Get Mystery Box with random crypto!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤ አቶ ታከለ ኡማ፤ አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ | Skyline media

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤ አቶ ታከለ ኡማ፤ አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬን በክብር ሸኘ
*****

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤ አቶ ታከለ ኡማ፤ አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ በክብር ሸኝቷቸዋል።

በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራቱንም የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው መመኘቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።