Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.54K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-01-30 06:04:00
ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል
የተላለፈ መልዕክት፤
ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተው ችግር ሁላችንንም እጅግ አሳዝኖናል፡፡ አሁንም የቤተክርስቲያኒቱ ብፁዓን አባቶች በጸሎት፤ በታላቅ ማስተዋልና በይቅርታ የተከሰተውን ክፍተት በመዝጋት አንድነትዋ የተጠበቀ ጠንካራ ቤተክርስቲያን ሆና እንድትቀጥል እንደሚያደርጉ እምነታችን ነው፡፡
ይህ እስከሚሆን ድረስ ግን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል፤ የቤተክርስቲያኒቱን አንደነትና ሰላም በተመለከተ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላካችን ፊት በጸሎት ማቅረባችንን እንደምንቀጥል ስንገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን የሰላምና የፍቅር ዓመት ያድርግልን!!

ቄስ ደረጀ ጀምበሩ
የካውንስሉ ጠቅላይ ፀሐፊ
4.8K viewsAnt B, 03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 13:53:19 1. የተማሪዎች አማካይ ውጤት በየትምህርት አይነቱ፤

አጠቃላይ መረጃ፡-  ፈተና የተፈተኑ ብዛት-----908,256 ናቸው፡፡

  አማራ………..30.37%
  ኦሮሚያ…..…27.96%
  ደቡብ………..28.17%
  ሀረሪ…………32.88%
  አዲስ አበባ----38.46%
  ደሬደዋ--------31.42%
  ሲዳማ---------28.34%

2. ከ50% እና በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት ከተፈተኑ መካከል

(እንደ ሀገር ያለፉ 29909 (3.3%) ናቸው

  አማራ………ከ246,675 መካከል 8,810 ((3.6%)
  ኦሮሚያ…..…327,737 መካከል 6,407 (2.0%)
  ደቡብ………..ከ127,345 መካል 2,533 (2.0%)
  ሀረሪ…………ከ1,849 መካከል 194 (10.5%)
  አዲስ አበባ----ከ47,980 መካከል 9,491 (19.8%)
  ደሬደዋ-------- ከ3,726 መካከል 250 (6.7%)
  ሲዳማ---------ከ53,478 መካከል 1247 (2.3%)

3. ተፈጥሮ ሳይንስ  ከ600 እና በላይ እንደ ሀገር 263 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ

  አማራ………70 ተማሪዎች
  ኦሮሚያ…..…51 ተማሪዎች
  ደቡብ………..10 ተማሪዎች
  ሀረሪ…………1 ተማሪዎች
  አዲስ አበባ----117 ተማሪዎች
  ደሬደዋ-------- 2 ተማሪዎች
  ሲዳማ---------8 ተማሪዎች

4. ማህበራዊ ሳይንስ  ከ500 እና በላይ እንደሀገር 10 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ

  አማራ………1ተማሪ
  አዲስ አበባ----8 ተማሪዎች
  ደሬደዋ-------- 1 ተማሪ

5. ሁሉንም ተማሪዎች 100% ያሳለፉ ት/ቤቶች 7 ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ

  ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት
  ባሕር ዳር ስቲም ት/ቤት
  ጎንደር ኮሙኒቲ ስኩል
  ወላይታ ሶዶ ሊቃ ት/ ቤት
  አዳማ ኦዳ አዳሪ ት/ ቤት
ናቸው።

6. ከፍተኛ ውጤት (የዓመቱ ሰቃይ)

 ከአማራ ክልል ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ ሚኪያስ አዳነ 666 አስመዝግቧል።
5.7K viewsAnt B, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 05:26:54
መረጃ

- በሀገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ባ1 ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ብሔራዊ ፈተና አላለፈም።

- የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተኑ 2 ሺህ 959 የመደበኛ ትምህርት ቤቶች መካከል ነው 1 ሺህ 161 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪዎችን እንዳላሰለፉ የታወቀው።

- ከአጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 798 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ አሳልፈዋል።

- 7 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ ያሳለፉ ሲሆን እነዚህም ትምህርት ቤቶች ፦

ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ ቤት፣
ኦዳ አዳሪ ልዩ ት/ቤት ፣
ባህርዳር ስቴም ት/ቤት  ፣
ወላይታ ሊቃ ት/ቤት፤
የጎንደር ማህበረሰብ አቀፍ ት/ቤት እና ከግል ትምህርት ቤት ደግሞ ለባዊ ት/ቤት ናቸው።

ምንጭ፦ WMCC

@sheger_press
@sheger_press
5.4K viewsAnteneh Babanto, 02:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 20:06:28 ሰበር ዜና

የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ሁሉም ወደ ዩንቨርስቲ መግባታቸውን አረጋገጡ።

ከተመሰረተበት ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ ብቁ እና ተወዳዳሪ ትውልድ እያፈራ ያለው የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ዘንድሮም ይህንኑ ታሪክ ደግሟል።

የዘንድሮውን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከተፈተኑ 75 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የዘንድሮ ከፍተኛ ውጤትም 643 ሆኖ ተመዝግቧል።

አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን በትምህርት ቤቱ ደረጃ የአንድ ተማሪ ውጤት ብቻ  378 ዝቅተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን ከትምህርት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዘንድሮ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ከተፈተኑ 980ሺህ ተማሪዎች መካከል 28ሺህ ብቻ ወደ ዩንቨርስቲ የሚያስገባ ውጤት ማምጣታቸውን ዘገባን ነበር።

   #በተገኘውም ውጤት እንኳን ደስ ያላችሁ
https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777
6.2K viewsAnteneh Babanto, edited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 21:04:41
አሸናፊም ተሸናፊም የለም ከ77 ቀናት በፊት ከተፈረመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የተወሰደ

ወድቀናል ተዋርደናል ተሸንፈናል።ከዚህ ሃቅ መሸሽ አንችልም። አሸንፈናል ገለመሌ ብንል ራሳችንን ከመሸወድ ያለፈ ፋይዳ የለውም። የሰላም ስምምነቱንም ቢሆን ምንም የተለየ ነገር ስለፈጠርን የሆነ ነገር አይደለም ፤ ወደን ሳይሆን ተገደን ነው የፈረምነው

ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ከሁለት ቀናት በፊት ለTPM የተናገረው

ትርጉም በአስፋው አብርሃ
1.4K viewsAnt B, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 00:55:04 https://www.tiktok.com/t/ZTRp2XUaT/
1.1K viewsAnt B, 21:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 13:27:00
ያለምወርቅ ጀምበር አሸንፋለች!
የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ 1,000,000 ብርና ዋንጫውን ወስዳዋለች!
ይገባታል!
2.2K viewsAnt B, 10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 11:04:41 https://www.tiktok.com/t/ZTRgK8U4V/
347 viewsAnteneh Babanto, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 11:16:02 የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤ አቶ ታከለ ኡማ፤ አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬን በክብር ሸኘ
*****

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤ አቶ ታከለ ኡማ፤ አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ በክብር ሸኝቷቸዋል።

በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራቱንም የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው መመኘቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
1.5K viewsAnt B, 08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 11:12:34
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፤ አቶ ታከለ ኡማ፤ አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ በክብር ሸኝቷቸዋል።
በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራቱንም የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው ተመኝቷል።
1.5K viewsAnt B, 08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ