Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ጦርነት “ምርኮኞች ነበሩ” የተባሉ 112 የመከላከያ ሰራዊት አባላት “በምህረት” ተለቀቁ | Muktarovich Ousmanova

በትግራይ ጦርነት “ምርኮኞች ነበሩ” የተባሉ 112 የመከላከያ ሰራዊት አባላት “በምህረት” ተለቀቁ

በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት “ተማርከው ነበር” የተባሉ 112 የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት፤ በዛሬው ዕለት “በምህረት” መፈታታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ። በዛሬው ፍቺ ያልተካተቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጉዳይም “በአጭር ጊዜ ውስጥ” መፍትሔ እንደሚያገኝም አስተዳደሩ ገልጿል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ፤ የፌደራል መንግስት እና የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በጥቅምት 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ከመፈራረማቸው በፊት የተማረኩ መሆናቸውን የትግራይ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ከ16 ሺህ በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መለቀቃቸውን ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አስታውሷል።

ዛሬ አርብ መጋቢት 13፤ 2016 የተለቀቁት የመከላከያ ሰራዊት አባላት፤ “በከባድ ወንጀል” ተጠርጥረው “በቁጥጥር ስር የቆዩ” መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለእነዚህ የሰራዊት አባላት “ምህረት” ያደረገው፤ የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተደረገ ውይይት ላይ “በተደረሰው መግግባት” መሆኑንም አክሏል።

* ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/12815/

@EthiopiaInsiderNews