Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.26K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-12-25 07:49:04
Video from ሰው
2.9K viewsAnt B, 04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 05:59:28 https://fb.watch/hDtxz5_xf_/
229 viewsAnt B, 02:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 10:56:59
የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሐት ማምሻውን በናይሮቢ የተፈራረሙበት ሠነድ::
2.3K viewsAnteneh Babanto, 07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 10:44:51
የአሜሪካው ኤግዚም ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የ281 ሚሊየን ዶላር የብድር መተማመኛ አፀደቀ

የአሜሪካው ኤግዚም (ኢምፖርት ኤክስፖርት) ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የ281 ሚሊየን ዶላር የብድር መተማመኛ አፀደቀ።
ባንኩ ያፀደቀው የብድር መተማመኛ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት እንደሚውል ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈም በአሜሪካ የተለያዩ አካባቢዎች ለ1 ሺህ 600 ሰዎች የሥራ እድል ለመፍጠር እንደሚያግዝ የባንኩ መረጃ ያመላክታል።
ባንኩ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪም ለዩናይትድ ኪንግደም 407 ሚሊየን ዶላር የብድር መተማመኛ ማፅደቁንም አስታውቋል።
በአጠቃላይ ባንኩ 688 ሚሊየን ዶላር የብድር መተማመኛን ያፀደቀ ሲሆን፥ ይህም በአሜሪካ ለ4 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እንደሚያግዝም ገልጿል።
ውሳኔው ባንኩ ከሀገራቱ ጋር ያለውን ትስስር የሚያጎለብት መሆኑንም ነው የገለጸው።
2.3K viewsAnt B, 07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-23 10:38:07
የኢትዮጵያን ጠ/ሚ ዶክተር አቢይ

#ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ጋር በመሆን ዛሬ የወላይታ ሶዶ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካን መርቀዋል::

ይህ ፋብሪካ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ከሚሠሩ በርካታ ድኻ ተኮር ሥራዎች አንዱ ብለዋል ። ሥራው #ኢትዮጵያን ቀጣናዊ እና አህጉራዊ የዳቦ ቅርጫት ለማድረግ ያለመ ብለዋል ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቀን 300 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቀን 300 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካን በወላይታ ሶዶ ከተማ መርቀው ከፈቱ፡፡

ፋብሪካው በወላይታ ሶዶ ከተማ የተገነባ ሲሆን፥ ከዳቦ በተጨማሪ 42 ቶን ዱቄት የማምረት አቅም አለው ተብሏል።

ፋብሪካውን በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት አማካኝነት፥ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ሂቤይ ፒንግል ማሽነሪስ አጋርነት የተገነባ ነው።

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በ11 ከተሞች ተመሳሳይ አቅም ያላቸው ዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎችን በጋራ ለመገንባት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ጋር ከተፈራረመ በኋላ ፅህፈት ቤቱ ሁለተኛውን ዳቦ ፋብሪካ ነው ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ ያስመረቀው።
3.4K views@A, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 12:29:04
የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በሚቀጥሉት 40 ዓመታት ለ7 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገለጸ
****
የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በሚቀጥሉት 40 ዓመታት ለ7 ሚሊዮን ዜጎች ፈጠራ ላይ የተመሰረተ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለሥልጣን አስታወቀ።

ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በቀጣይ 40 ዓመታት በአራት ዙሮች በ21 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል በጀት 24 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ዕቅድ መያዙን የባለስልጣኑ ዋና ኃላፊ አቶ ሞቱማ ተመስገን በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ የቀጣይ 40 ዓመታት የመነሻ፣ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ዕቅድ በጀት እና የሥራ ዝርዝር ተቀምጦ ወደ ሥራ መገባቱንም አቶ ሞቱማ አስታውቀዋል።

እንደ አቶ ሞቱማ ገለጻ፣ እ.አ.አ ከ2022 እስከ 2027 የአጭር ጊዜ እቅድ ሲሆን በ3 ቢሊየን ዶላር መነሻ ካፒታል 3 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የመሰረተ ልማት ዝርጋታው ተጀምሯል።
1.6K viewsAnt B, edited  09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 08:57:17
በኳስ ሜዳ ተጨዋቾች ደስታቸውን ለመግለጽ ልብሳቸውን ማውለቅ አለመቻላቸውን ያወልቃሉ?

ቢጫ ካርድም ይሰጣቸዋል። በስታዲዬም የሚገኙ ተመልካቾችና ደጋፊ ወንዶች ቲሸርት ቢያወልቁ የሚጠይቃቸው የለም። አንዲት የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ደጋፊ ሴት በኳታሩ የአለም ዋንጫ ፍጻሜ ሀገሯ ዋንጫ በመብላቱ ደስታዋል ለመግለጽ ቲሸርቷን አውልቃ ደስታዋን ስትገልፅ በቴሌቪዥን መታየቷን ተከትሎ በኳታር ፖሊሶች ቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን በኳታር የአለባበስ ደንብ መሰረት ለእስር ሊዳርጋት እንደሚችል ይጠበቃል።
2.1K viewsAnt B, edited  05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 05:39:29
2.2K viewsAnt B, 02:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 21:28:05
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአሜሪካ የነበራቸውን ቆይታ በስኬት አጠናቀው በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ አበባ አቅንተዋል።
1.6K viewsAnt B, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 09:16:41
ቪያግራን ከሀኪም ትዕዛዝ ውጪ መውሰድ ለውስብስብ የጤና ችግሮች ይዳርጋል- የህክምና ባለሙያዎች

በሀኪም ትዕዛዝ ብቻ መሰጠት የሚገባው ቪያግራ በአዲስ አሰበባ በሞተረኞችና በጀብሎ አዟሪዎች በመሸጥ ላይ ነው።

አል ዐይን በመድሀኒት መሸጫ ወይም ፋርማሲ ቤቶች፣ ምሽት ቤቶች፣ ለዚህ ሽያጭ በሚል በተፈጠሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መድሀኒቱ እየተሸጠ እንደሚገኝም ማወቅ ችሏል።

ረዳት ፕሮፌሰር መብራቱ እያሱ፤ ይህ መድሀኒት ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ከተወሰደ ለደም ግፊት፣ ለጡንቻ ህመም፣ ለአይን ህመም፣ ላልተለመደ ውፍረት፣ ለእንቅልፍ መዛባት እና ከልብ ጋር ለተያያዙ ህመሞች ሊዳርግ ይችላልም ይላሉ።
1.2K viewsAnt B, 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ