Get Mystery Box with random crypto!

መቀመጫውን ካይሮ ያደረገው የዓረብ ሊግ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ ኢትዮጵያ እንደ | Skyline media

መቀመጫውን ካይሮ ያደረገው የዓረብ ሊግ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል ገለፀች።

የካይሮው ዓረብ ሊግ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እና የውሃ ሙሌትን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ያወጣውን የአቋም መግለጫ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል ገልጻለች፡፡

ሊጉ በትናንትናው ዕለት ለግብጽ አቋም የወገነ መግለጫ ማውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ፥ ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም የሕዳሴ ግድብ የግንባታ ሥራና የውሃ ሙሌትን የማስተዳደር ስራ ለሚመለከታቸው የተፋሰሱ የአፍሪካ ሀገራት ሊተው እንደሚገባ አንስቷል፡፡

ለዓረብ ሊግ የግድቡ ጉዳይ የሚመለከታቸው የተፋሰሱ ሀገራት እንዳሉ ለማስታወስ አንፈልግም ያለው መግለጫው፥ ሊጉ መሰረታዊውን ዓለም አቀፍ ህግ ባላከበረ መልኩ የአንድ ሀገር ቃል አቀባይ ሆኖ እያገለገለ ነው ብሏል፡፡

የአፍሪካ ህብረትም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ መርህን በመከተል ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅን ለማቀራረብ የሶስትየሽ ድርድር ሲያመቻች መቆየቱን የጠቆመው መግለጫው ፥ የሊጉ አካሄድ ስህተት ነው ሲል ኮንኗል፡፡

ግብፅ በዓባይ ወንዝ ዙሪያ በራስ ወዳድነት በምታነሳው የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ድርድሩን ማዘግየቷን መግለጫው አመላክቷል፡፡

ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የድርድር ሂደት በፅኑ እንደሚደግፍ ነው የገለፀው፡፡

በመሆኑም መንግስት በፈረንጆቹ መጋቢት 2015 በኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን መካከል የተፈረመውን የስምምነት አዋጅ በመከተል የግድቡን ግንባታና ውሃ ሙሌት የሚቀጥል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

https://t.me/Skyline7777