Get Mystery Box with random crypto!

በግብረ ስጋ ግንኙነት ፣በደም ንክኪ ፣በምራቅ፣በእንባና በስለታም ነገሮች በቀላሉ ይተላለፋል ። ይህ | Skyline media

በግብረ ስጋ ግንኙነት
፣በደም ንክኪ ፣በምራቅ፣በእንባና በስለታም ነገሮች በቀላሉ
ይተላለፋል ።
ይህ ቫይረስ የከፋ ጉዳትና ሞት ሊያስከትል ይችላል።
ነገርግን አብዛኛው አዋቂ ሰው ቫይሱ ምንም ጉዳት
ሳያደርስበት የሚለቀው ሲሆን ከ5-10% ሰዎች ላይ ቋሚ የጉበት ጉዳት ያደርሳል ።
እነዚህ ሰዎች ካልታከሙ የጉበት ድክመት /
liver failure ወይም የጉበት ካንሰር ሊያጋጥማቸው ይችላል።
የሚታወቀው በደም ምርመራ ሲሆን ጉበት ላይ ጉዳት ማድረስ
ከጀመረ እና በከፍተኛ መራባት ከጀመረ
(ቫይራል ሎድ ከ10ሺ በላይ ከሆነ) ህክምና መጀመር
ያስፈልጋል።
መድሃኒቶቹ ከኤችአይቪ መድሀኒቶች ተመሳሳይ
ሲሆኑ በአሁን ሰዓት ጥሩ ሚባለው 93%የ ይሰራል። ይህም
ቴኖፎቪር/Tenofovir በመባል ይታወቃል ።
ሌሎች መድኃኒት
የማያስፈልጋቸው (ለመጀመር መስፈርቶችን የማያሟሉ) በየ
6ወሩ ክትትል ማድረግ አለባቸው ።
ተመርምረው ቫይረሱ
የሌለባቸው (ይዟቸውየማያውቅ)
ሰዎች ክትባት በመውሰድ
ራሳቸውን ከዚህ ቫይረስ መከላከል አለባቸው ።

ሄፓታይቲስ ሲ/Hepatitis C፦

ይህ ቫይረስ በብዙ ነገሮች
ከሌሎቹ ጉበትን ከሚጎዱ ቫይረሶች ከበድ ይላል።
አንደኛይህ ቫይረስ የያዛቸው 75 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ቋሚ የጉበት ጉዳት ይደርስባቸዋል ።
ይህም ለጉልበት ድክመት /liver failure እና
ለጉበት ካንሰር ይዳርጋል። ሁለተኛ ክትባትም የለውም።
መተላለፊያ መንገዶቹ ከኤችአይቪ መተላለፊያ መንገዶች
ተመሳሳይ ስለሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይበጃል ።

ሄፓታይቲስ ዲ/Hepatitis D፦

ይህ ቫይረስ ያለ ሄፓታይቲስ ቢ
መኖር ስለማይችል በዚህ ቫይረስ የተጠቃ ሰው ሄፓታይቲስ ቢ አብሮት አለ።
ይህ ጥምር ቫይረስ እንዳይዘን የሄፓታይቲስ ቢን
ክትባት መውሰድ ይጠቅማል።

ሄፓታይቲስ ኢ/Hepatitis E፦

ይህ ቫይረስ ለክ እንደ ሄፓታይቲስ
ኤ መተላለፊያ መንገዱ በተበከለ ውሃና ምግብ ነው።
በደም ምርመራ የሚታወቅ ሲሆን ባብዛኛው በራሱ ይጠፋል።
በእርግዝና ወቅት ከተከሰተ ጉበት ላይ ጫና በማድረስ በጠና ሊያሳምም ይችላል። ሕክምናዉም ድጋፋዊ ነው።

ደውለው የውስጥ ዴዌ ስፔሻሊስት ሀኪም ያማክሩ፣ ቀጠሮ ያስይዙ፣
በአካል መተው ይጎብኙን።
አድራሻ፦ አርባምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጀርባ
ስልክ፡- 0911541625/0911052389