Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.26K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2022-11-29 23:09:25
ውድ ደንበኞቻችን | Ethio-Telecom

"ከሀገር ውጭ በሚገኙ ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመሮች ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎታችን በመጠባበቂያ መስመሮች ብቻ እየሰራ በመሆኑ ከወዲሁ ሊያጋጥም ከሚችል የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ ወይም የፍጥነት መቀነስ ይቅርታ እየጠየቅን፣ አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ከአገልግሎት አቅራቢዎቹ ጋር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ በመሆናችን በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡" - Via:-Ethio-Telecom
 
716 viewsAnteneh Babanto, 20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 10:21:20
በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት በትዊተር ስፔስ
ከኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር ክቡር ዶ/ር አብረሃም በላይ እና ክቡር አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ ጋር
ሀሙስ ህዳር 22, 2015( 1 Dec 2022) በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ በ2 ሰአት ላይ: ከታች ያለውን የትዊተር ሊንክ በመጫን ውይይቱን ይከታተሉ::

Host:- Kiya Negash @KiyaEthiopia
Co-host Poetic @1EthiopiaTekdem
Co-host:- Teddy @Teddykaramara
#DisarmTPLF #Ethiopia

https://twitter.com/kiyaethiopia/status/1596990497905860608?s=46&t=NU6IEPvhciLikJ-txe0-qQ
2.3K viewsAnt B, 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 18:21:11 ፓስፖርት

ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ አስቸኳይ ፓስፖርት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው።

የኢሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን በማንሳት፣ ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ በአስቸኳይ እንዲያገኙ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቅድመ ሁኔታዎች ሲነሱ አሁኑ ላይ አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት ተገልጋዮች ማቅረብ ሚጠበቅባቸውን የሕክምና ደብዳቤ ፣ ነፃ የትምህርት ዕድል ማስረጃ... የመሳሰሉትን ማቅረብ አይጠበቅባቸውም፡፡

በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት በፀደቀው የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ፓስፖርት በአንድና በአምስት ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት የተቀመጠውን ክፍያ " መክፈል የቻለ ሁሉ " ፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆን የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ግንበቶ መናገራቸውን ሪፖርተር ገልጿል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

በአስቸኳይ_ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ለማንሳት ዝግጅት እየተደረገ ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጡ ከሙስናና ከብልሹ አሠራር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው፡፡

- " አስቸኳይ ፓስፖርት ከውስጥ ሠራተኞች ተነጋግረን እናስጨርሳለን " የሚሉ ደላሎች አሉ ከብልሹ አሠራሮች ጋር በተያያዘ ፣ በዓመት ግፋ ቢል ከ50 ሰዎች በላይ እያባረርን ነው። ከአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት ያስችላል ተብሎ የታሰበው መፍትሔ አገልግሎቱን ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማንሳት ነው።

- አሁን ባለው አሠራር ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማግኘት ከሚያስችሉ ማስረጃዎች መካከል ፦

ወደ ውጭ ሄደው መታከም እንዳለባቸው የሚገልጽ የሕክምና ደብዳቤ ፣
  ለሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ የሆነ የትምህርት ዕድል ማግኘትን የሚገልጽ ደብዳቤ

የዲቪ ሎተሪ ዕድል ማግኘትን የሚያሳይ ማስረጃ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተነስተው ሥራ ሲያስጀምር ደንበኞች የሚስተናገዱት በአዲሱ የክፍያ ተመን ይሆናል።

- ቅድመ ሁኔታዎችን አንስቶ አገልግሎቱን ለመጀመር ጥናት ተጠንቷል፤ ይህንን አገልግሎት ለማስጀመር የፓስፖርት ወረቀት ፣ ላምኔት ፣ የማተሚያ ቀለም እና የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ መለዋወጫዎችን ... የመሳሰሉ ግብዓቶች መሟላት እንዳለባቸው በጥናቱ ታይቷል።

የሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት የኦንላይን ፓስፖርት ቡድን መሪ አቶ ዳንኤል የሻነው ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

በአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሰጥባቸው መስኮቶች ሁለት ናቸው የአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎትን ያለገደብ ለማስጀመር እንዲቻል ቢያንስ ስድስት መስኮቶች መኖር አለባቸው።

አገልገሎቱን ለማስጀመር ሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጀምሯል ፤ ምን ያህል ብር እንደሚጠይቅም አዘጋጅተን ለሚመለከተው ክፍል አቅርበናል።

አገልግሎቱ እንዲጀመር ተጨማሪ በጀት ይጠይቃል ፤ በጀቱ የሚፈቀድልን ከሆነ #በቅርብ_ወራት ውስጥ ይኼንን አስጀምረን አገልግሎት አሰጣጡን እናሻሽላለን።

አሁን ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት ክፍያና የሚሻሻለው ክፍያ ምን ይመስላል ?

አሁን በሥራ ላይ ባለው አሠራር መሠረት ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት 2,186 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ ይኼንኑ ፓስፖርት በሁለት ቀናት ውስጥ ለማግኘት 3,279 ብር ክፍያ ይፈጸማል፡፡

በቅርቡ በሥራ ላይ መዋል ይጀምራል የተባለው አዲስ የአገልግሎት ክፍያ ተመን በ5 ቀናት ውስጥ ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት ለማግኘት የሚጠየቀውን ገንዘብ ወደ 5,000 ብር አሳድጎታል፡፡

ፓስፖርቱን በአንድ ቀን ለማግኘት ደግሞ 6,500 ብር ክፍያ መፈጸም እንዳለበት ደንቡ ያስረዳል፡፡

የባለ 64 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ ለማግኘት 6,500 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ በአንድ ቀን ለማግኘት የሚከለፈለው ክፍያ 8,000 ብር ይደርሳል።
ዘገባው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
2.7K views@A, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 07:28:40
የፕሪቶሪያ ስምምነት ቅድመ ሁኔታ የለውም፤ ስለሆነም በስምምነቱ መሠረት ይፈፀማል - #ዶክተር_ለገሰ_ቱሉ

#የፕሪቶሪያ የሠላም ስምምነት ቅድመ ሁኔታ እንደሌለውና በስምምነቱ መሠረት እንደሚፈፀም የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ገለፁ።

ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በማህበራዊ ትስስር ገፅ በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፥ "ፍላጎቶችን ማጣጣም የዴሞክራሲ መርህ ነው" ብለዋል።

ለህዝብና ለህብረ ብሄራዊ አንድነት ሲባል በየዕለቱ መንግስት መስዋዕትነት እየከፈለ መሆኑን አንስተዋል።

"እያንዳንዱ ሰው እንደሚመኘው ሰላምንና ብልፅግናን ማስፈን የመንግስታችን ተቀዳሚ ዓላማ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ፥ "ሰላምን የምናሰፍነው በመርህ እና በህግ ነው" ብለዋል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለሰሜኑ ሀገራችን ክፍል መሠረት መጣሉንም በመግለፅ፥ የናይሮቢው ደግሞ የማስፈጸሚያ መሠረት ማስቀመጡን አመልክተዋል።

"ያለን ብቻኛው አማራጭ ይህንን ማስፈፀም ነው" ብለዋል።

ሁሉንም አሸናፊ ለሚያደርገው መርህ ሁሉም አካል የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣም አሳስበዋል።
1.1K views@A, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 13:15:41
የዉሸት ዶክተር

በሀሰተኛ የሕክምና ት/ት ማስረጃ ተቀጥሮ የሁለት ሰዎች ህይወት ለሞት የዳረገው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በ5 ሺሕ ብር ተቀጣ።
***************************

የጃዊ ሆስፒታል ቅጥር ሰራተኛ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው የሀሰት ዶ/ር ጌትነት ወንድ አወቅ የተባለው ተከሳሽ በድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ሳይማር በሜዲስን የዶክትሬት ዲግሪ እንደተማረ በማስመሰል በሀሰት በተዘጋጀ የዶክትሬት ሰርቲፊኬት የትምህርት ማስረጃ አቅርቧል።

በአብክመ ጤና ቢሮ ከ4/2/2014-4/2/2019 የሚያገለግል የሚል የሀሰት የሙያ ፈቃድ በመያዝ በአብክመ ጤና ቢሮ ሥር ባሉት ሆስፒታሎች በማችንግ ፈንድ ኘሮግራም በ(Junior General Medical practitioner) የቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ ተወዳድሮ 50% በማምጣት በደረጃ 14 ብር 9056 እየተከፈለው ሲሰራም እንደነበር ተገልጿል።

በህክምና የእውቀት ችግር ምክንያት በተፈጠረ ስህተት ሟች የተመኝ አምላክ የተባለችውን የ7 ወር ህፃን እና ሟች የኔወርቅ ደሳለው የተባለችውን የ25 ዓመት ወጣት ለሞት የዳረገ መሆኑምን ተመላክቷል።

በፈፀመው የሙስና ወንጀል መንግሥታዊ ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሀሰት መለወጥ ወይም በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ሙስና ወንጀል በዐ/ህግ ክስ ቀርቦበት በቀን 15/3/2015 ባስቻለው ዳንግላ ተዘዋዋሪ ችሎት በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 5,000 መቀጣቱን ከአዊ ብሔረሰብ ዞን ፍትሕ መምሪያ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
1.2K viewsAnteneh Babanto, 10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 04:11:07 የውጭ ምንዛሪ ጥቁር ገበያ ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ በፍጥነት እያሽቆለቆለ ነው። ከስምምነቱ መፈረም በፊት አንድ የአሜሪካ ዶላር በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ 97 ብር ደርሶ የነበረ ሲሆን ሰሞኑን 95, 92 እያለ ወደ 90 ዳላር ወርዷል። በኢትዮጵያ ያለው የሰላም ሁኔታ እየተሻሻለ ከሄደ የምንዛሪው ዋጋ በቅርቡ ወደ 70 ብር በዶላር ሊደርስ እንደሚችል ይጠበቃል።
632 viewsAnteneh Babanto, 01:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 16:19:26 Breaking : የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬት ዝርፍያ ጋር በተያያዘ ሲያደርገው በቆየው የማጣራት ስራ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ  የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ፤የክ/ከተማ በመሬት ጉዳይ ይወስኑ የነበሩ አመራሮች ፤ ባለሙያዎች ፤ ደላሎችና ከህብረተሰቡ ውስጥ በዚህ ድርጊት የተሳተፉትን  ጨምሮ 37 ሰዎችን በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ   እስካሁን ድረስ 12 ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

ቀሪዎቹን ግለሰቦችም ፖሊስ ክትትል እያደረገባቸው ይገኛል፡፡ ተጨማሪ የማጥራት ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል::
በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦችም:-

1.  ለምለም አባይነህ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ  ወረዳ 4 ዋና ስራ አስፈፃሚ

2.  አቶ ከፍያለው አሰፋ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

3.  አቶ ዋሲሁን ሰውነት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

4.  አቶ ኢብራሂም ሀሰን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

5.  አቶ ሃይለየሱስ ደስታ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

6.  አቶ ዳዊት ከልሌ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ

7.  አቶ ልኡልሰገድ ታደሰ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ

ከመንግስት ተቋማት ውጪ በጉዳዩ ተሳታፊነት በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች

8.  አቶ አየለ ጉቱ

9.  አቶ ጎሳዬ ደሜ

10.  አቶ በፍቃዱ ወንደሰን

11.  አቶ ሮባ ደበሌ

12.  አቶ መታሰቢያ አባተ ናቸው፡፡
1.8K viewsAnt B, 13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 17:27:34 #ሰበር_ዜና

ተጠርጣሪ ሌቦች ተለቀሙ።

በሙስና እና በሀገር ክህደት ወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን የማደኑ ሂደት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ከሀገር ለመውጣት በድንበር በኩል በመሸሽ ላይ የነበሩ በርካታ ተጠርጣሪዎች በብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎትና በድንበር ጠባቂ ሃይሎች ቅንጅት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎች ይዘን እንመለሳለን።

https://t.me/Skyline7777
1.7K viewsAnt B, edited  14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 20:07:00
ማስታወቂያ!
የፓስፖርትና የትውልድ-ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የማውጣት እና የማደስ አገልግሎቶችን ለማግኘት ቀጥሎ የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (link) ይጠቀሙ! https://digitalinvea.com/
1.3K viewsAnt B, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 12:09:49
በአዲስ አበባ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከወሰዱ በኋላ ለረጅም ዓመታት መሬት አጥረው ባስቀመጡ  ባለሃብቶች ይዞታ ላይ ውሳኔ ተላለፈ።

በአዲስ አበባ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከወሰዱ በኋላ ለረጅም ዓመታት መሬት አጥረው ባስቀመጡ  ባለሃብቶች ይዞታ ላይ ውሳኔ መተላለፉን የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነአ ያደታ  ተናግረዋል።

በተወሰደው እርምጃ ከ90 ሄክታር በላይ መሬት መመለሱን ነው ዶክተር ቀንዓ የገለጹት፤

ወደመሬት ባንክ የተመለሰው 90 ሄክታር መሬት በግልፅ ጫረታ ለባለሃብቶች በድጋሚ እንዲተላለፍ አስተዳደሩ ስለመወሰኑም ኃላፊው አንስተዋል።

መሬት ወስደው ግንባታ ቢጀምሩም በሚፈለገው ጊዜ ያላጠናቀቁ 1ሺ200 ፕሮጀክቶች ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ድረስ እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ መቀመጡን ዶክተር ቀንዓ ጨምረው ተናግረዋል።
2.7K viewsAnt B, edited  09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ