Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-18 09:23:02
እነዚህ ትናንት ማለዳ ከሳተላይት የተሠበሠቡ ምስሎች በሡዳን የጦር ሐይሎች እና በRSF ታጣቂዎች መካከል በመካሔድ ላይ ባለዉ ግጭት በካርቱም አለም-አቀፍ የአዉሮፕላን ማረፊያ ላይ የደረሠዉን ጉዳት የሚያሳዩ ናቸዉ። በምስሎቹ እንደሚታየዉ ቢያንስ 14 አዉሮፕላኖች ሙሉ ለሙሉ ሲወድሙ ሌሎች በርካታ አዉሮፕላኖች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። እስካሁን በግጭቱ ሕይወታቸዉን የተነጠቁ ሠዎች ብዛት ከ180 ተሻግሯል።

አፍሪካ ለመሪዎች ስልጣንና ክብር ዜጎቿንና አንጡራ ሐብቷን የምትገብርበት ዘመን ማብቂያዉ ገና ሩቅ ይመስላል!
2.4K viewsAnt B, 06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 03:42:11 ለመስማት ከላይ ያለውን ሊንክ ይጫኑት
1.3K viewsAnt B, 00:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 03:39:03 https://www.facebook.com/reel/1337444473467378?sfnsn=mo&s=F5x8gs&fs=e&mibextid=6AJuK9
1.3K viewsAnt B, 00:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 19:55:53
የሶማሌ ክልል ካቢኔ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅር እንዲገቡ የቀረበውን ሃሳብ በሙሉ ድምፅ ደገፈ።
********
ካቢኔው ዛሬ በደረገው ስብሰባ ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ ለማድረግ የተወሰነው ውሳኔ ዕቅድ በሙሉ ድምጽ ደግፎታል።

ካቢኔው የሶማሌ ክልሉ ልዩ ኃይል ኢትዮጵያ አስቸጋሪ ፈተና በገጠማት ጊዜ ሕይወታቸውን ሠውተዋል። በክልላቸው መንግስት የተሰጣቸው ግዳጆችን በጀግንነት በመወጣት የሃገራችንን ዳር ድንበር አስከብረዋል ያለ ሲሆን የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ለሀገራችው የሚችሉትን ሁሉ ያደረጉ፤ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጀግንነት የተወጡ፤ ለወደፊትም በተሻለና ይበልጥ ኢትዮጵያን ማገልገል በሚያስችላቸው ቦታዎች ላይ እንደ የፍላጎታቸው ተመድበው እንዲያገለግሉ የተወሰነው ውሳኔ የክልሉ መንግስት በመደገፍ አስፈላጊ የሆነውን ሙሉ ደጋፍ ይሰጣል ብሏል።

በዚህም መሰረ ካቢኔው ተከታዮቹን ውሳኔዎች አሳልፏል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አመራሮችና አባላት በውሳኔው ላይ እንዲወያዩበት ይደረጋል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች እንደ ምርጫችው ወደ መከላከያ፣ ወደ ፌደራል ፖሊስ ወይም ወደ ክልል ፖሊስ የተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮችን እንዲቀላቀሉ ይደረጋል።

ጉዳዩ የትጥቅ መፍታት ጉዳይ ሳይሆን የበለጠ ሥልጠናና ትጥቅ አግኝተው ሀገርን በተሻለ ወደ ሚያገለግሉባቸው መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያደርግ መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ ካቢኔ በዛሬው ውሎው በሰፊው ውይይት ካደረገበት በኃላ ውሳኔውን በሙሉ ድምጽ መደገፉ ተገልፆአል።

Source
Somali fast Info
1.6K viewsAnt B, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 21:41:33
#VRecorder
1.5K viewsAnt B, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 22:18:08
646 viewsAnt B, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 23:23:58
ግብፅ ኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃት ፈፅማብኛለች አለች
የግብፅ የስለላ ተቋም የሞት ሽረት ትግል ላይ ነው። የመጨረሻ ያለውን የግብፅን ጥቅም የማስቀደም እንቅስቃ በዝግ መክሮ ያስቀመጠውን የስምምነት ሰነድና ኢትዮዽያ አልቀበልም ካለች የሚወሰደውን የእርምጃ አይነት በነጥብ ለይቶ አስቀምጦታል።

ለህዝብ የሚሆኑትን ተርጉምን ለማቅረብ እያዘጋጀነው ነው። ጠብቁን፣ ለመንግስት የሚሆኑቱን ወደ ደህንነቱ ተቋም ገቢ ለማድረግ ተስማምተናል።

የግብፅ የደህንነት ተቋም ከፍተኛ የሆነ የሳይበር ጥቃትን ያስተናገደ ሲሆን ከቱርክና ከአዲስ አበባ ብሎም መቀመጫቸውን በተለያዮ አገራት ያደረጉ ሳይበረኞች ጥቃት እንዳደረሱበት አምኗል። በጉዳዮ ላይ ግን በኢትዮዽያ መንግስት የማይደገፍ በፍፁም በማይታመን ቡድን ነው ጥቃቱን ያደረሱብኝ ቢልም፣ ተጠያቂ የሆነው ግን የኢትዮዽያ መንግስት ያደራጃቸው አይሁዳዊያን ናቸው ብሏል።
Bravo Ethiopia
657 viewsAnt B, 20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 14:50:02 በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ የተዋቀረው ከህወሓት፣ ከትግራይ ኃይሎች፣ ከምሁራን እና ከባይቶና ፖለቲካ ፓርቲ ነው።

የካቢኔው 51 በመቶ ቦታ የተያዘው በህወሓት ሲሆን፤ ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ሁለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል አግኝቷል።

የካቢኔው አባላት ፦

ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ - ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሰላምና ጸጥታ ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ - በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታዜይሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

አቶ በየነ ምክሩ - የኢኮኖሚ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ዶ/ር ሓጎስ ጎደፋይ - የእቅድ፣ ገቢና የሀብት አስተዳደር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት - የማህበራዊ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ወ/ሮ ያለም ጸጋይ - የመሰረት ልማት ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ብ/ ጄነራል ተኽላይ አሸብር - የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ዶ/ር አልጋነሽ ተሰማ - የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ስልጠና ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

አቶ አማኑኤል አሰፋ - ቺፍ ካቢኔ ሴክሬተሪያት

ዶ/ር እያሱ አብርሃ – የእርሻ ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር ገብረህይወት ዓገባ - የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሞገስ ገብረእግዚአብሄር - የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

አቶ ታደለ መንግስቱ - የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ ምሕረት በየነ – የፋይናንስና ሀብት ማስተባበር ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር አማኑኤል ሃይለ – የጤና ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሓድሽ ተስፋ - የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ

ሌ/ጄነራል ፍስሃ ኪዳኑ ፋንታ – የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር ከላሊ አድሃና – የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሓይሽ ሱባጋዳስ - የወጣቶች ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ ገነት አረፈ – የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ

ሜ/ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ - የማህበራዊ ጉዳይ እና መልሶ ማቋቋም ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ አልማዝ ገብረጻድቅ – የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ ፈለጉሽ አሳምነው – የመሬት እና ማዕድን ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ ፍረወይኒ ገብረእግዚአብሄር – የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር አጽብሃ ገብረእግዚአብሄር - የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

በሌላ በኩል ፤ አዲሱ የጊዜያዊ አስተዳደር ከቀድሞው አስተዳደር ጋር ዛሬ መቐለ ውስጥ ርክክብ አድርጋል።

መረጃው የ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር "  እና " ትግራይ ቴሌቪዥን " ነው።
2.1K viewsAnt B, 11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 00:06:55
#በሚያዚያ_ወር

የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል !

" የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ድረስ ባለበት ይቀጥላል " - የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ ይቀጥላል።

ምንጭ፦  የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777
454 views@A, edited  21:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 19:48:05
ፓስተር ቢኒ ምን አጋጠመው??
1.5K viewsAnt B, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ