Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ሁሉም ወደ ዩንቨርስቲ | Skyline media

ሰበር ዜና

የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ሁሉም ወደ ዩንቨርስቲ መግባታቸውን አረጋገጡ።

ከተመሰረተበት ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ ብቁ እና ተወዳዳሪ ትውልድ እያፈራ ያለው የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ዘንድሮም ይህንኑ ታሪክ ደግሟል።

የዘንድሮውን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከተፈተኑ 75 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የዘንድሮ ከፍተኛ ውጤትም 643 ሆኖ ተመዝግቧል።

አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን በትምህርት ቤቱ ደረጃ የአንድ ተማሪ ውጤት ብቻ  378 ዝቅተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን ከትምህርት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዘንድሮ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ከተፈተኑ 980ሺህ ተማሪዎች መካከል 28ሺህ ብቻ ወደ ዩንቨርስቲ የሚያስገባ ውጤት ማምጣታቸውን ዘገባን ነበር።

   #በተገኘውም ውጤት እንኳን ደስ ያላችሁ
https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777