Get Mystery Box with random crypto!

ABX

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX A
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedseidabx — ABX
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedseidabx
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.70K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 64

2021-01-31 11:23:37 ያቺን አንዲት ፍሬ የት እንደዘራህ ረስተህ ሊሆን ይችላል፡፡ ግና ከቀናት ቆይታ በኋላ ዝናብ ያበቅላትና ቦታዉን  ይጠቁምሃል፡፡ ሁሌም በየትኛዉም ሁኔታና አካባቢ ላይ፤ እንዲሁም ለማንኛዉም ሰው መልካምን መዝራት ቢቆይም ፍሬ አለው፡፡ ስለሆነም ሰዎች “መልካሙ” ብለው እስኪያውቁህ ድረስ በመልካምነትና መልካምን በመዝራት ታወቅ፡፡
ግዴለህም ሳታመነታ ቦታ ሳትመርጥ ዝራ፡፡ መልካምነት የትም ብትዘራው ይበቅላል፡፡ ያ ዘር መቼ እና የት ፍሬ አፍርቶ እንደሚጠብቅህ አታውቅምና፡፡ የተቸገሩትን መርዳት፣ ለተጨነቁት መፍትሄ ብትጠቁም ምንዳዉን በዚሁ ምድር ላይ ታያለህ፤ አሊያም ወደፊት ቀድሞህ በአኺራህ የሚጠብቅህ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡

ወዳጆቼ የምድር ላይ ዕድሜያችን ከምናስበው በላይ አጭር ናት፡፡ ከቶ የአንድንም ሰው ደስታ አትስረቁ፤ የአንድንም ሰው ተስፋ አትንጠቁ፡፡


http://t.me/MuhammedSeidABX
1.2K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-31 10:23:56

986 views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-29 16:28:35 ያ ረብ!

ማለት ብቻዉን በቂ ነው።

ያ ረብ !
ሰፊ እና ጥልቅ ትርጉም አለው።

እስቲ ያ ረብ! በሉ በረጅሙ ተንፍሱ።
1.9K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-29 15:53:53 ከኢስቲግፋር ጋር
ሲሳይ፣
ምህረት፣
ዕውቀት ፣
ስኬት፣
እፎይታ ፣
እርካታ፣
እርጋታ፣
ደስታ ... አለ።
መልካም ጁምዓ ይሁንላችሁ ።

https://t.me/NejashiPP
1.3K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-29 09:22:31 ሰው ሲሞት ገላ አፈር ዉስጥ ይቀበራል።
ሩሕ ግን ወደ ሰማይ ትወጣለች።

ከነፍስ በላይ ሥጋ ከፍ ያለ ዋጋ ቢኖረው ኖሮ ሥጋ መሬት ዉስጥ ባልተቀበረ
ነፍስም ወደ ሰማይ ባልተወሰደች ነበር ።


ለነፍሳችን ትልቅ ትኩረት እንስጥ።

ጁምዓ ሙባረክ !

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.5K viewsedited  06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-28 19:38:08 ተራና ድሃ ሰው ነው ብለህ ብታስብ እንኳ እንግዳህን አክብር፤
አሚር ብትሆንም እንኳ ለአስተማሪህ እና ለወላጆችህ ተነስ።

ይላሉ ዐሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ

http://t.me/MuhammedSeidABX
1.2K views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-28 19:29:06 ከሐሰን አል-በስሪ ንግግሮች (ረሒመሁላህ/አላህ ይዘንለት

1- አማኝ አውቆ አያጠፋም፡፡ ሌሎች ያጠፉበት እንደሆነም ታጋሽ ነው፡፡ አይበድልም፤ የበደሉት እንደሆነም ይቅር ባይ ነው፡፡ አይሰስትም ከስስታሞች አንፃርም ታጋሽ ነው፡፡

2- አንዳንድ ሰዎች አንድም መልካም ነገር ሳይኖራቸው ይህችን ዓለም እስኪለቁ ድረስ አጓጉል ምኞት አዘናጋቸው፡፡ ‹ጀነት እንገባለን በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ አለን፡፡› ይላሉ። ውሸታቸውን ነው በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ቢኖራቸው ኖሮ ሥራቸውን ባሳመሩ ነበር፡፡›

3- አማኝ ዘወትር ራሱን የሚወቅስ ሆኖ እንጂ አታገኘውም፡፡ በንግግሬ በርግጥ ምን አስቤበት ነው? በመመገቤና በመጠጣቴስ ምን ፈልጌበት ነው? ይላል፡፡ ደካማ ሰው ግን ነፍሱ አይወቅሳትም፣ አይቆጣጠራትም፣ አይመረምራትም፡፡ ዝም ብሎ ይኖራል፡፡

4 - አንድ የአላህ ባሪያ የምትመክረው ነፍስ እስካለው ድረስ መልካም ሁኔታ ላይ ነው፡፡ ያኔ ሀሳቡ ሁሉ ስለራሱና ስለ ፍፃሜው አብዝቶ መጨነቅ ይሆናል፡፡

5- ለዚህ ዓይነቱ /ለሞት ቀኑ/ ለሠራ ሰው አላህ ይዘንለት፡፡ እናንተ ዛሬ ላይ  የመቃብር ሰዎች የሆኑ ወንድሞቻችሁ የማይችሉትን ነገር ትችላላችሁ፡፡ ጤናና ትርፍ ጊዜያችሁን የድንጋጤና የምርመራ ቀን ከመምጣቱ በፊት ተጠቀሙበት፡፡

6- የዱንያ ቀን አንዱም አይመጣም እንዲህ ያለ ቢሆን እንጂ፡- ሰዎች ሆይ! እኔ አዲስ ቀን ነኝ፡፡ እኔ በኔ ውስጥ በሚሰራብኝ ነገር መስካሪ ነኝ፡፡ ፀሐይ የጠለቀች እንደሆነ እስከ እለተ ትንሳኤ ድረስ ወደናንተ የማልመለስ ነኝ፡፡

ምንጭ - ምርጥ አባባሎች
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር

https://t.me/NejashiPP
1.1K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-28 08:25:32

1.2K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-27 13:07:07 ነጃሺ ማተሚያ ቤት ለአንባቢያን ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን መርካቶ ካለው መጽሐፍ መደብር በተጨማሪ በአ/አ ለአንባቢያን ምቹ የሆነ ቦታ ላይ መደብር መክፈት ይፈልጋል፡፡ አዲሱ መደብር የት አካባቢ ቢሆን ለአብዛኛው ተጠቃሚ ምቹ ይሆናል የሚለውን ለመወሰን የደንበኞቻችንን ፍላጎት ማወቅ አስፈላጊ በመሆኑ ከታች ከተጠቀሱት አካባቢዎች ይበልጥ ምቹ የሆነውን በመምረጥ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን፡፡
public poll

ቤተል – 4
57%
@lawen7, @Ahbabu, @AbdellaS, Shehabudin

ፒያሳ – 2
29%
@Endovsiky, @Emranium

ሜክሲኮ – 1
14%
@DUJDEMMAHOM

ፍልውሃ
0%

7 people voted so far.
1.2K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-26 18:21:26 አል-ሓሪሥ አል-ሙሓሲቢ እንዲህ ይላል -
‹ ከአላህ ዘንድ በርሱ ላይ የተወረደውን ነገር የማያውቅ ሰው፤ ከርሱ ዘንድም ወደ አላህ ሊሄድ የሚችልን ነገር የማያውቅ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ›

አዎን ... በየቀኑ ጠዋትና ማታ ወዳንተ የሚወርዱትን የአላህ (ሱ.ወ.) ፀጋዎች፣ በይፋም ሆነ በስውር ወዳንተ የሚንቧቡትን ችሮታዎች የማታውቅ ከሆነ ይህ የሚያሳየው የቀልብህ እይታ የተጋረደ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም በመጋረዱ የተነሳ መጥፎን ነገር ከጥሩ ለይቶ ሊያውቅ አይችልም፡፡ ወደ ጀነት የሚያቃርበውንና  ለእሣት የሚዳርገውን ነገር አይለይም፡፡
ከዕውርነት ሁሉ ክፉው የልብ ዕውርነት ነው፡፡ ቀልብ የታወረ እንደሆነ በየጊዜው ወደ ጌታው የሚወጣውን ሥራውን መለየት ይሳነዋል፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡
ይህ መጽሐፍ አንዳንድ ከኛ የተጋረዱና የተደበቁ የአላህ ችሮታዎችን ይገልፅልናል፣ ከፍቶ ያሳየናል፡፡ በዚሁ መነሻነትም ያስተዋልናቸውን ፀጋዎች እናጣጥማለን፡፡ የደረስንባቸውን ችሮታዎች እናመሰግናለን፡፡ ቀልባችንም አላህ ላደረገልህ በጎ ነገር ጥሩ ምላሽ ይኖረዋል፡፡ የአላህን በጎነትም በበጎ ይመልሳል፡፡ እሱ የመረጠለትንም ነገር ከሌላው ነገር ሁሉ ያስበልጣል፡፡

ምንጭ ፦ የሁለት ዓለም ጀነት
ኻሊድ አቡ ሻዲ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ


https://t.me/NejashiPP
1.3K views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ