Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በድጋሜ የድርድር ጥሪ አቀረበ 'የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ያለበት ተጨባጭ | Muktarovich Ousmanova

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በድጋሜ የድርድር ጥሪ አቀረበ

"የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ያለበት ተጨባጭ የትግል ምዕራፍ ለትጥቅ ትግል የሚያነሳሳም አይደለም" ሲል የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ሕዝብ ሲታገልላቸው የነበሩ "ዋና ዋና ጥያቄዎች" ተመልሰዋል ብሎ የቀሩትም በሂደት እየተፈቱ ይገኛሉ ሲል አስታውቋል።

"ከለውጡ" ወዲህ የትላንቱን የፖለቲካ ኋላ ቀርነት ለማስወገድ እና ሰላምን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ያለው የክልሉ መንግስት፤ የሰላም በሮችን ክፍት አድርጓል ማለቱን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።

"የተለያዩ አካላት ነጠላ ትርክት እየተከተሉ የትናንቱ ኋላ ቀርነት አብሮን እንዲቀጥል እየሠሩ ነው" ያለው መግለጫው፤ እስካሁን ከ3 ሺህ 500 በላይ "የሸኔ" ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ ተቀብለው 1 ሺህ 500 የሚሆኑት ተዋጊዎች የመልሶ ማቋቋም ስልጠና ወስደው ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቅለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ በመግለጫው "ለኦሮሞ ሕዝብ የሚበጀው የተገኘውን ድል ተባብሮ በመጠበቅ ለተሻለ ነገ በሕብረት መሥራት እንጂ እርስ በርስ መፋለም እና መጠፋፋት አይደለም" ብሎ መጠፋፋትና መጠላለፍ "እንደአገር ያገኘነውን ድል" ለማስቀጠል ፈተና ሆኗል ብሏል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራ ውስጥ ከስድስት ዓመታት ገደማ በፊት የተፈራረሙት ስምምነትን ተከትሎ ወደ አገር ወስጥ የገባው ታጣቂ ቡድን ወደ ኦሮሚያ ክልል ከገባ በኋላ ላለፉት ዓመታት የግጭት ቀጠና ሆኗል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)ን ጨምሮ ሌሎችም የፖለቲካ ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ያላባራ እና ያልተቋረጠ በመሆኑ ከፍተኛ ውድመት እና የሰው ህይወት መጥፋት እያስከተለ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገልጻሉ።