Get Mystery Box with random crypto!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን | Skyline media

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀመረ
*
******
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማካሄድ ጀመሯል፡፡

ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የተከበሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርት ማዳመጥና ሕዝበ ውሳኔውን አስመልክቶ በቋሚ ኮሚቴው የሚቀርበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ማጽደቅ የሚሉና ሌሎች መደበኛ የመወያያ አጀንዳዎች በማጽደቅ ውይይቱን የቀጠለ ሲሆን ምክር ቤቱ ያጸደቃቸውን አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው ይጠበቃል።

ጉባኤው ለቀድሞ የፌዴሬሽን ም/ቤት አባልና የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ አባል ለነበሩትና በቅርቡ ሕይወታቸው ላለፈው የተከበሩ አቶ ግርማ የሺጥላ የሕሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡