Get Mystery Box with random crypto!

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቋል፦ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት  | Skyline media

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቋል፦ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት 
**** 

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ
ግንባታ 90 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታወቀ። 

የሕዳሴ ግድብ መሠረተ ድንጋይ የተጣለበት 12ኛ ዓመት የቦንድ ሳምንትን አስመልክቶ ጽ/ቤቱ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ሴት ነጋዴዎች ማኅበር እና ሌሎች ማኅበራት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
ለግድቡ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ የፖለቲካ ልዩነት፣ ዕድሜ እና ጾታን ሳይገድብ የተደረገ መሆኑን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብረሓ ገልጸዋል።