Get Mystery Box with random crypto!

የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በሚቀጥሉት 40 ዓመታት ለ7 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገለጸ | Skyline media

የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በሚቀጥሉት 40 ዓመታት ለ7 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገለጸ
****
የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በሚቀጥሉት 40 ዓመታት ለ7 ሚሊዮን ዜጎች ፈጠራ ላይ የተመሰረተ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለሥልጣን አስታወቀ።

ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በቀጣይ 40 ዓመታት በአራት ዙሮች በ21 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል በጀት 24 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ዕቅድ መያዙን የባለስልጣኑ ዋና ኃላፊ አቶ ሞቱማ ተመስገን በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ የቀጣይ 40 ዓመታት የመነሻ፣ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ዕቅድ በጀት እና የሥራ ዝርዝር ተቀምጦ ወደ ሥራ መገባቱንም አቶ ሞቱማ አስታውቀዋል።

እንደ አቶ ሞቱማ ገለጻ፣ እ.አ.አ ከ2022 እስከ 2027 የአጭር ጊዜ እቅድ ሲሆን በ3 ቢሊየን ዶላር መነሻ ካፒታል 3 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የመሰረተ ልማት ዝርጋታው ተጀምሯል።