የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ፦ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል ለመደራጀት ያካሄዱትን የህዝበ ውሳኔ ውጤት በሙሉ ድምፅ አጸድቋል። ይህም ማለት በኢትዮጵያ 12ኛው ክልል እንዲደራጃ ይሁንታ ሰጥቷል። በዚህም መሠረት ፦ ላለፉት 30 ዓመታት ገደማ በደቡብ ክልል ሥር ሲተዳደሩ የቆዩት ፦ የዎላይታ ፣ የጋሞ ፣ የጎፋ ፤ የኮንሶ ፣ የደቡብ ኦሞ ፣ የጌዲኦ ዞኖች እንዲሁም የአማሮ ፣ የቡርጂ ፣ የደራሼ ፣ የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች የፌዴራል ሪፐብሊኩ 12ኛ ክልል ሆነው " ደቡብ ኢትዮጵያ " በሚል እንዲደራጁ ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በሌላ በኩል ፦ የሃድያ ፣ የከንባታ ጠንባሮ ፣ የሀላባ ፣ የሥልጤ ፣ የጉራጌ ዞኖችና እና የየም ልዩ ወረዳ ራሳቸውን መልሰው በማደራጀት #በነባሩ ክልል እንዲቀጥሉ ሲል ምክር ቤቱ ወስኗል። 740 views@A, 19:58