Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-01 23:43:40
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ መግባት የሚፈልጉ” ያሏቸውን ኃይሎች፤ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ እየገቡ መፈትፈት የሚፈልጉ” ያሏቸውን “ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ኃይሎች” ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቡ። “በመገዳደል፣ በመሰዳደብ እና በመናናቅ” ለማሳካት የሚፈለግ “የፖለቲካ ዓላማ” ውስጥ ይሳተፋሉ ያሏቸውን ባለሀብቶች፣ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና በሀገር ውስጥ ያሉ ወጣቶችንም “ደጋግማው እንዲያስቡ” ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህንን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባው “የሃላላ ኬላ ሪዞርት” ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 23፣ 2015 በተመረቀበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ንግግራቸው፤ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተገደሉትን የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የአቶ ግርማ የሺጥላን ጉዳይ አንስተዋል።

አብይ በዛሬው ንግግራቸው፤ የብልጽግና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን የአቶ ግርማን ግድያ “አላግባብ መሰዋት” ሲሉ ጠርተውታል። አቶ ግርማን “ገና ሮጦ ያልጠገበ ወጣት፣ ለህዝቡ ለሀገሩ ብዙ ሊያገለግል የሚችል፣ ልጆች ቤተሰቦች ያሉት” ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በሰላም ቤተሰቡን ሊጠይቅ እየነዳ የሄደ፤ ጀግና መሳይ ፈሪዎች ተደብቀው በጥይት ገደሉት” ብለዋል። ይህንን ድርጊት የፈጸሙት ሰዎች፤ የሚፈልጉትን ነገር “በሀሳብ ብልጫ” “ብዙሃንን አሳምነው መከወን እንደማይሳካላቸው ያሰቡ” መሆናቸውን ተናግረዋል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/10784/
7.3K viewsAnt B, 20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:39:10
ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

በአማራ ክልል ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በህቡዕ ተደራጅተውና ተቀናጅተው በሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።

በመሆኑም የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል እየወሰደ ባለው እርምጃ በዚህ ህቡዕ አደረጃጀት ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ የተገኙ 47 ተጠርጣሪዎችን ከበርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ ቦንቦችና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እንዲሁም ከሳተላይት መገናኛ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መረጃዎችን ከያዙ ላፕቶፖች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ አመልክቷል።

ተጠርጣሪዎቹ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን የግድያ ዒላማ በማድረግ፤ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ የክልሉን መንግሥታዊ መዋቅር በመቆጣጠር የፌደራል መንግሥትን ለመጣል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ተደራጅተው እና ተቀናጅተው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ እንደተደረሰባቸው አስታውቋል።

ግብረ-ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ፤ መንግስት የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እና ለሐሳብ ትግል ሰፊ ዕድል በመስጠቱ እንዲሁም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ባደረገው ጥረት ብዙዎች ይሄንን ዕድል መጠቀማቸውን አስታውሷል።

https://www.fanabc.com/archives/191875
1.6K viewsAnt B, 15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 23:40:30
ሰበር መረጃ የግርማ የሺጥላን ህይወት በጎዳና ላይ ያስቀረው በለጠ ጋሻው የተባለ የፅንፈኛ ሀይሉ ቡድን መሪ ነው:: ክፍል 1

ነገሩ እንዲህ ነው ለአማራ ህዝብ እልፍ ሲልም ለሀገሩ ደከመኝ ሰለቸኝ የማይለው የአማራ ብልጽግና ጽ/ቤት ሀላፊ ግርማ የሺጥላ በትውልድ ቅየው በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ አንድም ቤተሰቦቹን በሌላ በኩል ደግሞ የቀየውን ማህበረሰብ የሰላምና የልማት ጥያቄዎች ተቀብሎ ለመፍታት ሲያወያይ ቆይቶ ሀገር ሰላም ነው ብሎ ከቤተሰቦቹ፡ከስራ ባልደረቦቹና ከጠባቂዎቹ ጋር በ6 ተሸከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ መንገድ ላይ አድፍጠው በጠበቁት የበለጠ ጋሻው ጅቦች ህይወቱን አጥቷል፡፡የምስራቅ አማራ ፋኖ ብርጌድ አዛዥ የሆነው በለጠ ጋሻው የኋላሸትና ጌታቸው ከሚባሉ የፅንፈኛ ሀይሉ አስተባባሪዎች ጋር 40 ታጣቂ ቡድኑን በመያዝ ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ወረዳ 020 ደፈርጌ ቀበሌ በተለምዶ ዋስሎጅ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደ ጅብ ከተደበቁበት በመውጣት የጥይት እሩምታ በመክፈት የግርማ የሺጥላን ህይወት ቀጥፈውታል፡፡
3.2K viewsAnt B, 20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 11:51:20 የኤርትራ ልጆች ውይይታቸውን በአማርኛ አድርገውታል። ኤርትራ ሰው በብሄር የማይገዳደልባት ወንጀል የሌለባት ብቸኛ ሀገር ነች ብለው ሲያወሩ ሞኝ ባያፍር ዘመዱ ያፍር ብለን ተውነው። በአፍሪካ ሁለተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ የገነባችውን ኢትዮጵያን ሲያጣጥሉ ስራ ጠል ሲያደርጉ ይውላሉ።

ኢትጵያዊያን ነን እኛ ቆንጆዎች ነን እናንተ አፍርካዊያን አስቀያሚዎች ናችሁ አንፈልጋችሁም ከከተማችን ውጡና ናይጄሪያ ሂዱልን እያሉ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እየነገዱ ኢትዮጵያዊያንንና ሃገሪቷን ለማስጠላት የሚታትሩት ኤርትራዊያን ታዝበናቸዋል። ኢትዮጵያዊያን አማራ ነን ሲሉ ይቆዩና በሌላ የቲክቶግ ገጽ ኦሮሞ ሆነው አማራውን ሲሳደቡ እንደርስባቸዋለን።

እኔ ለኤርትራዊያን ወገኖቼ የምመክሬቸው በኢትዮጵያ የውስጥ የፖለቲካ ጉዳይ ከመግባት እንዲቆጠቡ ነው። የራሴ የሚሉት ሀገር ያላቸው በመሆኑ ሙሉ ትኩረታቸውን በገዛ ሃገራቸው ላይ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ በህግ ለዜጎች ብቻ በተተዉት የስራ ዘርፎች ላይ ከመሰማራት መቆጠብ አለባቸው። ይህንንም የምለው በህግ ክልክል ስለሆነ ነው። ይህ ማለት ለንብረታችሁ ምንም ዋስትናና የህግ ከለላ የላችሁም ለማለት ነው።

እንደ መንግስት በስትራቴጂካዊ ጉዳዩች ትብብር ሊኖር ይችላል ። ግን እርግጠኛ መሆን ያለባችሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ህግንና ህገመንግስት መጣስ የሚችል ስልጣን ያለው ባለስልጣን የሌለ መሆኑን ነው። ስለሆነም ህዝቡም ሆነ መንግሥት እያንዳንዱን የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በጣም በቅርበት እየተከታተሉት ያሉት መሆኑን መረዳት ይኖርባችኋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኤርትራ መንግሥት የሚኖራቸው የህዝብ ለህዝብ የንግድና ኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዲሁም የሃገራቹ ግንኙነት የሚመራበትና የህግ መተላለፍ በሚኖርበት ጊዜ መደረግ ስላለባቸው ሁኔታዎች የተደረገ የመንግስታት ስምምነት ካለ ለኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርቦ መጽደቅ ይኖርበታል። ይህ ባልተደረገበት ባልተፈቀደ የውጭ ምንዛሪ የጥቁር ገበያ ላይ መሳተፍ በጥቃቅንና የነስተኛ ንግድ አስመጪና ላኪ አከፋፋይ ምግብ ቤት ጫት ቤት ማሳጅ ቤት ስራ ላይ መሰማራት መብት ሊኖራችሁ አይችልም ።

ከምንም ነገር በላይ ደግሞ የውጭ ሀገር ዜጎች መሆናችሁን መዘንጋት አይኖርባችሁም። አንድም ኢትዮጵያዊ ኤርትራ ሄዶ ንግድ ባልጀመረበት ችኮላችሁ ከልክ ያለፈ ሆኗል። አልፋችሁ ተርፋችሁ ኢትዮጵያዊያን ወንድማማቾች መሃል በመግባት የምትሰሩት ስራ መልካም አይደለምና በገለልተኝነት ራቅ ብላችሁ ብትመለከቱን ጥሩ ነው። በማህበራዊ ሚዲያ የራሳችሁን ጉዳይ በአማረኛ ማውራት መብታችሁ ነው። ግን ጉራውን ስድባችሁን ትንሽ ብትቀንሱልን መልካም ነው። ነጻነታችሁን በሃገራችሁ አጣጥሙት በምንም መለኪያ ለአንድ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ስለ ነጻነት ምንነት ልትነግሩት አትችሉምና ብታስቡበት ጥሩ ነው።
3.9K viewsAnt B, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 00:54:46 የአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ግርማ የሺጥላ መሰዋት እጅግ አዝኛለሁ።
ግርማ ላመነበት የወንድማማችነት እና ህብረብሔራዊ አንድነት አላማ በጀግንነት የታገለ የአቋም ሰው ነው ።
ዛሬ ግርማን መግደል ብትችሉም ሀሳቡንና የቆመለትን አላማ መግደል አትችሉም ። የጽንፈኝነት ተሸናፊ ሀሳብ እየሞተ የወንድማማችነት ሀሳብ አሸናፊ ሆኖ ይቀጥላል።

ለቤተሰቦቹ ፣ለወዳጆቹ እና ለስራ ጓዶቹ መጽናናትን እየተመኘሁ ፈጣሪ ነብሱን በአፀደ ገነት ያሳርፈው።

Itti gaafatamaa waajjira paartii badhaadhinaa damee Naannoo Amaaraa kan turan obbo Girmaa Yeshixilaa wareegamuu isaanii dhagahuu kiyyaan baay'ee gaddeera.

Girmaan kaayyoo obbolummaa fi tokkummaa sabdaneessummaa itti amaneef kan qabsaa'e nama ijjannooti.
Har'a Girmaa ajjeessuu dandeessanis yaadaa fi kaayyoo inni dhaabbateef ajjeessuu hin dandeessan.
Yaadni injifatamaan Finxaalessummaa du'aa, yaadni obbolummaa injifataa ta'ee itti fufa.

Maatii isaatiif, jaalattoota isaatii fi jaala hojii isaatiif jajjabina hawwaa waaqni lubbuu isaaf jannata akka kennun hawwaaf!

@adanechabiebie
4.2K viewsAnt B, 21:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 00:54:46
3.9K viewsAnt B, 21:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 04:10:22 ከህዝበ ውሳኔ ጋር በተያያዘ በወላይታ ዞን በተከሰተው የህግ ጥሰት 136 ተጠርጣሪዎች ተለይተው 93ቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል
***

ከደቡብ ክልል ህዝበ ውሳኔው ጋር በተያያዘ በወላይታ ዞን በተከሰተው የህግ ጥሰት 136 ተጠርጣሪዎች ተለይተው 93 ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

የፍትህ ሚኒስትር ድኤታው አቶ ፍቃዱ ፀጋ እና በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የወንጀል ምርመራና ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙልሳ አብዲሳ በጋራ በመሆን መግለጫ ዛሬ በጉዳዩ ዙሪያ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም ሁለት ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ስራውን ሲያከናውን እንደነበር ተገልጿል።

7 አባላት ያሉት በአዲስ አበባ ከአቃቤ ህግ፣ ከፖሊስ እና ከሌሎች አካላት የተደራጀ ሲሆን እንዲሁም በወላይታ ዞን በተመሳሳይ 23 አባላት ያሉት ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ስራውን እያከናወነ እንደሆነና በተቋቋመበት አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የደረሰበትን ውጤት አሳውቋል ተብሏል።

በውጤቱም የተፈጠረውን የህግ ጥሰት ለማጣራት በተቋቋመው ግብረ ሀይል በተከናወኑ ስራዎች አማካኝነት 136 ተጠርጣሪዎች ተለይተው 93ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው በመግለጫው ተመላክቷል።

ከእነኝህም መካከል 18 በወረዳና በቀበሌ የሚገኙ አመራሮች እንደሆኑና ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገልጿል።

118ቱ ደግሞ የምርጫ አስፈፃሚዎች ሲሆኑ፤ ከእነኝህም መካከል 75 በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተቀሩት 43 በቁጥጥር ስር እንዳልዋሉና ግብረ ሀይሉ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

https://t.me/Skyline7777
2.4K viewsAnt B, edited  01:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 00:03:17
https://t.me/Skyline7777
2.1K viewsAnt B, edited  21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 20:59:27
https://t.me/Skyline7777
2.6K viewsAnt B, edited  17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 18:16:40
ሱዳን ነደደች
1.6K viewsAnt B, 15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ