Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ፤ የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) ለሚለግሱ ሰዎች 10ሺ ብር ስጦታ ይሰጣል ተባለ 'አዶ | Muktarovich Ousmanova

በትግራይ ፤ የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) ለሚለግሱ ሰዎች 10ሺ ብር ስጦታ ይሰጣል ተባለ

'አዶ' በሚል ስም እሚታወቅ አንድ የግል የህክምና ማዕከል በተፈጥሮአዊ መንገድ ፅንስ ለመቋጠር ላልቻሉት ልጅ እእዲኖራቸው ለማድረግ እየሰራሁት ነው ባለው ስራ ሴት እንስቶች 'እንቁላል' ወንዶች ደግሞ 'የዘር ፍሬ (ስፐርም) እንዲለግሱ ጥሪውን አቅርቧል።

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ መቀመጫውን ያደረገው 'አዶ' የእናቶች፣ ሕጻናት እና የነቃ ሕይወት ሕክምና ማዕከል ይህንን ሕክምና ለመስጠት ዝግጅት የጀመረው ከትግራይ ጦርነት በፊት እንደሆነና ህክምናውን ለመጀመር የተደረገው ጥረት በጦርነቱ ምክንያት ቢቋረጥም ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ግን ሂደቱ መቀጠሉን ይገለፃል።

ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት ታድያ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በመከወን ስፐርም እና እንቁላል ለመለገስ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን እየጠበቀ ነውም መባሉን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

የወንድ ዘር ለጋሾች የዘር ፍሬያቸው መጠን ከ 1.5 ሚ/ሊ በላይ መሆን አለበት፣በአንድ ሚ/ሊ ስፐርም ውስጥ ከ15 ሚሊዮን በላይ የወንድ የዘር ህዋስ (sperm cells) መኖር አለበት በተጨማሪም ለጋሾች ለኤችአይቪ፣ ለሄፐታይተስ ቫይረስ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ምርመራ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል።

እንቁላል ለሚለግሱ ሴቶች የእድሜ ገደብ እንዳለና እንቁላል ለመለገስ ብቁ የሆኑ ሴቶች በ 20 እና 30 አመት መካከል ናቸው በተጨማሪም ሴት ለጋሾች ቀደም ብለው የወለዱ መሆን አለባቸው ይላሉ ዶ/ር ሳምሶን። ይህ መስፈርት የተቀመጠው ለምን እንደሆነ ሲገልጹም “[የወለዱ ሴቶች] እንቁላሎቻቸው ተፈትነዋል ብለዋል።

የዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው