Get Mystery Box with random crypto!

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ የተዋቀ | Skyline media

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ የተዋቀረው ከህወሓት፣ ከትግራይ ኃይሎች፣ ከምሁራን እና ከባይቶና ፖለቲካ ፓርቲ ነው።

የካቢኔው 51 በመቶ ቦታ የተያዘው በህወሓት ሲሆን፤ ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ሁለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል አግኝቷል።

የካቢኔው አባላት ፦

ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ - ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሰላምና ጸጥታ ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ - በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታዜይሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

አቶ በየነ ምክሩ - የኢኮኖሚ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ዶ/ር ሓጎስ ጎደፋይ - የእቅድ፣ ገቢና የሀብት አስተዳደር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት - የማህበራዊ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ወ/ሮ ያለም ጸጋይ - የመሰረት ልማት ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ብ/ ጄነራል ተኽላይ አሸብር - የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

ዶ/ር አልጋነሽ ተሰማ - የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ስልጠና ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

አቶ አማኑኤል አሰፋ - ቺፍ ካቢኔ ሴክሬተሪያት

ዶ/ር እያሱ አብርሃ – የእርሻ ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር ገብረህይወት ዓገባ - የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሞገስ ገብረእግዚአብሄር - የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

አቶ ታደለ መንግስቱ - የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ ምሕረት በየነ – የፋይናንስና ሀብት ማስተባበር ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር አማኑኤል ሃይለ – የጤና ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሓድሽ ተስፋ - የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ

ሌ/ጄነራል ፍስሃ ኪዳኑ ፋንታ – የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር ከላሊ አድሃና – የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሓይሽ ሱባጋዳስ - የወጣቶች ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ ገነት አረፈ – የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ

ሜ/ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ - የማህበራዊ ጉዳይ እና መልሶ ማቋቋም ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ አልማዝ ገብረጻድቅ – የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ ፈለጉሽ አሳምነው – የመሬት እና ማዕድን ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ ፍረወይኒ ገብረእግዚአብሄር – የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

ዶ/ር አጽብሃ ገብረእግዚአብሄር - የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

በሌላ በኩል ፤ አዲሱ የጊዜያዊ አስተዳደር ከቀድሞው አስተዳደር ጋር ዛሬ መቐለ ውስጥ ርክክብ አድርጋል።

መረጃው የ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር "  እና " ትግራይ ቴሌቪዥን " ነው።