Get Mystery Box with random crypto!

ውቧና ደገኛዋ የወላይታ ሶዶ ከተማ የአዲሱ ክልል ዋና መቀመጫ እንድትሆን ምኞቴ ነው። ሶዶ በለም ቀ | Skyline media

ውቧና ደገኛዋ የወላይታ ሶዶ ከተማ የአዲሱ ክልል ዋና መቀመጫ እንድትሆን ምኞቴ ነው። ሶዶ በለም ቀይ አፈሯ እና አሬንጓዴነቷ ትታወቃለች። የዳሞት ተራራን ተንተርሳ በከፍታ ላይ ያለች በመሆኑ ሩቅ አማትሮ ለመመልከት ስትራቴጂካዊ ስፍራ ላይ ከትማለች እኔም ወላይታ ሶዶን እወዳታለሁ።

ቁርጥ ስጋ በዳጣ በርበሬ ከቀመሱ ከሶዶ እግሮን አያነሱም። ቆጭ ቆጯ (ጎመን በስጋ) ክሽን አይቢ በወላይታ እመቤት እመቤቶች የሚራቀቁባቸው ምርጥ ምግቦች መቼም ከሂሊና አይጠፉም። I love Wolaita, I love SODO. መልካም እድል ለጥንታዊቷ ወላይታ ሶዶ በተፈጥሮው ለሁሉም እንዴት አማካይ ቦታ ላይ እንዳለና ከሰባት በላይ አገናኝ መንገዶች ያሉት ነው።

በሆሳዕና አዲስ አበባ ፣ በሻሸመኔ አዲስ አበባ ፣ በሀዋሳ አዲስ አበባ የሚያኬዱ መንገዶች መሃል ሶዶን ረግጠው ያልፋሉ።

ወደ ደቡብ ደግሞ በቀጥታ ወደ ጂንካ፣ ወደ አርባሚጭ እና ዲላ ለየብቻ ያስኬዳሉ። ወደ ጅማ በቀጥታ ወደ ከፋ በቀጥታ ከሶዶ መንቀሳቀስ ይችላሉ። ሶዶ የደቡብ ደም ስር መገናኛ ነው የሚባለውም ለዛ ነው።

የአዲሱ ክልል መቀመጫ ይሁን ሲባልም ሌላው ምክንያት ለሁሉም የክልሉ ዞኖች አማካይ ቦታ ላይ መገኘቱን አመቺ መሆኑ ተጠቃሽ ነው። ለምሳሌ ከጎፋ ዞን ዋና ከተማ ሳውላ ሳውላ እስከ አርባምንጭ እና ሳውላ ደግሞ እስከ ሶዶ ድረስ ያለውን ብንመለከት ለጎፋው ሶዶ ይቀርበዋል። ውድድሩ በሶዶ እና በአርባምንጭ መካከል ነው ብንል እንኳን ማለቴ ነው።

ለምሳሌ በቀጥታ አዲሱ ጂንካ ሳውላ ሶዶ መንገድ ከደቡብ ኦሞ ዋና ከተማ ጂንካ እስከ ሶዶ ያለው ርቀት 203 ኪ.ሜ ብቻ ሲሆን ከጂንካ እስከ አርባምንጭ 255 ኪ.ሜ. ይርቃል። ከሳውላ እስከ ሶዶ 140 ኪ.ሜ ብቻ ሲሆን ሳውላ እስከ አርባምንጭ ያለው ርቀት ደግሞ 167 ኪ.ሜ. የራቀ ነው። የጌዲዮ ዞን ዋና ከተማ ዲላን ብንመለከት ከዲላ እስከ ሶዶ 133 ኪሎ ሜትር ብቻ የሚርቅ ሲሆን ከዲላ እስከ አርባምንጭ ድረስ በሶዶ ወይም በኮንሶ በኩል እጅግ ረጅም ርቀት ለመጓዝ ያስገድዳል። የውሃ ማጓጓዣው በጣም ውድ ነው እና ለብዙ የህዝብ ማመላለሻ የማይመች ነው።

የየብስ ትራንስፖርት እስከ ሀይቁ እና ከሀይቁ በኋላ ሲደመር በሐይቁ ውስጥ ያለው ርቀት ተደምሮ 150ኪ/ሜ አካባቢ ነው።
ስለሆነም ሶዶ ወደ ሁሉም ዋና ዋና ዞኖች ለመጓዝ በጣም ቅርብ ነው ።

ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ከአርባምንጭ ከተማ ይልቅ ወላይታ ሶዶ ይቀርባቸዋል። ከወላይታ ዞንና የሶዶ ከተማ በተጨማሪ በአዲሱ ክልላዊ መንግስት ትልቁ የህዝብ ቁጥር ያለው መሆኑም የሚታወቅ ነው።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ቀድሞ የተመሰረተ ሲሆን ከአርባምንጭ ከተማ ያለው ርቀት 110 ኪ.ሜ. ነው።

ሁሉም ዞኖች ወላይታ ሶዶን የሚመርጡት ከራሳቸው ቅርበት አንጻር አመቺና ወጪና ጊዜ ቆጣቢ በመሆኑ ነው።