Get Mystery Box with random crypto!

ህጋዊ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በኮምፒውተር ሞኒተር ውስጥ ተደብቀው የገቡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና | Skyline media

ህጋዊ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በኮምፒውተር ሞኒተር ውስጥ ተደብቀው የገቡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋለ

በሞጆ ጉምሩክ ህጋዊ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በኮምፒውተር ሞኒተር ውስጥ ተደብቀው የገቡ 100 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ሀርዲስኮች እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ

የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን ሞኒተር ውስጡን ባዶ በማድረግ እና በምትኩ አዳዲስ ላፕቶፖችን እና ሌሎች የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችን በማስገባት እና መልሶ በማሸግ በህገወጥ መንገድ ሊገቡ የነበሩ 100 ላፕቶፖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል

በተገኘው የፍተሻ ውጤት መሰረትም በሰነድ ላይ ያልተገለፀው ዕቃ የቀረጥና ታክስ መጠን ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን አቶ ፈረጃ ጠቁመዋል

የተፈፀመዉ የንግድ ማጭበርበር ተግባር በወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያለው አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ሲሆን በተያዘው እቃ ላይም የውርስ ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑንም ም/ስራ አስሊያጁ አስረድተዋል

አቶ ፈረጃ አክለውም የስሪት ሀገርን ማሳሳት፣ ህጋዊ እቃዎች ሽፋንን በማድረግ ህገወጥ እቃዎችን ማስገባት እና ሌሎች የማጭበርበሪያ ስልቶችን በመጠቀም ከህጋዊ መንገድ ያፈነገጠ ስራ የሚሰሩ አንዳንድ አስመጭና ላኪዎች እንዳሉ ታውቋል

በዚህ መሰረት ባለፉት አምስት ወራት እቃዎች የጉምሩክ ስነ ስርዓት አጠናቀው ለነፃ ዝውውር ከተለቀቁ በኃላ የአስመጭዎችን የህግ ተገዥነት ለማረጋገጥ በድንገተኛ ፍተሻ እና የመረጃ ክፍሎች በተደረጉት የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች በየተለያዩ የማጭበርበሪያ ስልቶችን በመጠቀም መንግስት ሊያጣው የነበረ የቀረጥና ታክስ መጠኑ ከ320 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል፡