የሰርጥ አድራሻ:
ምድቦች:
መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች:
49.54K
የሰርጥ መግለጫ
ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777
Ratings & Reviews
Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.
5 stars
3
4 stars
0
3 stars
0
2 stars
0
1 stars
0
የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13
2023-01-02 21:28:03
የኤምፔሪያል ተሻጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ለትራፊክ ክፍት ሆነ
ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መስመር ላይ የሚገኘው የኢምፔሪያል ተሸጋጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል። የተሸጋጋሪ ድልድዩን የግራ ክፍል እና ሌሎች የመንገድ ግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል።
በቦሌ ሚካኤል፣ በኢምፔሪያል እና በለቡ መጋጠሚያ መንገዶች (inter change) ላይ የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ (overpass) እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ ግንባታዎቹን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
ቀደም ሲልም ቦሌ ሚካኤል አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የቀለበት መንገድ ተሸጋጋሪ የትራፊክ ማሳለጫ ድልድይ የግራ ክፍል ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መደረጉ ይታወሳል።
1.6K views@A, 18:28
2023-01-02 10:32:10
ከላይ የሚታየውን ቲክቶክ ፎሎ እንድታደርጉ እጋብዛለሁ።
1.5K viewsAnt B, 07:32
2023-01-02 10:31:30
https://www.tiktok.com/t/ZTRbaLTs9/
1.5K viewsAnt B, 07:31
2022-12-29 23:06:33
የኳስ ንጉሱ ፔሌ በ82 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
‘’የእግር ኳሱ ንጉስ’’ ተብሎ የሚጠራው ብራዚላዊው ኳስ ተጫዋች ፔሌ በ82 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ፔሌ በአለም ዋንጫ ታሪክ ሶስት የዓለም ዋንጫዎችን፣ በ1958፣ 1962 እና በ1970 ከሀገሩ ጋር የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ብቸኛ ባለታሪክ ነው፡፡
ባለፈው አንድ ወር በአንጀት ካንሰር ሳቢያ ህክምና ሲደረግለት የቆየው ፔሌ ባለፈው ሣምንት አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሆነ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘግቡት እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዚህም ኳስ ትታዘዝለታለች የሚባልለት የኳስ ጥበበኛው ፔሌ መትረፍ አልቻለም።
621 viewsAnt B, 20:06
2022-12-29 02:15:02
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ለመሄድ በሁለት ቀን ውስጥ የተመዘገበ የሰው ብዛት 9ሺህ ሲሆን ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት የተመዘገበው የሰው ብዛት ደግሞ 27ሺህ ደርሷል።
2.8K viewsAnt B, 23:15
2022-12-27 09:08:39
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ ነገ ታሕሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መቀሌ መደበኛ በረራ ማድረግ የሚጀምር መሆኑን አስታወቀ ።
5.5K views@A, 06:08
2022-12-26 09:17:18
ሰበር ዜና
በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቀና
***********************
በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቀና።
የልኡካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ነው።
የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል።
በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም ተካትተዋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
400 viewsAnt B, 06:17
2022-12-25 21:14:38
1.3K viewsAnt B, 18:14
2022-12-25 11:44:05
ፖሊስ ተከሳሹን ፈልጎ እንዳጣ ቢናገርም ተከሳሹ ግን በድብቅ ችሎት እየገባ ክሱን አዳምጦ ይወጣ ነበር።
አቢሲኒያ ባንክን የ6.1ሚሊዮን ብር አሳጥተዋል ተብለው በከባድ ሙስና ወንጀል ከተከሰሱ ከ 5 ተከሳሾች መካከል አንደኛ ተከሳሽ አይተንፍሱ እንዳሻው ይባላል።
ይህ ተከሳሽ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ፖሊስ አፈላልጎ እንዲያቀርበው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር።
በመጨረሻም ፖሊስ ተከሳሹን በመኖሪያ አድራሻው አፈላልጎ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጾ መልስ መስጠቱን ተከትሎ ተከሳሹ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግለት ተደርጓል። ከጋዜጣ ጥሪው በኋላ ተከሳሹ በችሎት አለመቅረቡን ተከትሎ በሌለበት መዝገቡ እንዲቀጥል ብይን ተሰጥቶ ነበር።
ይሁንና ግን ተከሳሹ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የችሎቱ ዳኞች በአካል ስለማይለዩት ተደብቆ ችሎት እየገባ ምን እንደተባለ አዳምጦ ሾልኮ ይወጣ ነበር። በዚህ መልኩ ተከሳሹ ተደብቆ ሲገባ አንደኛዋ ተከሳሽ ለፍርድ ቤት ለሚገኙ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር እንዲያውሉት ብትጠቁማቸውም በቁጥጥር ስር ሳያውሉት ቀርተዋል። ተከሳሹም ሳይያዝ ከችሎት ወጥቶ ይሄዳል። ይህንን ሁኔታ ተከሳሿ ለችሎቱ ዳኞች ጥቆማ ሰጥታለች።
የችሎቱ ዳኞች አርብ ዕለት በነበረ ቀጠሮ ጉዳዩን ለማጣራት የተከሳሹ የአክስት ልጅ የሆነ በዚሁ መዝገብ ለቀረበ ግለሰብ ተከሳሹን በሚመለከት ጥያቄ አቅርበዋል።
''በቁጥጥር ስር ያልዋለውን አይተንፍሱ የሚባለው ተከሳሽ እዚህ ሲመጣ አይተኸዋል ወይ?'' ተብሎ የቀረበለት ግለሰብም በበኩሉ ''አዎ አይቼዋለሁ፣ እኔ እንደሚፈለግ አላቅም እንጂ ፍርድ ቤት እየመጣ ተከታትሎ ሲሄድ አይቻለው'' ሲል መልስ ሰጥቷል።
2.8K viewsAnt B, 08:44