Get Mystery Box with random crypto!

# viralhepatitis ሄፓታይቲስ/የጉበት ኢንፌክሽን ጉበታችን በብዙ ዓይነት ቫይረሶች ልትጠቃ | Skyline media

# viralhepatitis ሄፓታይቲስ/የጉበት ኢንፌክሽን

ጉበታችን በብዙ ዓይነት ቫይረሶች ልትጠቃ ትችላለች። ጉበትን ከሚያጠቁ የቫይረሶች ዓይነቶች ዋናዎቹን እናያለን ።
የመጀመሪያው

ሄፓታይትስ ቫይረስ ኤ/hepatitis virus A

ይህ ቫይረስ የሚተላለፈው በሽታው ያለበት ሰው የተፀዳዳው ዓይነምድር ከውሃ ወይም ከምግብ ጋር ተነካክቶ ሌላ ጤነኛ ሰው ያንን የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ ሲመገብ ወይም ሲጠጣ ነው።
ንፅህናን በማሻሻል ቫይረሱ እንዳይዘን ማድረግ
ይጠበቅብናል።
ይህ ቫይረስ በአንደኛ ደረጃ በስፋት የሚገኝ
ቫይረስ ሲሆን በብዛት ህፃናትንና ወጣቶችን ያጠቃል።
በማደግ ላይ ባሉ አንዳንድ ሀገሮች እስከ 75% ያለው ህዝብ በዚህ
ቫይረስ ይያዛል።
ባብዛኛው በቶሎ በራሱ የሚድን ሲሆን
በአንዳንድ ሰዎች የጠና ህመም ወይም ሞት ሊያስከትል
ይችላል ።
በደም ምርመራ የሚታወቅ ሲሆን ቋሚ የሆነ የጉበት
ጉዳት አያደርስም።
አንዴ ካመመን ወይም ክትባቱን ከወሰድን ከዚህ በሽታ ይከላከልልናል።

ሄፓታይቲስ ቢ/Hepatitis B፦

ይህ በብዛት በሁለተኛ
ደረጃየሚገኝ ነገርግን የከፋ ጉዳት ሊያደርስ የሚያችል ቫይረስ ነዉ ።
በአፍሪካ እኔ በኤዥያ ክፍለ አህጉራት በስፋት ይገኛል።
ይህም የሆነዉ በነዚህ አህጉራት ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ ስለሚተላለፍ ነው ።
በሀገራችን በሰፊው የሚገኝ ሲሆን በጣም በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል ።