Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከወሰዱ በኋላ ለረጅም ዓመታት መሬት አጥረው ባስቀመጡ  ባለሃብ | Skyline media

በአዲስ አበባ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከወሰዱ በኋላ ለረጅም ዓመታት መሬት አጥረው ባስቀመጡ  ባለሃብቶች ይዞታ ላይ ውሳኔ ተላለፈ።

በአዲስ አበባ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከወሰዱ በኋላ ለረጅም ዓመታት መሬት አጥረው ባስቀመጡ  ባለሃብቶች ይዞታ ላይ ውሳኔ መተላለፉን የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነአ ያደታ  ተናግረዋል።

በተወሰደው እርምጃ ከ90 ሄክታር በላይ መሬት መመለሱን ነው ዶክተር ቀንዓ የገለጹት፤

ወደመሬት ባንክ የተመለሰው 90 ሄክታር መሬት በግልፅ ጫረታ ለባለሃብቶች በድጋሚ እንዲተላለፍ አስተዳደሩ ስለመወሰኑም ኃላፊው አንስተዋል።

መሬት ወስደው ግንባታ ቢጀምሩም በሚፈለገው ጊዜ ያላጠናቀቁ 1ሺ200 ፕሮጀክቶች ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ድረስ እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ መቀመጡን ዶክተር ቀንዓ ጨምረው ተናግረዋል።