Get Mystery Box with random crypto!

የኤርትራ ልጆች ውይይታቸውን በአማርኛ አድርገውታል። ኤርትራ ሰው በብሄር የማይገዳደልባት ወንጀል የ | Skyline media

የኤርትራ ልጆች ውይይታቸውን በአማርኛ አድርገውታል። ኤርትራ ሰው በብሄር የማይገዳደልባት ወንጀል የሌለባት ብቸኛ ሀገር ነች ብለው ሲያወሩ ሞኝ ባያፍር ዘመዱ ያፍር ብለን ተውነው። በአፍሪካ ሁለተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ የገነባችውን ኢትዮጵያን ሲያጣጥሉ ስራ ጠል ሲያደርጉ ይውላሉ።

ኢትጵያዊያን ነን እኛ ቆንጆዎች ነን እናንተ አፍርካዊያን አስቀያሚዎች ናችሁ አንፈልጋችሁም ከከተማችን ውጡና ናይጄሪያ ሂዱልን እያሉ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እየነገዱ ኢትዮጵያዊያንንና ሃገሪቷን ለማስጠላት የሚታትሩት ኤርትራዊያን ታዝበናቸዋል። ኢትዮጵያዊያን አማራ ነን ሲሉ ይቆዩና በሌላ የቲክቶግ ገጽ ኦሮሞ ሆነው አማራውን ሲሳደቡ እንደርስባቸዋለን።

እኔ ለኤርትራዊያን ወገኖቼ የምመክሬቸው በኢትዮጵያ የውስጥ የፖለቲካ ጉዳይ ከመግባት እንዲቆጠቡ ነው። የራሴ የሚሉት ሀገር ያላቸው በመሆኑ ሙሉ ትኩረታቸውን በገዛ ሃገራቸው ላይ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ በህግ ለዜጎች ብቻ በተተዉት የስራ ዘርፎች ላይ ከመሰማራት መቆጠብ አለባቸው። ይህንንም የምለው በህግ ክልክል ስለሆነ ነው። ይህ ማለት ለንብረታችሁ ምንም ዋስትናና የህግ ከለላ የላችሁም ለማለት ነው።

እንደ መንግስት በስትራቴጂካዊ ጉዳዩች ትብብር ሊኖር ይችላል ። ግን እርግጠኛ መሆን ያለባችሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ህግንና ህገመንግስት መጣስ የሚችል ስልጣን ያለው ባለስልጣን የሌለ መሆኑን ነው። ስለሆነም ህዝቡም ሆነ መንግሥት እያንዳንዱን የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በጣም በቅርበት እየተከታተሉት ያሉት መሆኑን መረዳት ይኖርባችኋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኤርትራ መንግሥት የሚኖራቸው የህዝብ ለህዝብ የንግድና ኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዲሁም የሃገራቹ ግንኙነት የሚመራበትና የህግ መተላለፍ በሚኖርበት ጊዜ መደረግ ስላለባቸው ሁኔታዎች የተደረገ የመንግስታት ስምምነት ካለ ለኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርቦ መጽደቅ ይኖርበታል። ይህ ባልተደረገበት ባልተፈቀደ የውጭ ምንዛሪ የጥቁር ገበያ ላይ መሳተፍ በጥቃቅንና የነስተኛ ንግድ አስመጪና ላኪ አከፋፋይ ምግብ ቤት ጫት ቤት ማሳጅ ቤት ስራ ላይ መሰማራት መብት ሊኖራችሁ አይችልም ።

ከምንም ነገር በላይ ደግሞ የውጭ ሀገር ዜጎች መሆናችሁን መዘንጋት አይኖርባችሁም። አንድም ኢትዮጵያዊ ኤርትራ ሄዶ ንግድ ባልጀመረበት ችኮላችሁ ከልክ ያለፈ ሆኗል። አልፋችሁ ተርፋችሁ ኢትዮጵያዊያን ወንድማማቾች መሃል በመግባት የምትሰሩት ስራ መልካም አይደለምና በገለልተኝነት ራቅ ብላችሁ ብትመለከቱን ጥሩ ነው። በማህበራዊ ሚዲያ የራሳችሁን ጉዳይ በአማረኛ ማውራት መብታችሁ ነው። ግን ጉራውን ስድባችሁን ትንሽ ብትቀንሱልን መልካም ነው። ነጻነታችሁን በሃገራችሁ አጣጥሙት በምንም መለኪያ ለአንድ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ስለ ነጻነት ምንነት ልትነግሩት አትችሉምና ብታስቡበት ጥሩ ነው።