Get Mystery Box with random crypto!

በጦርነት ሳቢያ ሥራ አቋርጦ የቆየው የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ መመለሱ ተገለጸ የኢንዱስ | Muktarovich Ousmanova

በጦርነት ሳቢያ ሥራ አቋርጦ የቆየው የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ መመለሱ ተገለጸ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ምርት ሂደት መመለሱን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑን ዋና ስራ አስፈጽሚ ዋቢ ያደርገውን ዘገባ አዲስ ማለዳ የተመለከተች ሲሆን በሰሜኑ ግጭት ምክንያት ሥራ አቋርጦ የቆየው የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በከፍተኛ ርብርብ ዛሬ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል።

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ከዚህ ቀደም ያመርቱ የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እና አዳዲስ ኢንቨስተሮች እንዲገቡ ጥሪ ቀርቧል።

የቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎቻቸውን እያጠናቀቁ የሚገኙ አልሚዎች መኖራቸውን ያስታወቀው ኮርፖሬሽኑ፤ ኩባንያዎቹ ወደ ምርት ሂደት እንዲገቡ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ238 ሄክታር መሬት ላይ ተገንብቶ በፈረንጆች 2017 ሥራ የጀመረ ሲሆን 15 የማምረቻ ሼዶች እና የለማ መሬት ይገኝበታል።