2022-05-14 12:24:22
2. የቢቢሲ ክስ!!!
ሰሞኑን ትህነግ በአፈ ቀላጤው ሉሲ ካሳ በኩል ዓለም ላይ ይፈጠራል ተብሎ የማይታሰብ ክስ በአማራ መንግስትና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ላይ መስርቶ ቢቢሲ ላይ አትሟል:: ይህንን አደገኛ ክስ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አላየውም ብየ ማሰብ ይቸግረኛል:: ስራው ምን ሆኖ ላያየው ይችላል ብዬ ልጠርጥር ? ሆኖም ጠንካራ ምላሽ ይሰጣል ብዬ ጠብቄ ነበር:: ተቋሙ ግን እንደተኛ ነው:: እጅግ ያሳዝናል:: ዝምታው ክሱን ተቀብለነዋል የሚል መልዕክት ያስተላልፋል ብዬ አምናለሁ::
. የቢቢሲ ክስ!!!
ሰሞኑን ትህነግ በአፈ ቀላጤው ሉሲ ካሳ በኩል ዓለም ላይ ይፈጠራል ተብሎ የማይታሰብ ክስ በአማራ መንግስትና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ላይ መስርቶ ቢቢሲ ላይ አትሟል:: ይህንን አደገኛ ክስ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አላየውም ብየ ማሰብ ይቸግረኛል:: ስራው ምን ሆኖ ላያየው ይችላል ብዬ ልጠርጥር ? ሆኖም ጠንካራ ምላሽ ይሰጣል ብዬ ጠብቄ ነበር:: ተቋሙ ግን እንደተኛ ነው:: እጅግ ያሳዝናል:: ዝምታው ክሱን ተቀብለነዋል የሚል መልዕክት ያስተላልፋል ብዬ አምናለሁ::
3. የኦፌኮ እንቶ ፈንቶ ውንጀላ !!
በእርግጥ የኦፌኮን የጃጀና የውስጥን ፍርሃት ፈንቅሎ የወጣ መግለጫ ማንም ሚዛናዊ አዕምሮ ያለው ሰው ከመዝናኛነት ያለፈ ትርጉም ሊሰጠው እንደማይችል እገምታለሁ:: ነገር ግን ራሱን ኦፌኮን የመሰሉ የተወራው ሁሉ እውነት የሚመስላቸው አይኖሩም ማለት ደግሞ አይቻልም:: እናም እንደእዚህ አይነት ብዥታዎች ሲፈጠሩ የኮሙኒኬሽኑ ቢሮ ፈጥኖ ማረቅ ስራው ይመስለኛል:: እስካሁን ባለኝ መረጃ ምንም አላለም:: ያው ዝምታ መስማማት በመሆኑ ተቀብየዋለሁ አይነት እንድምታ እያስተላለፈ ይመስላል::
4. የኦሮሚያ መንግስት መግለጫ
ከሳምንታት በፊት የኦሮሚያው መንግስት አደገኛ መግለጫ መስጠቱን እናስታውሳለን:: መግለጫውን ከአንዴም ሁለት ጊዜ ደግመውታል:: በአማራው በኩል ይህንን ለማረም ትንፍሽ አልተባለም:: ኮሙኒኬሽን ተቋሙ የት ነው ያለው ?
5. በትህነግ ስር ያሉ አካባቢዎች
እንደሚታወቀው በራያ: ዋግ እና ሰሜን ጎንደር ብዙ አካባቢዎች አሁንም በትህነግ ቁጥጥር ስር ናቸው:: ስለእነዚህ አካባቢዎች ርሃብና እንግልት የክልሉ ኮሙኒኬሽን ምን መረጃ ሰጥቶን ያውቃል? በእገታ ላይ ከመሆናቸው በላይ እናንተ ተርባችሁ የእኔን ወታደር መግቡ እየተባሉ ሲኦልን በምድር እያሳለፉ ይገኛሉ:: ይህ አጀንዳ እንዲታወቅ የማድረግ ስራው የኮሙኒኬሽኑ አልነበረም ወይ ?
6. የትግራይ ተፈናቃዮች
የትግሬ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል ያደረሰው ግፍ በትውልድ ይቅር የማይባል ነው:: ወራሪ ቡድኑ ያቆሰላቸው እናቶች ቁስላቸው ሳይደርቅ ግን የትግራይ ህዝብ "እርቦኛል: እናም ከአማራ ወንድሜና እህቴ ጋር ተካፍየ እበላለሁ" ብሎ ወደክልሉ እየጎረፈ ነው:: ሰብአዊነት እሴቱ የሆነው የአማራ ህዝብም እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ ያለውን አካፍሎ እያበላቸው ይገኛል:: ልጆቻችሁ እንዲህ አድርገውኝ እናንተን አልቀበልም ወይም ልበቀላችሁ አላለም:: ተፈጥሮው አይደለምና:: ከእዚህ በላይ ሰብአዊነት የትም አይኖርም:: ይህ ግን ጥቂቶች የምናውቀው እውነታ ብቻ ሆኖ ተደብቋል:: ለምን? የኮሙኒኬሽን ቢሮው ስራውን በአግባቡ ባለመስራቱ:: የአገር ውስጥም የውጭም ጋዜጠኞችን ጋብዞ ይህንን ሃቅ ለአለም ማሳወቅ ግዴታው አልነበረም ወይ ?? አሁንም አልረፈደም !!
7. አጀንዳ ማውጣት
የክልሉን የልማት: የመልካም አስተዳደር: የፀጥታ ሁኔታን በተመለከተ እስከቀበሌ ድረስ ባሉት መዋቅሮቹ አጀንዳ ቀርፆ ህዝብን ማወያየትና ያደገ የህዝብ ተግባቦት መፍጠር ተቀዳሚ ሃላፊነቱ ነበር:: ነገር ግን ሲሰራ አላየሁም:: በእርግጥ የሚሰጠውን አጀንዳ በአግባቡ ተንትኖ አጥጋቢ ምላሽ የማይሰጥ እንቅልፋም ተቋም የራሱን አጀንዳ እንደማይቀርፅ ግልፅ ነው::
8. የትግራይ ሰራዊት ለዳግም ጥፋት መጠነ ሰፊ ዝግጅቶች እያደረጉ እንደሆነ ይሰማል(ትንኮሳም ሞክረዋል) ። ነገር ግን የእኛን ህዝብ ዝግጁ እንዲሆን በማንቃት ረገድ እና ወቅታዊ መረጃ በመስጠት ረገድ የተቋሙ ስራ አይደለም ወይ ?
እንደመውጫ: ብዙ ሙያተኞች (እኔን ጨምሮ) እንደእዚህ አይነት ክፍተቶችን መጠቆማችን መልካም ነው:: ከእዚህ በዘለለ በተግባር የምታግዙ ሰዎች ካላችሁ ደግሞ የድርሻችሁን ብትወጡ መልካም ነው እላለሁ::
ተቋሙ ነቃ እንዲል በቀናነት የተወረወረ ሀሳብ ነው !!
Tesfaye Woldesilassei እንደፃፈው
8.2K views09:24