Get Mystery Box with random crypto!

የኤምፔሪያል ተሻጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ለትራፊክ ክፍት ሆነ ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መስመ | Skyline media

የኤምፔሪያል ተሻጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ለትራፊክ ክፍት ሆነ

ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መስመር ላይ የሚገኘው የኢምፔሪያል ተሸጋጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል። የተሸጋጋሪ ድልድዩን የግራ ክፍል እና ሌሎች የመንገድ ግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል።

በቦሌ ሚካኤል፣ በኢምፔሪያል እና በለቡ መጋጠሚያ መንገዶች (inter change) ላይ የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ (overpass) እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ ግንባታዎቹን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።

ቀደም ሲልም ቦሌ ሚካኤል አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የቀለበት መንገድ ተሸጋጋሪ የትራፊክ ማሳለጫ ድልድይ የግራ ክፍል ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መደረጉ ይታወሳል።