Get Mystery Box with random crypto!

አቶ ጌታቸው ረዳ  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ አቶ ጌታቸው | Skyline media

አቶ ጌታቸው ረዳ  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ የፌዴሬሸን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት፣ እንዲሁም በኢፌዴሪ መንግስት እና በህወሓት መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና ግጭትን ለማስቆም በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ በተደረገው የሰላም ስምምት አንቀጽ (10) መሰረት አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም አስፈልጓል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 9 ቀን 2015 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ “የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ደንብን ማጽደቁ ተመላክቷል፡፡

በዚሁ ደንብ አንቀጽ 3(2) መሰረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አድርገው  መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት አስታውቋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎችን ውክልና የሚያረጋገጥ እና አካታች የሆነ አስተዳደር በማዋቀር የክልሉን አስፈጻሚ አካል የመምራት እና የማስተባበር ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

https://t.me/Skyline7777