Get Mystery Box with random crypto!

ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ በአማራ ክልል ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በማ | Skyline media

ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

በአማራ ክልል ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በህቡዕ ተደራጅተውና ተቀናጅተው በሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።

በመሆኑም የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል እየወሰደ ባለው እርምጃ በዚህ ህቡዕ አደረጃጀት ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ የተገኙ 47 ተጠርጣሪዎችን ከበርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ ቦንቦችና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እንዲሁም ከሳተላይት መገናኛ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መረጃዎችን ከያዙ ላፕቶፖች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ አመልክቷል።

ተጠርጣሪዎቹ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን የግድያ ዒላማ በማድረግ፤ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ የክልሉን መንግሥታዊ መዋቅር በመቆጣጠር የፌደራል መንግሥትን ለመጣል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ተደራጅተው እና ተቀናጅተው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ እንደተደረሰባቸው አስታውቋል።

ግብረ-ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ፤ መንግስት የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እና ለሐሳብ ትግል ሰፊ ዕድል በመስጠቱ እንዲሁም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ባደረገው ጥረት ብዙዎች ይሄንን ዕድል መጠቀማቸውን አስታውሷል።

https://www.fanabc.com/archives/191875