Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-21 15:19:44
ዜና እረፍት

ታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንስቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሄር ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል፡፡

ዶ/ር ተወልደብርሃን በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ አቅራቢያ ባለችው ‹‹አዲ-ስላም›› የተሰኘች የገጠር መንደር የተወለዱ ሲሆን ፣ በቀለም ትምህርት ገፍተው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1955 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተቀበሉ በኋላ የሁለተኛ እና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከዌልስ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ናቸው፡፡

በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ አገልግሎት የተከበረ ሥም ያላቸው ዶክተር ተወልደ በዘርፉ ላደረጉት ምርምርና በጉዳዩ ዙሪያ ከፍተኛ ግንዛቤ እንዲፈጠር ላደረጉት ጥረት በፈረንጆቹ 2000 Right Livlihood Award ሽልማት አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በፈረንጆቹ 2006 ዓመት የተባበሩት መንግሥታት በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጠውን Champions of the Earth ሽልማት አግኝተዋል፡፡ የተማሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በ1997 የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷቸዋል፡፡

ዶ/ር ተወልደ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ፋኩልቲ ዲን ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ ከ1975 እስከ 1983 በነበረው ዘመን ደግሞ የአስመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላ ለብዙ ዓመታት በሚታወቁበት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡

ዶክተር ተወልደ ገብረእግዚአብሔር የደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ወንድም መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ምንጭ :- ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ
1.8K viewsAnt B, 12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 22:54:12
መምህር ታዬ ቦጋለ በደረሰብህ ጉዳት እጅጉን አዝኛለሁ። እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥህ ፣ከክፉም ይጠብቅህ።

ኃይል የእግዚአብሔር ነው። ክፉ አድራጊዎችም በአሳፋሪ ተግባራችሁ አንገታችሁን ልትደፉ ይገባል።

https://t.me/Skyline7777
576 viewsAnt B, edited  19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 20:24:57
ከነገ ጀምሮ መቶ ሺህ ኩንታል ስንዴ ለአዲስ አበባ ከተማ ይቀርባል

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ #አዳነች_አቤቤ በዛሬው የአዲስ አበበ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት ስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ክብርት ከንቲባዋ ያቀረቡትን ሪፖርት ተከትሎ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የቀረበላቸው ሲሆን፤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኑሮ ውድነቱን ተከትሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም ከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ እየተስተዋለ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ለማቃለል ከተለያዩ አካባቢዎች ምርት ወደ ከተማዋ ለማስገባት የመሀል ደላሎችን በመቆጣጠር ከክልሎች ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህን ተከትሎም ከነገ መጋቢት 06 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ 100 ሺህ ኩንታል ስንዴ ከኦሮሚያ ክልል፤ ከአማራ ክልል ደግሞ ጤፍ በከፍተኛ መሻሻል ወደ ከተማዋ እንደሚገባ ክብርት ከንቲባዋ ገልፀዋል።

ጥሌ-ዘመቂ
1.5K viewsAnteneh Babanto, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 17:56:40 ሰበር ዳጉ...

በህወሓት እጅ የነበሩ ሚሳኢሎችን ጨምሮ ከባድ መሳሪያዎች በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት መከላከያ ሰራዊት ተረክቦ ወደ አዲስአበባ እየተጫኑ ነው።

https://t.me/Skyline7777
1.9K viewsAnt B, edited  14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 17:56:38
2.3K viewsAnt B, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 22:44:11
አንቶኒ ብሊንከን አዲስ አበባ ገቡ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ  ማምሻውን አዲስ አበባ ገቡ።

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ  አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

አንቶኒ ብሊንከን  ኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሠላም ለማሥፈን በተወሰዱ እርምጃዎች እና የጦርነት ማቆም ስምምነቱን ተከትሎ አፈፃፀሙ ላይ እንደሚመክሩም ነው የሚጠበቀው።

በተጨማሪም የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት አጋሮችን እና የሲቪል ማኅበረሰብ አካላትንም በማነጋገር የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ፣ በምግብ ዋስትና እና በሰብዓዊ መብቶች ላይም ይወያያሉ ነው የተባለው።

በተጨማሪም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አንቶኒ ብሊንከን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በኒጀር የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

https://t.me/Skyline7777
274 viewsAnt B, edited  19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 17:02:18
መቀመጫውን ካይሮ ያደረገው የዓረብ ሊግ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል ገለፀች።

የካይሮው ዓረብ ሊግ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እና የውሃ ሙሌትን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ያወጣውን የአቋም መግለጫ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል ገልጻለች፡፡

ሊጉ በትናንትናው ዕለት ለግብጽ አቋም የወገነ መግለጫ ማውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ፥ ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም የሕዳሴ ግድብ የግንባታ ሥራና የውሃ ሙሌትን የማስተዳደር ስራ ለሚመለከታቸው የተፋሰሱ የአፍሪካ ሀገራት ሊተው እንደሚገባ አንስቷል፡፡

ለዓረብ ሊግ የግድቡ ጉዳይ የሚመለከታቸው የተፋሰሱ ሀገራት እንዳሉ ለማስታወስ አንፈልግም ያለው መግለጫው፥ ሊጉ መሰረታዊውን ዓለም አቀፍ ህግ ባላከበረ መልኩ የአንድ ሀገር ቃል አቀባይ ሆኖ እያገለገለ ነው ብሏል፡፡

የአፍሪካ ህብረትም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ መርህን በመከተል ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅን ለማቀራረብ የሶስትየሽ ድርድር ሲያመቻች መቆየቱን የጠቆመው መግለጫው ፥ የሊጉ አካሄድ ስህተት ነው ሲል ኮንኗል፡፡

ግብፅ በዓባይ ወንዝ ዙሪያ በራስ ወዳድነት በምታነሳው የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ድርድሩን ማዘግየቷን መግለጫው አመላክቷል፡፡

ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የድርድር ሂደት በፅኑ እንደሚደግፍ ነው የገለፀው፡፡

በመሆኑም መንግስት በፈረንጆቹ መጋቢት 2015 በኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን መካከል የተፈረመውን የስምምነት አዋጅ በመከተል የግድቡን ግንባታና ውሃ ሙሌት የሚቀጥል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

https://t.me/Skyline7777
2.7K viewsAnt B, edited  14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 13:34:23
ጤናማ የደም ግፊት መጠን ― 120/80
ጤናማ የደም ሥኳር መጠን ― ከ 70 እስከ 120
ጤናማ የልብ ምት በደቂቃ ― ከ 60 እስከ 80
ጤናማ የኮሌስትሮል መጠን በሚሊ-ግራም ― 200
ጤናማ የሰውነት ክብደት ከቁመት ጋር ያለው ንጽጽር (BMI) ― ከ 20 እስከ 25
ሰውነታችን በሳምንት ውስጥ የሚያስፈልገው የእንቅስቃሴ መጠን በደቂቃ ― 150 ደቂቃ
በቀን ውስጥ የሚያስፈልገን የመጠጥ ውሃ መጠን በሊትር ― ከ 2 እስከ 3 ሊትር
በቀን ውስጥ ማግኘት ያለብን የእንቅልፍ ሠዓት ― ከ 7 እስከ 9 ሠዓት

“ጤና ይብዛልዎት”


ሼርርርር
https://t.me/Skyline7777
1.5K views@A, 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 06:31:19
#VRecorder
1.3K viewsAnt B, edited  03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 16:45:12 ሰበር ዜና
ምርጫ ቦርድ በወላይታ ዞን የተደረገው ህዝበ ውሳኔ በድጋሚ እንዲካሄድ ወሰነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በወላይታ ዞን የተደረገው ህዝበ ውሳኔ ምርጫ እና የመራጮች ምዝገባ ውድቅ ተደርጎ ድጋሚ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡ ቦርዱ በዞኑ የተካሄደውን የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ውድቅ ያደረገው፤ “መጠነ ሰፊ” ጥሰቶች በመፈጸማቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡

ምርጫ ቦርድ ይህን ያስታወቀው፤  የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ህዝበ ውሳኔን አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 22፤ 2015 በሰጠው መግለጫ ነው፡፡ በዚሁ መግለጫ ላይ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ፤ አጠቃላይ የህዝበ ውሳኔውን ሂደት እና በወላይታ ዞን የነበረውን ጥሰት በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ በንባብ አሰምተዋል።

ቦርዱ በዛሬ መግለጫው በወላይታ ዞን የተፈጸመው ጥሰት “የምርጫ ሂደቱን ተዓማኒነት እና እውነተኝነት ያሳጣ እና አጠቃላይ የምርጫ ውጤቱንም የሚያዛባ” መሆኑን ገልጿል። አቶ ውብሸት “የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ውድቅ እንዲደረግ እና የመራጮች ምዝገባ እና ድምጽ አሰጣጡም በድጋሚ እንዲደረግ ቦርዱ ወስኗል” ሲሉ የወላይታ ዞን የህዝበ ውሳኔ ሂደትን በተመለከተ የቦርዱን ውሳኔ ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል። 

ከዚህ በተጨማሪም ቦርዱ “ጥሰቶቹን ያስፈጸሙ፣ የፈጸሙ እና የተባበሩ” ያላቸውን አካላት በመለየት ምርመራ እንዲያከናውን እና ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ለምርጫ ቦርድ ሪፖርት እንዲያደርግ ለፌደራል ፖሊስ ደብዳቤ እንዲጻፍ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
1.7K viewsAnt B, 13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ