፣
የጋሞ ፣
የጎፋ ፤
የኮንሶ ፣
የደቡብ ኦሞ ፣
የጌዲኦ ዞኖች እንዲሁም
የአማሮ ፣
የቡርጂ ፣
የደራሼ ፣
የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች የፌዴራል ሪፐብሊኩ 12ኛ ክልል ሆነው " ደቡብ ኢትዮጵያ " በሚል እንዲደራጁ ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በሌላ በኩል ፦
የሃድያ ፣
የከንባታ ጠንባሮ ፣
የሀላባ ፣
የሥልጤ ፣
የጉራጌ ዞኖችና እና የየም ልዩ ወረዳ ራሳቸውን መልሰው በማደራጀት #በነባሩ ክልል እንዲቀጥሉ ሲል ምክር ቤቱ ወስኗል።
740 views@A, 19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 23:25:55 ውቧና ደገኛዋ የወላይታ ሶዶ ከተማ የአዲሱ ክልል ዋና መቀመጫ እንድትሆን ምኞቴ ነው። ሶዶ በለም ቀይ አፈሯ እና አሬንጓዴነቷ ትታወቃለች። የዳሞት ተራራን ተንተርሳ በከፍታ ላይ ያለች በመሆኑ ሩቅ አማትሮ ለመመልከት ስትራቴጂካዊ ስፍራ ላይ ከትማለች እኔም ወላይታ ሶዶን እወዳታለሁ።

ቁርጥ ስጋ በዳጣ በርበሬ ከቀመሱ ከሶዶ እግሮን አያነሱም። ቆጭ ቆጯ (ጎመን በስጋ) ክሽን አይቢ በወላይታ እመቤት እመቤቶች የሚራቀቁባቸው ምርጥ ምግቦች መቼም ከሂሊና አይጠፉም። I love Wolaita, I love SODO. መልካም እድል ለጥንታዊቷ ወላይታ ሶዶ በተፈጥሮው ለሁሉም እንዴት አማካይ ቦታ ላይ እንዳለና ከሰባት በላይ አገናኝ መንገዶች ያሉት ነው።

በሆሳዕና አዲስ አበባ ፣ በሻሸመኔ አዲስ አበባ ፣ በሀዋሳ አዲስ አበባ የሚያኬዱ መንገዶች መሃል ሶዶን ረግጠው ያልፋሉ።

ወደ ደቡብ ደግሞ በቀጥታ ወደ ጂንካ፣ ወደ አርባሚጭ እና ዲላ ለየብቻ ያስኬዳሉ። ወደ ጅማ በቀጥታ ወደ ከፋ በቀጥታ ከሶዶ መንቀሳቀስ ይችላሉ። ሶዶ የደቡብ ደም ስር መገናኛ ነው የሚባለውም ለዛ ነው።

የአዲሱ ክልል መቀመጫ ይሁን ሲባልም ሌላው ምክንያት ለሁሉም የክልሉ ዞኖች አማካይ ቦታ ላይ መገኘቱን አመቺ መሆኑ ተጠቃሽ ነው። ለምሳሌ ከጎፋ ዞን ዋና ከተማ ሳውላ ሳውላ እስከ አርባምንጭ እና ሳውላ ደግሞ እስከ ሶዶ ድረስ ያለውን ብንመለከት ለጎፋው ሶዶ ይቀርበዋል። ውድድሩ በሶዶ እና በአርባምንጭ መካከል ነው ብንል እንኳን ማለቴ ነው።

ለምሳሌ በቀጥታ አዲሱ ጂንካ ሳውላ ሶዶ መንገድ ከደቡብ ኦሞ ዋና ከተማ ጂንካ እስከ ሶዶ ያለው ርቀት 203 ኪ.ሜ ብቻ ሲሆን ከጂንካ እስከ አርባምንጭ 255 ኪ.ሜ. ይርቃል። ከሳውላ እስከ ሶዶ 140 ኪ.ሜ ብቻ ሲሆን ሳውላ እስከ አርባምንጭ ያለው ርቀት ደግሞ 167 ኪ.ሜ. የራቀ ነው። የጌዲዮ ዞን ዋና ከተማ ዲላን ብንመለከት ከዲላ እስከ ሶዶ 133 ኪሎ ሜትር ብቻ የሚርቅ ሲሆን ከዲላ እስከ አርባምንጭ ድረስ በሶዶ ወይም በኮንሶ በኩል እጅግ ረጅም ርቀት ለመጓዝ ያስገድዳል። የውሃ ማጓጓዣው በጣም ውድ ነው እና ለብዙ የህዝብ ማመላለሻ የማይመች ነው።

የየብስ ትራንስፖርት እስከ ሀይቁ እና ከሀይቁ በኋላ ሲደመር በሐይቁ ውስጥ ያለው ርቀት ተደምሮ 150ኪ/ሜ አካባቢ ነው።
ስለሆነም ሶዶ ወደ ሁሉም ዋና ዋና ዞኖች ለመጓዝ በጣም ቅርብ ነው ።

ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ከአርባምንጭ ከተማ ይልቅ ወላይታ ሶዶ ይቀርባቸዋል። ከወላይታ ዞንና የሶዶ ከተማ በተጨማሪ በአዲሱ ክልላዊ መንግስት ትልቁ የህዝብ ቁጥር ያለው መሆኑም የሚታወቅ ነው።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ቀድሞ የተመሰረተ ሲሆን ከአርባምንጭ ከተማ ያለው ርቀት 110 ኪ.ሜ. ነው።

ሁሉም ዞኖች ወላይታ ሶዶን የሚመርጡት ከራሳቸው ቅርበት አንጻር አመቺና ወጪና ጊዜ ቆጣቢ በመሆኑ ነው።
2.2K viewsAnt B, edited  20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 18:16:54
የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀመረ
*
******
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማካሄድ ጀመሯል፡፡

ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የተከበሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርት ማዳመጥና ሕዝበ ውሳኔውን አስመልክቶ በቋሚ ኮሚቴው የሚቀርበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ማጽደቅ የሚሉና ሌሎች መደበኛ የመወያያ አጀንዳዎች በማጽደቅ ውይይቱን የቀጠለ ሲሆን ምክር ቤቱ ያጸደቃቸውን አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው ይጠበቃል።

ጉባኤው ለቀድሞ የፌዴሬሽን ም/ቤት አባልና የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ አባል ለነበሩትና በቅርቡ ሕይወታቸው ላለፈው የተከበሩ አቶ ግርማ የሺጥላ የሕሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡
2.6K viewsAnt B, 15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 13:04:01
ያልወለደቻቸውን ሦስት ህፃናትን ይዛ የተገኘች ግለሰብን ጉዳይ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ፖሊስ የህፃናቱን ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች እያፈላለገ ነው።

ሰኔ 22 ቀን 2015 ከቀኑ 8 ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ትልቁ አውቶቡስ ተራ አንዲት ግለሰብ ሦስት ህፃናትን ይዛ የተመለከቱ ፖሊስ ለፀጥታ ስራ ያደራጃቸው አካላት ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣሉ።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጥቆማውን መነሻ በማድረግ ባደረገው ክትትል እና ባሰባሰብው መረጃ ግለሰቧ ሦስቱን ህፃናት ከቡታጅራ ይዛቸው እንደመጣች በማረጋገጡ ፖሊስ መምሪያው ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ግለሰቧ ህፃናቱን እንዳሳደገቻቸው ብትገልፅም አጠራጣሪ ጉዳዮች በመኖሩ ፖሊስ የህፃናቱን ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች እያፈላለገ ነው፡፡ ህፃናቱ በአሁኑ ወቅት ክበበ ፀሐይ ህፃናት ማሳደጊያ የሚገኙ መሆኑን ፖሊስ አስታውቆ መረጃውን በማድረስ የዜግነታቸውን ለተወጡ የፀጥታ አጋዥ ኃይሎች መምሪያ ምስጋናውን አቅርቧል።

የህፃናቱ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ነኝ የሚል ግሰለብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማመልከት እንደሚችል እና ስለ ህፃናቱ ተጨማሪ መረጃ ያለው ማንኛውም ግለሰብ ለመምሪያው መረጃ በመስጠት እንዲተባበር የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
3.3K viewsAnt B, 10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 22:07:26
በመንገዳችን ላይ !!

የልጅቱን ስልክ ቀምቶ የሮጠው የቦሌው ሙባይል ነጣቂ እጅ ከፍንጅ ተይዞዋል::

ሌባውን ለመያዝ በተደረገው ሩጫ ታየና ጉደኞቹ ለአካባቢው ፖሊስ አባላት ላደረጋችሁት ትብብር ምስጋና ይገባችሁል:::
4.2K viewsAnt B, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 18:32:06
በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም በተመዘገቡ ንብረቶች ላይ የሃራጅ ማስታወቂያ ወጣ፡፡

በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም በተመዘገበ ንብረት ላይ የሃራጅ ማስታወቂያ ያወጣው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ነው፡፡

ባንኩ ሰኔ 13 ቀን 2015 አመት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባወጣው የሃራጅ ማስታወቂያ፣ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም የተመዘገቡ ንብረቶች በሃራጅ እንደሚሸጡ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት በዮናታን ስም የተመዘገበ ሃዋሳ ከተማ ላይ የሚገኝ 400ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ያለው ባለ ሶስት ወለል መኖሪያ ቤት አንደኛው ሲሆን፣ በ22 ሚሊዮን ብር የሃራጅ መነሻ መሸጫ ዋጋ ተቀምጦለታል፡፡

እንዲሁም በዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመዘገበ ሃዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ የሚገኝ 1ሺህ 271 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ህንጻ ሌላኛው በሃራጅ እንዲሸጥ ጫረታ የወጣበት ሲሆን 30 ሚሊዮን ብር የሃራጅ መነሻ ብር ተቀምጦለታል፡፡

ሌላኛው በሃራጅ እንዲሸጥ ጨረታ የወጣበት ደግሞ በዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመዘገበ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኝ በካርታ ቁጥር የተመዘገበ 500 ካሬ ሜትር ይዞታ ያለው መኖሪያ ቤትም ይገኝበታል፡፡
3.8K viewsAnt B, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ