Get Mystery Box with random crypto!

አንቶኒ ብሊንከን አዲስ አበባ ገቡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ | Skyline media

አንቶኒ ብሊንከን አዲስ አበባ ገቡ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ  ማምሻውን አዲስ አበባ ገቡ።

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ  አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

አንቶኒ ብሊንከን  ኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሠላም ለማሥፈን በተወሰዱ እርምጃዎች እና የጦርነት ማቆም ስምምነቱን ተከትሎ አፈፃፀሙ ላይ እንደሚመክሩም ነው የሚጠበቀው።

በተጨማሪም የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት አጋሮችን እና የሲቪል ማኅበረሰብ አካላትንም በማነጋገር የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ፣ በምግብ ዋስትና እና በሰብዓዊ መብቶች ላይም ይወያያሉ ነው የተባለው።

በተጨማሪም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አንቶኒ ብሊንከን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በኒጀር የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

https://t.me/Skyline7777