Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-01 04:54:26 https://www.tiktok.com/t/ZTRcNk41w/
1.0K viewsAnt B, 01:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 02:38:31 በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት እርምጃ ጋር በተያያዘ የአንድ ሰው ህይወት ህልፈት ሪፓርት እንደደረሰው ኢሰመኮ አስታወቀ።

በቤት ማፍረስና በግዳጅ ማንሳት እርምጃ ለተጎዱ ሰዎች በሕጋዊ መንገድ የመኖሪያ ቤት የሚያገኙበትና ለደረሰባቸው የንብረት ውድመት ሊካሱ የሚችሉበት መንገድ በአፋጣኝ ሊመቻች እንደሚገባ አሳስቧል፡፡ 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት እርምጃ የመኖሪያ ቤት አልባነትን አባብሷል ብሏል።

ኢሰመኮ በጉዳዩ ዙሪያ በለገጣፎ ለገዳዲ፣ በሰበታ  አካባቢ ፉሪ እና ለቡ ተክለሃይማኖት እንዲሁም በቡራዩ ገፈርሳ ኖኖ አካባቢዎች በመዘዋወር ቀደም ሲል የፈረሱ እና የማፍረስ ተግባሩ እየተከናወነ የነበረባቸውን አካባቢዎች ተመልክቻለሁ ነው ያልው፡፡

ኮሚሽኑ በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ በመገኘት
እየፈረሱ የነበሩ ቤቶችንም ለመመልከት ችሏል።
በምልከታው የቤት ማፍረሱ እና በግዳጅ ማስነሳቱ በግብረ ኃይል እየተከናወነ እንደነበረ እና በቦታው ከፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት በተጨማሪ ሌሎች ዱላ የያዙ ሲቪል ሰዎች እንደነበሩም መመልከቱን ነው ያሳወቀው።

በዘመቻ ቤት የማፍረሱ ሂደት ተገቢ ልየታ ያልተደረገበት ስለመሆኑ  ፣ አድሏዊ አሰራሮች መኖራቸውና ይህም ከብሔር ማንነት ጋር የተገናኘ መሆኑን፣ እና በቂ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ቤቶች እንደሚፈርሱ መረዳቱን ገልጿል።

እስር፣ የአካል እና የስነልቦና ጉዳት መድረሱንም በሪፓርቱ ኢሰመኮ አትቷል። ፊሊዶሮ በተባለ ቦታ ላይ በተደረገው የቤት ፈረሳ የሰው ሕይወት ማለፉን ኢሰመኮ መረጃ የደረሰው ሲሆን ይህን በተመለከተ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አስታውቋል። 

ኢሰመኮ ከአቤቱታ አቅራቢዎች እና ተገቢነት ካላቸው የመንግሥት አካላት ባሰባሰበው መረጃ እና ማስረጃ መሠረት የማፍረስና በግዳጅ የማንሳት እርምጃው በርካታ ቤተሰቦችን ለከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ቀውስ ዳርጓል፤ ተማሪዎች ከትምህርታቸው ለማቋረጥ ተገደዋል፤ በርካታ ቤተሰቦች የእለት ተእለት ተግባራቸውን ማከናወን የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፤ በርካታ ቤተሰቦች ተፈናቅለው ወደ ሌሎች ቦታዎች ለመሄድ ተገደዋል፤ ከፊሎቹም መንገድ ላይ ወድቀዋል ወይም በተለያዩ የሀገር ውስጥ መጠለያ ጣቢያ በመሰብሰብ የመንግሥት እርዳታ ለመጠባበቅ ተገደዋል" ነው ያለው፡፡ 

የክልሉ መንግሥትና የከተማ አስተዳደሩ የማፍረስና በግዳጅ የማንሳት እርምጃውን ተግባራዊ ከማድረግ በፊት ቤቶቹ እንደተገነቡበት የይዞታ ዓይነትና ሁኔታ፣ ለብዙ ዓመታት የመብራት እና የውሃ እንዲሁም ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን እየሰጠ እና ነዋሪዎቹ የማኅበራዊ ሕይወት እንዲመሠርቱ ሲያደርግ የቆየ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት አማራጭ መፍትሔዎችን በማመቻቸት የሰብአዊ መብቶች መከበራቸውንና መጠበቃቸውን ሊያረጋግጥ ይገባ እንደነበር አስገንዝቧል፡፡ 

በቤት ማፍረስና በግዳጅ ማንሳት እርምጃ ለተጎዱ ሰዎች በሕጋዊ መንገድ የመኖሪያ ቤት ሊያገኙ የሚችሉበት መንገድና ለደረሰባቸው የንብረት ውድመት ሊካሱ የሚችሉበት መንገድ በአፋጣኝ ሊመቻች እንደሚገባ አሳስቧል፡፡ 

የኢሰመኮ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል “ኢመደበኛ ይዞታዎቸን መከላከል የመንግሥት ኃላፊነት ቢሆንም የማፍረስና በግዳጅ የማንሳት እርምጃዎች ሰዎች ሕይወታቸው እንዲናጋ እና ቤተሰብ እንዲበተን የሚያደርግ መሆን የለበትም፤ ይልቁንም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች የተከበሩበት አሠራር መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል” ብለዋል፡፡
1.3K viewsAnt B, 23:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 19:20:15 https://www.tiktok.com/t/ZTRvsSwC6/
1.0K viewsAnt B, 16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 10:43:04 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02fE5z2UPxxVmZyLwvKCR31F7ciERkjixAGxhLvxZsdhPXQcmtJjEf3VXaxU7pnxWSl&id=100084991505029&mibextid=NzXCef
1.3K viewsAnt B, 07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 05:02:18 በግብረ ስጋ ግንኙነት
፣በደም ንክኪ ፣በምራቅ፣በእንባና በስለታም ነገሮች በቀላሉ
ይተላለፋል ።
ይህ ቫይረስ የከፋ ጉዳትና ሞት ሊያስከትል ይችላል።
ነገርግን አብዛኛው አዋቂ ሰው ቫይሱ ምንም ጉዳት
ሳያደርስበት የሚለቀው ሲሆን ከ5-10% ሰዎች ላይ ቋሚ የጉበት ጉዳት ያደርሳል ።
እነዚህ ሰዎች ካልታከሙ የጉበት ድክመት /
liver failure ወይም የጉበት ካንሰር ሊያጋጥማቸው ይችላል።
የሚታወቀው በደም ምርመራ ሲሆን ጉበት ላይ ጉዳት ማድረስ
ከጀመረ እና በከፍተኛ መራባት ከጀመረ
(ቫይራል ሎድ ከ10ሺ በላይ ከሆነ) ህክምና መጀመር
ያስፈልጋል።
መድሃኒቶቹ ከኤችአይቪ መድሀኒቶች ተመሳሳይ
ሲሆኑ በአሁን ሰዓት ጥሩ ሚባለው 93%የ ይሰራል። ይህም
ቴኖፎቪር/Tenofovir በመባል ይታወቃል ።
ሌሎች መድኃኒት
የማያስፈልጋቸው (ለመጀመር መስፈርቶችን የማያሟሉ) በየ
6ወሩ ክትትል ማድረግ አለባቸው ።
ተመርምረው ቫይረሱ
የሌለባቸው (ይዟቸውየማያውቅ)
ሰዎች ክትባት በመውሰድ
ራሳቸውን ከዚህ ቫይረስ መከላከል አለባቸው ።

ሄፓታይቲስ ሲ/Hepatitis C፦

ይህ ቫይረስ በብዙ ነገሮች
ከሌሎቹ ጉበትን ከሚጎዱ ቫይረሶች ከበድ ይላል።
አንደኛይህ ቫይረስ የያዛቸው 75 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ቋሚ የጉበት ጉዳት ይደርስባቸዋል ።
ይህም ለጉልበት ድክመት /liver failure እና
ለጉበት ካንሰር ይዳርጋል። ሁለተኛ ክትባትም የለውም።
መተላለፊያ መንገዶቹ ከኤችአይቪ መተላለፊያ መንገዶች
ተመሳሳይ ስለሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይበጃል ።

ሄፓታይቲስ ዲ/Hepatitis D፦

ይህ ቫይረስ ያለ ሄፓታይቲስ ቢ
መኖር ስለማይችል በዚህ ቫይረስ የተጠቃ ሰው ሄፓታይቲስ ቢ አብሮት አለ።
ይህ ጥምር ቫይረስ እንዳይዘን የሄፓታይቲስ ቢን
ክትባት መውሰድ ይጠቅማል።

ሄፓታይቲስ ኢ/Hepatitis E፦

ይህ ቫይረስ ለክ እንደ ሄፓታይቲስ
ኤ መተላለፊያ መንገዱ በተበከለ ውሃና ምግብ ነው።
በደም ምርመራ የሚታወቅ ሲሆን ባብዛኛው በራሱ ይጠፋል።
በእርግዝና ወቅት ከተከሰተ ጉበት ላይ ጫና በማድረስ በጠና ሊያሳምም ይችላል። ሕክምናዉም ድጋፋዊ ነው።

ደውለው የውስጥ ዴዌ ስፔሻሊስት ሀኪም ያማክሩ፣ ቀጠሮ ያስይዙ፣
በአካል መተው ይጎብኙን።
አድራሻ፦ አርባምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጀርባ
ስልክ፡- 0911541625/0911052389
2.0K viewsAnt B, 02:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 05:02:17
# viralhepatitis ሄፓታይቲስ/የጉበት ኢንፌክሽን

ጉበታችን በብዙ ዓይነት ቫይረሶች ልትጠቃ ትችላለች። ጉበትን ከሚያጠቁ የቫይረሶች ዓይነቶች ዋናዎቹን እናያለን ።
የመጀመሪያው

ሄፓታይትስ ቫይረስ ኤ/hepatitis virus A

ይህ ቫይረስ የሚተላለፈው በሽታው ያለበት ሰው የተፀዳዳው ዓይነምድር ከውሃ ወይም ከምግብ ጋር ተነካክቶ ሌላ ጤነኛ ሰው ያንን የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ ሲመገብ ወይም ሲጠጣ ነው።
ንፅህናን በማሻሻል ቫይረሱ እንዳይዘን ማድረግ
ይጠበቅብናል።
ይህ ቫይረስ በአንደኛ ደረጃ በስፋት የሚገኝ
ቫይረስ ሲሆን በብዛት ህፃናትንና ወጣቶችን ያጠቃል።
በማደግ ላይ ባሉ አንዳንድ ሀገሮች እስከ 75% ያለው ህዝብ በዚህ
ቫይረስ ይያዛል።
ባብዛኛው በቶሎ በራሱ የሚድን ሲሆን
በአንዳንድ ሰዎች የጠና ህመም ወይም ሞት ሊያስከትል
ይችላል ።
በደም ምርመራ የሚታወቅ ሲሆን ቋሚ የሆነ የጉበት
ጉዳት አያደርስም።
አንዴ ካመመን ወይም ክትባቱን ከወሰድን ከዚህ በሽታ ይከላከልልናል።

ሄፓታይቲስ ቢ/Hepatitis B፦

ይህ በብዛት በሁለተኛ
ደረጃየሚገኝ ነገርግን የከፋ ጉዳት ሊያደርስ የሚያችል ቫይረስ ነዉ ።
በአፍሪካ እኔ በኤዥያ ክፍለ አህጉራት በስፋት ይገኛል።
ይህም የሆነዉ በነዚህ አህጉራት ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ ስለሚተላለፍ ነው ።
በሀገራችን በሰፊው የሚገኝ ሲሆን በጣም በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል ።
1.9K viewsAnt B, 02:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 21:01:14 የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቋል፦ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት 
**** 

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ
ግንባታ 90 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታወቀ። 

የሕዳሴ ግድብ መሠረተ ድንጋይ የተጣለበት 12ኛ ዓመት የቦንድ ሳምንትን አስመልክቶ ጽ/ቤቱ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ሴት ነጋዴዎች ማኅበር እና ሌሎች ማኅበራት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
ለግድቡ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ የፖለቲካ ልዩነት፣ ዕድሜ እና ጾታን ሳይገድብ የተደረገ መሆኑን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብረሓ ገልጸዋል። 
937 viewsAnt B, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 14:45:48
አቶ ጌታቸው ረዳ  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ የፌዴሬሸን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት፣ እንዲሁም በኢፌዴሪ መንግስት እና በህወሓት መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና ግጭትን ለማስቆም በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ በተደረገው የሰላም ስምምት አንቀጽ (10) መሰረት አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም አስፈልጓል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 9 ቀን 2015 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ “የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ደንብን ማጽደቁ ተመላክቷል፡፡

በዚሁ ደንብ አንቀጽ 3(2) መሰረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አድርገው  መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት አስታውቋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎችን ውክልና የሚያረጋገጥ እና አካታች የሆነ አስተዳደር በማዋቀር የክልሉን አስፈጻሚ አካል የመምራት እና የማስተባበር ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

https://t.me/Skyline7777
2.6K viewsAnt B, edited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 15:36:02 ምክር ቤቱ ህወሓትን ከሽብርተኝነት ሰረዘ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ልዩ ጉባኤው ነው ከሁለት ዓመታት በፊት በህወሓት ላይ ተጥሎ የነበረውን የሽብርተኝነት ወንጀል ያነሳው።

ከ2 ዓመት በፊት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ምክንያት የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 20 ንኡስ አንቀጽ 2 መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዚያ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና “ሸኔ’’ ድርጅቶች በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሃሳብ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ምክር ቤቱ እንዳጸደቀው ይታወሳል።

በጉዳዩ ላይ የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፤ በመጨረሻም ህወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ለማውጣት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በ61 ተቃውሞ እና በ5 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

https://t.me/Skyline7777
1.8K viewsAnt B, edited  12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 15:19:53
ኖብ ኮምፕሌክስ ድንቅ ህንጻ መሃል አብነት ላይ አስገንብቶ አጠናቀቀ ። ለሽያጭም አቀረበ። የአፓርትመንትና የንግድ ቤት ግዥዎች እንኳን ደስ አላችሁ። እውነተኛና ከፍለው ቁልፉን የሚቀበሉበት ቀጠሮ የሌለው መልካም አጋጣሚ ተፈጥሯል። ይፍጠኑ!!

  የቤቶን ቁልፍ ዛሬውኑ ይረከቡ
የመኖሪያ ቤት ሽያጭ በመሀል ከተማ
  
    አድራሻ ፦ ወደ አብነት መታጠፊያ ጆስ ሃንሰን ወረድ ብሎ
  ሙሉ ለሙሉ ጥንቅቅ ብሎ የተገነባ G+9
99% የደረሠ
  ወዲያው የሚረከቡት
ከ178 ካሬ እስከ 252ካሬ ሜትር ስፋት እንደፍላጎትዎ አለልዎ።

    ህንፃው የሚኖሩት አገልግሎቶች

ቴራስ፣ኢንተርኮም፣ ጋርቤጅ ሹተር፣ ሊፍት (2)፣ለሁሉም የህንፃው ክፍል ጀኔሬተር ፣ የውሀ ታንከር እንዲሁም
   ፋርማሲ፣ባንኮች፣ ለንግድ ቦታም አመቺ ነው።
 
  ሳይት ለመጎብኘት እና ቢሮ ለመምጣት
     +252930106598
       +251911-978792
+251911666097
1.9K viewsAnt B, 12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ