Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ መግባት የሚፈልጉ” ያሏቸውን ኃይሎች፤ ከ | Skyline media

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ መግባት የሚፈልጉ” ያሏቸውን ኃይሎች፤ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ እየገቡ መፈትፈት የሚፈልጉ” ያሏቸውን “ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ኃይሎች” ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቡ። “በመገዳደል፣ በመሰዳደብ እና በመናናቅ” ለማሳካት የሚፈለግ “የፖለቲካ ዓላማ” ውስጥ ይሳተፋሉ ያሏቸውን ባለሀብቶች፣ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና በሀገር ውስጥ ያሉ ወጣቶችንም “ደጋግማው እንዲያስቡ” ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህንን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባው “የሃላላ ኬላ ሪዞርት” ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 23፣ 2015 በተመረቀበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ንግግራቸው፤ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተገደሉትን የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የአቶ ግርማ የሺጥላን ጉዳይ አንስተዋል።

አብይ በዛሬው ንግግራቸው፤ የብልጽግና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን የአቶ ግርማን ግድያ “አላግባብ መሰዋት” ሲሉ ጠርተውታል። አቶ ግርማን “ገና ሮጦ ያልጠገበ ወጣት፣ ለህዝቡ ለሀገሩ ብዙ ሊያገለግል የሚችል፣ ልጆች ቤተሰቦች ያሉት” ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በሰላም ቤተሰቡን ሊጠይቅ እየነዳ የሄደ፤ ጀግና መሳይ ፈሪዎች ተደብቀው በጥይት ገደሉት” ብለዋል። ይህንን ድርጊት የፈጸሙት ሰዎች፤ የሚፈልጉትን ነገር “በሀሳብ ብልጫ” “ብዙሃንን አሳምነው መከወን እንደማይሳካላቸው ያሰቡ” መሆናቸውን ተናግረዋል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/10784/