Get Mystery Box with random crypto!

Muktarovich Ousmanova

የሰርጥ አድራሻ: @muktarovichousmanova
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 63.61K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia forever

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2024-03-23 13:12:45
እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ የላከችው ይህን አምባሳደር፣ የኢትዮጵያ መንግስት አልቀበላቸውም ማለቱ ተሰማ።

ምክንያት በጎንደር አከባቢ በፈላሾች ቤት ተቃጠለ የሚል በቪድዮ የተሰራጨ ስም ማጥፋት ላይ ተሳታፊ ነበሩ የሚል ነው።
17.4K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-23 10:25:56
ስልክዎትን ለመቀየር ወይም አዲስ ለመግዛት አስበዋል ?

  አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

https://t.me/sellphone2777

0929008292

inbox @bina27

አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ

ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
17.9K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 20:11:06
በትግራይ ጦርነት “ምርኮኞች ነበሩ” የተባሉ 112 የመከላከያ ሰራዊት አባላት “በምህረት” ተለቀቁ

በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት “ተማርከው ነበር” የተባሉ 112 የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት፤ በዛሬው ዕለት “በምህረት” መፈታታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ። በዛሬው ፍቺ ያልተካተቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጉዳይም “በአጭር ጊዜ ውስጥ” መፍትሔ እንደሚያገኝም አስተዳደሩ ገልጿል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ፤ የፌደራል መንግስት እና የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በጥቅምት 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ከመፈራረማቸው በፊት የተማረኩ መሆናቸውን የትግራይ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ከ16 ሺህ በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መለቀቃቸውን ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አስታውሷል።

ዛሬ አርብ መጋቢት 13፤ 2016 የተለቀቁት የመከላከያ ሰራዊት አባላት፤ “በከባድ ወንጀል” ተጠርጥረው “በቁጥጥር ስር የቆዩ” መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለእነዚህ የሰራዊት አባላት “ምህረት” ያደረገው፤ የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተደረገ ውይይት ላይ “በተደረሰው መግግባት” መሆኑንም አክሏል።

* ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/12815/

@EthiopiaInsiderNews
19.2K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 13:30:52
ማሳሰቢያ
በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ክፍለከተሞች እና ወረዳዎች ውሃ በከፊል ስለሚቋረጥ ቅድመ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ስለማሳሰብ
#አዩዘሀበሻ
ነገ ቅዳሜ መጋቢት 14 እና እሁድ መጋቢት 15 እንዲሁም ከመጪው ሳምንት ቅዳሜ መጋቢት 21 እና እሁድ መጋቢት 22 በለገዳዲ የሚገኘው የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ አጠባ ስለሚከናወን በሚከተሉት ክፍለከተሞች
በየካ ክፍለከተማ ከወረዳ 1-13
በቂርቆስ ክፍለከተማ ከወረዳ 1-8
በአራዳ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 1-10
በጉለሌ ክፍለከተማ ከወረዳ 1-10
በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 1፣2፣4፣6፣7፣11
በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 3፣5፣8፣9
እና 10
በልደታ ክፍለከተማ ወረዳ 5፣6፣7፣9 በከፊል ውሃ ስለሚቋረጥ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ማለቱን አዩዘሀበሻ ከከተማው ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ያገኘው መረጃ ያሳያል(አዩዘሀበሻ)።
ጥቆማ
በዚህ የቴሌግራም ቻናል ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያግኙ፣ከስር ባለው ሊንክ join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
19.7K views10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 13:20:09
በጦርነት ሳቢያ ሥራ አቋርጦ የቆየው የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ መመለሱ ተገለጸ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ምርት ሂደት መመለሱን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑን ዋና ስራ አስፈጽሚ ዋቢ ያደርገውን ዘገባ አዲስ ማለዳ የተመለከተች ሲሆን በሰሜኑ ግጭት ምክንያት ሥራ አቋርጦ የቆየው የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በከፍተኛ ርብርብ ዛሬ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል።

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ከዚህ ቀደም ያመርቱ የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እና አዳዲስ ኢንቨስተሮች እንዲገቡ ጥሪ ቀርቧል።

የቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎቻቸውን እያጠናቀቁ የሚገኙ አልሚዎች መኖራቸውን ያስታወቀው ኮርፖሬሽኑ፤ ኩባንያዎቹ ወደ ምርት ሂደት እንዲገቡ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ238 ሄክታር መሬት ላይ ተገንብቶ በፈረንጆች 2017 ሥራ የጀመረ ሲሆን 15 የማምረቻ ሼዶች እና የለማ መሬት ይገኝበታል።
18.9K views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 09:56:20
ጽዱና ውብ ከተማ እንገነባለን። ባጃጅ ከከተማ እናስወጣለን። የብስክሌት መጓጓዣ እንሰራለን። የቤት ተሽከርካሪ በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት እናግዳለን ...

A few moment later ...

"የአህያና የፈረስ ጋሪዎችን በማዘመን እንደ ትራንስፓርት አማራጭ እንጠቀማለን።"

ጎበዝ አህያና ፈረስ ሲዘምኑ ወደ ምን ይቀየሩ ይሆን ? ሞተር ይገጠምላቸው ይሆን ? በፀሐይ ሃይል ይሰሩ ይሆን። መቼስ ዘንድሮ ተአምራቱ ብዙ ነው።

ጆሮ በር የለው፣ አልሰማ አይልም
18.5K views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-21 19:09:26
በሳውዲ አረቢያ ወህኒ ለበርካታ ወራት በሶቃይና እንግልት የከረሙ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራው ሊጀመር መሆኑን ውጭ ጉዳይ አሳወቀ
19.5K views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-21 18:10:37
ስልክዎትን ለመቀየር ወይም አዲስ ለመግዛት አስበዋል ?

  አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

https://t.me/sellphone2777

0929008292

inbox @bina27

አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ

ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
19.7K views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-21 12:13:14
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በድጋሜ የድርድር ጥሪ አቀረበ

"የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ያለበት ተጨባጭ የትግል ምዕራፍ ለትጥቅ ትግል የሚያነሳሳም አይደለም" ሲል የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ሕዝብ ሲታገልላቸው የነበሩ "ዋና ዋና ጥያቄዎች" ተመልሰዋል ብሎ የቀሩትም በሂደት እየተፈቱ ይገኛሉ ሲል አስታውቋል።

"ከለውጡ" ወዲህ የትላንቱን የፖለቲካ ኋላ ቀርነት ለማስወገድ እና ሰላምን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ያለው የክልሉ መንግስት፤ የሰላም በሮችን ክፍት አድርጓል ማለቱን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።

"የተለያዩ አካላት ነጠላ ትርክት እየተከተሉ የትናንቱ ኋላ ቀርነት አብሮን እንዲቀጥል እየሠሩ ነው" ያለው መግለጫው፤ እስካሁን ከ3 ሺህ 500 በላይ "የሸኔ" ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ ተቀብለው 1 ሺህ 500 የሚሆኑት ተዋጊዎች የመልሶ ማቋቋም ስልጠና ወስደው ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቅለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ በመግለጫው "ለኦሮሞ ሕዝብ የሚበጀው የተገኘውን ድል ተባብሮ በመጠበቅ ለተሻለ ነገ በሕብረት መሥራት እንጂ እርስ በርስ መፋለም እና መጠፋፋት አይደለም" ብሎ መጠፋፋትና መጠላለፍ "እንደአገር ያገኘነውን ድል" ለማስቀጠል ፈተና ሆኗል ብሏል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራ ውስጥ ከስድስት ዓመታት ገደማ በፊት የተፈራረሙት ስምምነትን ተከትሎ ወደ አገር ወስጥ የገባው ታጣቂ ቡድን ወደ ኦሮሚያ ክልል ከገባ በኋላ ላለፉት ዓመታት የግጭት ቀጠና ሆኗል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)ን ጨምሮ ሌሎችም የፖለቲካ ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ያላባራ እና ያልተቋረጠ በመሆኑ ከፍተኛ ውድመት እና የሰው ህይወት መጥፋት እያስከተለ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገልጻሉ።
15.2K views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-21 10:57:44
በትግራይ ፤ የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) ለሚለግሱ ሰዎች 10ሺ ብር ስጦታ ይሰጣል ተባለ

'አዶ' በሚል ስም እሚታወቅ አንድ የግል የህክምና ማዕከል በተፈጥሮአዊ መንገድ ፅንስ ለመቋጠር ላልቻሉት ልጅ እእዲኖራቸው ለማድረግ እየሰራሁት ነው ባለው ስራ ሴት እንስቶች 'እንቁላል' ወንዶች ደግሞ 'የዘር ፍሬ (ስፐርም) እንዲለግሱ ጥሪውን አቅርቧል።

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ መቀመጫውን ያደረገው 'አዶ' የእናቶች፣ ሕጻናት እና የነቃ ሕይወት ሕክምና ማዕከል ይህንን ሕክምና ለመስጠት ዝግጅት የጀመረው ከትግራይ ጦርነት በፊት እንደሆነና ህክምናውን ለመጀመር የተደረገው ጥረት በጦርነቱ ምክንያት ቢቋረጥም ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ግን ሂደቱ መቀጠሉን ይገለፃል።

ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት ታድያ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በመከወን ስፐርም እና እንቁላል ለመለገስ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን እየጠበቀ ነውም መባሉን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

የወንድ ዘር ለጋሾች የዘር ፍሬያቸው መጠን ከ 1.5 ሚ/ሊ በላይ መሆን አለበት፣በአንድ ሚ/ሊ ስፐርም ውስጥ ከ15 ሚሊዮን በላይ የወንድ የዘር ህዋስ (sperm cells) መኖር አለበት በተጨማሪም ለጋሾች ለኤችአይቪ፣ ለሄፐታይተስ ቫይረስ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ምርመራ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል።

እንቁላል ለሚለግሱ ሴቶች የእድሜ ገደብ እንዳለና እንቁላል ለመለገስ ብቁ የሆኑ ሴቶች በ 20 እና 30 አመት መካከል ናቸው በተጨማሪም ሴት ለጋሾች ቀደም ብለው የወለዱ መሆን አለባቸው ይላሉ ዶ/ር ሳምሶን። ይህ መስፈርት የተቀመጠው ለምን እንደሆነ ሲገልጹም “[የወለዱ ሴቶች] እንቁላሎቻቸው ተፈትነዋል ብለዋል።

የዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው
15.7K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ