Get Mystery Box with random crypto!

ከነገ ጀምሮ መቶ ሺህ ኩንታል ስንዴ ለአዲስ አበባ ከተማ ይቀርባል የአዲስ አበባ ከተማ መስተ | Skyline media

ከነገ ጀምሮ መቶ ሺህ ኩንታል ስንዴ ለአዲስ አበባ ከተማ ይቀርባል

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ #አዳነች_አቤቤ በዛሬው የአዲስ አበበ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት ስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ክብርት ከንቲባዋ ያቀረቡትን ሪፖርት ተከትሎ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የቀረበላቸው ሲሆን፤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኑሮ ውድነቱን ተከትሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም ከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ እየተስተዋለ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ለማቃለል ከተለያዩ አካባቢዎች ምርት ወደ ከተማዋ ለማስገባት የመሀል ደላሎችን በመቆጣጠር ከክልሎች ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህን ተከትሎም ከነገ መጋቢት 06 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ 100 ሺህ ኩንታል ስንዴ ከኦሮሚያ ክልል፤ ከአማራ ክልል ደግሞ ጤፍ በከፍተኛ መሻሻል ወደ ከተማዋ እንደሚገባ ክብርት ከንቲባዋ ገልፀዋል።

ጥሌ-ዘመቂ