Get Mystery Box with random crypto!

ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የተላለፈ መልዕክት፤ ጥር 19 ቀን 20 | Skyline media

ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል
የተላለፈ መልዕክት፤
ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተው ችግር ሁላችንንም እጅግ አሳዝኖናል፡፡ አሁንም የቤተክርስቲያኒቱ ብፁዓን አባቶች በጸሎት፤ በታላቅ ማስተዋልና በይቅርታ የተከሰተውን ክፍተት በመዝጋት አንድነትዋ የተጠበቀ ጠንካራ ቤተክርስቲያን ሆና እንድትቀጥል እንደሚያደርጉ እምነታችን ነው፡፡
ይህ እስከሚሆን ድረስ ግን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል፤ የቤተክርስቲያኒቱን አንደነትና ሰላም በተመለከተ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላካችን ፊት በጸሎት ማቅረባችንን እንደምንቀጥል ስንገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን የሰላምና የፍቅር ዓመት ያድርግልን!!

ቄስ ደረጀ ጀምበሩ
የካውንስሉ ጠቅላይ ፀሐፊ