Get Mystery Box with random crypto!

ከህዝበ ውሳኔ ጋር በተያያዘ በወላይታ ዞን በተከሰተው የህግ ጥሰት 136 ተጠርጣሪዎች ተለይተው 93 | Skyline media

ከህዝበ ውሳኔ ጋር በተያያዘ በወላይታ ዞን በተከሰተው የህግ ጥሰት 136 ተጠርጣሪዎች ተለይተው 93ቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል
***

ከደቡብ ክልል ህዝበ ውሳኔው ጋር በተያያዘ በወላይታ ዞን በተከሰተው የህግ ጥሰት 136 ተጠርጣሪዎች ተለይተው 93 ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

የፍትህ ሚኒስትር ድኤታው አቶ ፍቃዱ ፀጋ እና በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የወንጀል ምርመራና ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙልሳ አብዲሳ በጋራ በመሆን መግለጫ ዛሬ በጉዳዩ ዙሪያ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም ሁለት ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ስራውን ሲያከናውን እንደነበር ተገልጿል።

7 አባላት ያሉት በአዲስ አበባ ከአቃቤ ህግ፣ ከፖሊስ እና ከሌሎች አካላት የተደራጀ ሲሆን እንዲሁም በወላይታ ዞን በተመሳሳይ 23 አባላት ያሉት ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ስራውን እያከናወነ እንደሆነና በተቋቋመበት አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የደረሰበትን ውጤት አሳውቋል ተብሏል።

በውጤቱም የተፈጠረውን የህግ ጥሰት ለማጣራት በተቋቋመው ግብረ ሀይል በተከናወኑ ስራዎች አማካኝነት 136 ተጠርጣሪዎች ተለይተው 93ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው በመግለጫው ተመላክቷል።

ከእነኝህም መካከል 18 በወረዳና በቀበሌ የሚገኙ አመራሮች እንደሆኑና ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገልጿል።

118ቱ ደግሞ የምርጫ አስፈፃሚዎች ሲሆኑ፤ ከእነኝህም መካከል 75 በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተቀሩት 43 በቁጥጥር ስር እንዳልዋሉና ግብረ ሀይሉ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

https://t.me/Skyline7777